
የተከበራችሁ የቡና ባንክ አ.ማ ባለአክሲዮኖች
በኢትዮጵያ ንግድ ሕግ አንቀፅ 366/1/፣ 367/1/፣ 370፣ እና በባንኩ መመስረቻ ፅሑፍ አንቀፅ 21 እና 22 መሰረት የቡና ባንክ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 17ኛ መደበኛ እና 8ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ህዳር 12 ቀን 2019 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ አበባ ከተማ፣ ሲኤምሲ አደባባይ አካባቢ በሚገኘው፣ በአዲስ ዓለም አቀፍ የስብሰባ ማዕከል ስለሚያካሂድ፤ ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ተወካዮች በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ቦታ በጉባዔው ላይ እንድትገኙ የማህበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ የአክብሮት ጥሪውን ያቀርባል፡፡
- አክሲዮን ማህበሩን የሚመለከቱ ዋና ዋና መረጃዎች፣
- የአክሲዮን ማህበሩ ስም፡- ቡና ባንክ አክሲዮን ማህበር፣
- የአክሲዮን ማህበሩ ዓይነት፡- የባንክ ሥራ ላይ የተሰማራ አክሲዮን ማህበር፣
- የአክሲዮን ማህበሩ የተፈረመና የተከፈለ ዋና ገንዘብ /ካፒታል/፡- 6,189,559,800 ብር፣
- የአክሲዮን ማህበሩ የምዝገባ ቁጥር፡-AR/AA/3/0003357/2006፣
- የአክሲዮን ማህበሩ ዋና መ/ቤት አድራሻ፡-አዲስ አበባ፣ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 02 የቤት ቁጥር አዲስ፣
ድረ ገጽ፡ http://www.bunnabanksc.com/
- የ17ኛው ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች፣
- በባንኩ ውስጥ የተደረጉ የአክሲዮን ዝውውሮችን ማጽደቅ፤
- እ.ኤ.አ የ2025/26 የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥና መወሰን፤
- እ.ኤ.አ የ2025/26 የውጭ ኦዲተሮችን ዓመታዊ የኦዲት ሪፖርት ማዳመጥና ማጽደቅ፤
- ባንኩን ለሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት የሚያገለግሉ የውጭ ኦዲተሮችን ሹመት ማጽደቅና አበላቸውን መወሰን፣
- እ.ኤ.አ የ2026/27 ሒሳብ ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ወርሃዊ አበልና እ.ኤ.አ የ2025/26 ሒሳብ ዓመት ዓመታዊ ክፍያ መወሰን፤
- እ.ኤ.አ በ2025/26 ሒሳብ ዓመት የተጣራ ትርፍ ድልድልና ክፍፍል ላይ ተወያይቶ መወሰን፣
- የጉባዔውን ቃለጉባዔ ማጽደቅ፣ የሚሉት ናቸው፡፡
- የ8ኛው አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች፣
- የጉርሻ አክሲዮንን / Bonus Share / በተመለከተ ተወያይቶ መወሰን፤
- የባንኩን መመስረቻ ጽሁፍ ማሻሻል፤
- የጉባዔውን ቃለጉባዔ ማጽደቅ፣ የሚሉት ናቸው፡፡
ማሳሰቢያ
- በጉባዔው ላይ በአካል መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ስልጣን ባለው አካል የተሰጠ የውክልና ሰነድ ወይም በንግድ ህግ አንቀጽ 377 መሰረት ጉባዔው ከመካሄዱ ሦስት ቀን በፊት በባንኩ ዋና መ/ቤት አክሲዮን አስተዳደር ቢሮ በመቅረብ በባንኩ የተዘጋጀውን የውክልና ቅጽ በመሙላትና በመፈረም ተወካይ መሾምና ተወካዩም የውክልና ማስረጃውን በመያዝ የጉባዔው ተካፋይ ለመሆንና ድምጽ ለመስጠት የሚችል መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡ ሆኖም አንድ ባለአክሲዮን በማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ በማንኛውም ችሎታ መወከል የሚችለው አንድ ሰው ብቻ መሆኑን እናሳስባለን፡፡
- የአክሲዮን ማህበሩ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባዔው ላይ ለመሳተፍ ሲመጡ ኢትዮጵያዊ ዜግነታቸውን የሚያሳይ የብሔራዊ መታወቂያ / ፋይዳ/ እና የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ዋናውንና ኮፒ በመያዝ በጉባዔው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡ እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የሆኑ የውጭ አገር ዜግነት ያላቸው ባለአክሲዮኖች ትውልደ ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ቀኑ ያላለፈበት መታወቂያ /ቢጫ ካርድ/ ይዘው እንዲቀርቡ እናሳውቃለን፡፡ የድርጅትና የማህበር ተወካዮች ድርጅቱን/ማህበሩን ወክለው በስብሰባው እንዲገኙና ድምፅ እንዲሰጡ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ይዘው መቅረብ ያለባቸው መሆኑን በአክብሮት እናስታውቃለን፡፡
- የሚወከሉ ባለአክሲዮኖች የሚቀበሉት የውክልና መጠን የራሳቸውን አክሲዮን ጨምሮ ከባንኩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ ከአስር በመቶ /10% / መብለጥ የለበትም፡፡
- ባለአክሲዮኖች በስራ ላይ ያሉ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትና ሰራተኞች በባለአክሲዮኖች ጉባዔ ላይ እንዲሳተፉና ድምጽ እንዲሰጡ መወከል አይችሉም፡፡
- የጉባዔው ቦታ ከሲኤምሲ ቤቶች በተቃራኒ ከፀሐይ ሪል ስቴት አጠገብ ወደወሰን መሄጃ በስተግራ በኩል የሚገኘው አዲስ ዓለም አቀፍ ኮንቬንሽን ማዕከል መሆኑን ያስታውሱ፡፡
የቡና ባንክ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ
| Call Us 8501
የባለራዕዮች ባንክ! Bank of the visionaries!
|
| www.bunnabanksc.com |