የቡና ባንክ አ.ማ 15ኛ የባለአክስዮኖች መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ታህሳስ 06 ቀን 2017 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሔዳል፡፡ ጉባዔው በዕለቱ ባንኩን ለቀጣይ ሶስት ዓመታት የሚመሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ይመርጣል፡፡
በመሆኑም፣በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር SBB/91/2024 አንቀጽ 9 ንዑስ አንቀጽ 9.3 በተደነገገው መሰረት መላው የባንካችን ባለአክስዮኖች በእለቱ ቢያንስ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ዕጩዎችን መጠቆምና መምረጥ እንድትችሉ ይህ የጥቆማና ምርጫ መስፈርቶችን የያዘ ማስታወቂያ ወጥቷል፡፡፡
የጥቆማና ምርጫ መስፈርቶች
- የቦርድ አባላት ምርጫ ከሚደረግበት ዕለት ሁለት ዓመታት በፊት ባለአክሲዮን ሆኖ የተመዘገበ፤
- በቦርድ አባልነት ለማገልገል ፈቃደኛ የሆነ፤
- እውቅና ካለው ከፍተኛ የትምህርት ተቋም ቢያንስ የመጀመሪያ ዲግሪ ወይም የዚህ ተመጣጣኝ የትምህርት ደረጃ ያለው፤
- በባንክ ሥራ ወይም በስጋት አስተዳደር ወይም በፋይናንስ ወይም በአካውንቲንግ ወይም በማኔጀመንት ወይም ኢኮኖሚክሰ ወይም በሕግ ወይም ቢዝነስ አስተዳደር ወይም በኦዲቲንግ ወይም በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ወይም በኢንቨስትመንት ማኔጅመንትና ዘላቂነት የሙያ ዘርፎች የተመረቀ እና በቢዝነስ አስተዳደር፣ በባንኪንግ እና ወይም ፋይናንስ ቢያንስ ሰባት ዓመት የሥራ ልምድ ያለው፤
- ቢያንስ ሁለት ሴቶች የቦርድ አባል ሆነው መመረጥ አለባቸው፡፡
- ታማኝ፣ ሀቀኛ፣ መልካም ዝና እና ሥነ ምግባር ያለው፤
- ከአራት በላይ በሆኑ ሌሎች ድርጅቶች ውስጥ በቦርድ ዳይሬክተርነት እየሠራ የማይገኝ እና በቂ ጊዜ በመመደብ ኃላፊነቱን መወጣት የሚችል፤
- በሌላ የፋይናንስ ተቋም የዳይሬክተሮች ቦርድ አባል ወይም ዋና ስራ አስፈጻሚ እና የሌላ ባንክ ሠራተኛ ያልሆነ፤
- ማንኛውም በኢትُዮጵያ ውስጥ ሆֲነ ከኢትُዮጵያ ውጭ እምነት በማጉደል፣ ወይም በማጭበርበር ወንጀል ተከሶ በፍርድ ቤት የጥፋተኝነት ውሳኔ ያልተሰጠበት፤
- ከባንኩ ጋር ምንም ዓይነት የጥቅም ግጭት የሌለው፣
- የባንክ ብድር ወስዶ ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ የተበላሸ ብድር የሌለው እና ግብር የከፈለ፤የተሳሳተ የፋይናንስ መረጃ ወይም መግለጫ ያላቀረበ፣
- ዳይሬክተር ወይም ዋና ሥራ አስፈጻሚ ወይም ከፍተኛ ሥራ አስፈጻሚ ወይም ባለቤት በሆነበት ድርጅት የመክሰር ሂደት ያላስጀመረ ወይም መክሰሩ ያልተወሰነበት፤ ንብረት ያልተወረሰበት፣ ንብረቱ በመክሰር ውሳኔ መሠረት እንዲተዳደር ያልተደረገበት ወይም የባንክ ብድር መክፈል ባለመቻሉ ንብረቱ ለእዳ ማስመለሻነት ያልተሸጠበት፤
- ኃላፊነት በጎደለው ወይም በግዴለሽነት ወይም በማጭበርበር ወይም በሕገወጥ የንግድ ሥራ ምክንያት ኪሳራ በደረሰበት ሌላ ሰው በተገኘ ገንዘብ በፋይናንስ ተቋም የአክሲዮን ግዥ ያልፈፀመ፤
- በቂ ስንቅ/ገንዘብ ሳይኖረው የብሔራዊ ባንክ መመሪያን በመጣስ የቼክ ክፍያ ፈጽሞ የባንክ ሂሳቡ ያልተዘጋበት፤
- በተጨማሪም፣ አግባብነት ባላቸው ህጎችና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በወጡ መመሪያዎች ላይ የተገለጹ ሌሎች መመዘኛዎችን የሚያሟላ፣ ሊሆን ይገባል፡፡
ማሳሰቢያ
• አንድ ባለአክስዮን ራሱን በእጩነት መጠቆም ይችላል፡፡
• ከማህበሩ ፀሐፊ በስተቀር ሁለት የባንኩ ሠራተኞች ሊመረጡ ይችላሉ፡፡
• ከላይ የተጠቀሱት መስፈርቶች ህጋዊ ሰውነት ያለው ተቋምን ለሚወክለው የተፈጥሮ ሰውም ይሰራሉ፡፡
• የአስመራጭ ኮሚቴ አባል የሆነ ለቦርድ አባልነት መመረጥ አይችልም፡፡
• የእጩ ቦርድ አባላት ጥቆማና ምርጫ የሚካሔደው በጉባዔው እለት ይሆናል፡፡
• የቦርድ አባላት ጥቆማና ምርጫ የሙያና ጾታ ስብጥርን ማረጋገጥ አለበት፡፡
• መስፈርቱን እስካሟሉ ድረስ ነባር የቦርድ አባላት ለእጩነት ሊጠቆሙ ይችላሉ፡፡
• በጥቆማ ወቅት የጠቋሚዎች ስምና የአክሲዮን መጠን መገለጽ አለበት፡፡
• የቦርድ አባላትና የባንኩ ሠራተኞች ባለአክሲዮኖችን ወክለው ድምጽ መስጠት አይችሉም፡፡
• አንድ ባለአክሲዮን የሚጠቁመውን እጩ የትምህርትና የሥራ ልምድ ማስረጃዎች ቅጂ ይዞ መምጣትና ለአስመራጭ ኮሚቴው መስጠት አለበት፡፡
• በወንድ ጾታ የተገለፀው ለሴት ጾታም ያገለግላል፡፡
• በባንኩ መመሥረቻ ጽሁፍ መሠረት የሚመረጡት ዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ቁጥር ዘጠኝ ሲሆን፣ በዕለቱ በመጀመሪያ የምርጫ ፖሊሲና ደንብ ከጸደቀ በኋላ አስመራጭ ኮሚቴ ይመረጣል፣ በሚያዝለት ፕሮግራም መሰረት የዳሬክተሮች ቦርድ ምርጫ ይከናወናል፡፡ ምርጫውም ተደማጭነት በሌላቸው ባለአክስዮኖች ተጠቁመው የሚመረጡ (ምድብ 1) ፣ በሁሉም ባለአክስዮኖች ተጠቁመው የሚመረጡ (ምድብ 2) እንዲሁም ሥራ ላይ ባለው ቦርድ ተመልምለው በሁሉም ባለአክስዮኖች የሚመረጡ ገለልተኛ ዳይሬክተሮችን (ምድብ 3) በመምረጥ በሶስት ቡድን ተከፍሎ በቅደምተከተል የሚከናወን ይሆናል፡፡
የማህበሩ ፀሐፊ
ቡና ባንክ አ.ማ
የባለራዕዮች ባንክ!!!