Bunna Bank

የቡና ባንክ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 15ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ

በኢትዮጵያ ንግድ ሕግ አንቀፅ 366/1/፣ 367/1ና2/፣ 370፣ 394/1፣2ና5/ እና በባንኩ መመስረቻ ፅሑፍ አንቀፅ 21 መሰረት የቡና ባንክ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 15ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ ታህሳስ 6 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ በሚሊኒየም አዳራሽ ይካሄዳል፡፡ ስለሆም የባንኩ ባለአክሲዮኖች በአካል ወይም በሕጋዊ ተወካዮቻችሁ አማካኝነት በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ቦታ በጉባዔው ላይ እንድትገኙ የማህበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ የአክብሮት ጥሪውን ያቀርባል፡፡
የአክሲዮን ማህበሩ ዋና መ/ቤት አድራሸ፡ አዲስ አበባ፣ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 02 የቤት ቁጥር አዲስ፣
ድረ ገጽ፡ http://www.bunnabanksc.com/
የአክሲዮን ማህበሩ የምዝገባ ቁጥር፡ AR/AA/3/0003357/2006፣
የአክሲዮን ማህበሩ የተፈረመና የተከፈለ ዋና ገንዘብ /ካፒታል/፡ 4,826,220,600 ብር
የ15ኛ ዓመታዊ መደበኛ ጠቅላላ ጉባዔ አጀንዳዎች፣

  1. በባንኩ ውስጥ የተደረጉ የአክሲዮን ዝውውሮችን እና የአዲስ አክሲዮኖችን ሽያጭ ማፅደቅ፤
  2. የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማና ምርጫ አፈጻጸም ፖሊሲና አሰራር ደንብን ተወያይቶ ማጽደቅ፣
  3. የዳይሬክተሮች ቦርድ ጊዜያዊ አስመራጭ ኮሚቴ መምረጥ፣
  4. እ.ኤ.አ የ2023/24 የዳይሬክተሮች ቦርድ ዓመታዊ ሪፖርት ማዳመጥና ተወያይቶ መወሰን፤
  5. እ.ኤ.አ የ2023/24 የውጭ ኦዲተሮችን ዓመታዊ የኦዲት ሪፖርት ማዳመጥና ተወያይቶ ማጽደቅ፤
  6. በዘመኑ የተጣራ ትርፍ አደላደል እና አከፋፈል ላይ የቀረበውን የውሳኔ ሐሳብ ተወያይቶ ማጽደቅ፤
  7. እ.ኤ.አ የ2024/25 በጀት ዓመት የዳይሬክተሮች ቦርድ ወርሃዊ አበልና እ.ኤ.አ የ2023/24 በጀት ዓመት ዓመታዊ ክፍያ ላይ ተወያይቶ መወሰን፤
  8. ባንኩን ለሚቀጥሉት ሦስት ዓመታት የሚያገለግሉ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን መምረጥ፣የሚሉት ናቸው፡፡
    ማሳሰቢያ
  9. በጉባዔው ላይ በአካል መገኘት የማይችሉ ባለአክሲዮኖች ውል ለማዋዋል ስልጣን ባለው አካል በስብሰባው ላይ ለመገኘትና ድምፅ ለመስጠት የሚያስችል የውክልና ሰነድ ወይም በንግድ ህግ አንቀጽ 377 መሰረት ጉባዔው ከመካሄዱ ሦስት ቀን በፊት ቦሌ መንገድ ከወሎ ሰፈር አደባባይ ቀጥሎ ሩዋንዳ መታጠፊያ ከመደረሱ በፊት በሚገኘው የባንኩ ዋና መ/ቤት 4ኛ ፎቅ የባንኩ ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ድረስ በመቅረብ በባንኩ የተዘጋጀውን የውክልና ቅጽ በመሙላትና በመፈረም ተወካይ መሾምና ተወካዩም የውክልና ማስረጃውን በመያዝ የጉባዔው ተካፋይ ለመሆንና ድምጽ ለመስጠት የሚችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡ ሆኖም አንድ ባለአክሲዮን በማህበሩ ጠቅላላ ጉባዔ በማንኛውም ችሎታ መወከል የሚችለው አንድ ሰው ብቻ መሆኑን እናሳስባለን፡፡
  10. የአክሲዮን ማህበሩ ባለአክሲዮኖች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጉባዔው ላይ ለመሳተፍ ሲመጡ ኢትዮጵያዊ ዜግነታቸውን የሚያሳይ የታደሰ መታወቂያ ወይም ፓስፖርት ወይም መንጃ ፈቃድ ዋናውንና ኮፒ በመያዝ በጉባዔው ላይ መሳተፍ ይችላሉ፡፡ እንዲሁም ትውልደ ኢትዮጵያዊያን የሆኑ ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ባለአክሲዮኖች ትውልደ ኢትዮጵያዊያን መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ቀኑ ያላለፈበት መታወቂያ/ቢጫ ካርድ/ ይዘው እንዲቀርቡ እናሳውቃለን፡፡ የድርጅትና የማህበር ተወካዮች ድርጅቱን/ማህበሩን ወክለው በስብሰባው እንዲገኙና ድምፅ እንዲሰጡ የሚያረጋግጥ ማስረጃ ይዘው መቅረብ ያለባቸው መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
  11. የሚወከሉ ባለአክሲዮኖች የሚቀበሉት የውክልና መጠን የራሳቸውን አክሲዮን ጨምሮ ከባንኩ የተፈረመ ዋና ገንዘብ ከአስር በመቶ መብለጥ የለበትም፡፡
  12. በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መመሪያ ቁጥር SBB/91/2024 አንቀጽ 20/3/ መሰረት የባንኩ የቦርድ አባላትና ሰራተኞች በማናቸውም የባለአክሲዮኖች ጉባዔ ላይ ማንኛውንም ባለአክሲዮን ወክለው መገኘት አይችሉም፡፡
    የዳይሬክተሮች ቦርድ
    የቡና ባንክ አ.ማ

[ivory-search id="5747" title="Custom Search Form"]

This will close in 0 seconds

error: