- ታህሳስ 03 ቀን 2014 ዓ.ም በተደረገው የባንኩ ባለአክሲዮኖች 5ተኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ የባንኩ ካፒታል ወደ ብር 6.5 ቢሊየን እንዲያድግ በሙሉ ድምጽ መወሰኑ ይታወሳል፡፡
- በመሆኑም የባለአክሲዮኖች 5ተኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባኤ ለዳይሬክተሮች ቦርድ በሰጠው ስልጣን መሰረት አዲስ አክሲዮኖችን በባንኩ የመተዳደርያ ደንብና አግባብነት ባላቸው የንግድ ህጉ ድንጋጌዎች መሰረት ለነባር ባለአክሲዮኖች እ.ኤ.አ. ግንቦት 31 ቀን 2022 ዓ.ም በባንኩ ባላቸው አክሲዮን መጠን ልክ እንዲደለደል ስለወሰነ ነባር ባለአክሲዮኖች የተደለደለላችሁን አክሲዮን ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 3 ላይ በተገለጸው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት አዲስ አበባ ቦሌ ሩዋንዳ ማዞሪያ በሚገኘው የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት 4ተኛ ፎቅ የባንኩ አክሲዮን አስተዳደር ዋና ክፍል ወይም በአቅራቢያችሁ በሚገኙ የባንኩ ቅርንጫፎች አስፈላጊ የሆኑ ማስረጃዎችን ይዞ በአካል በመቅረብ የተደለደለላችሁን አክሲዮን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እናስታውቃለን፡፡
- ስለሆነም ባለአስዮኖች የተደለደለላችሁን የአክሲዮን ድርሻ እ.ኤ.አ. ከሰኔ 15 ቀን 2022 እስከ ሐምሌ 15 ቀን 2022 ድረስ የባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ወይም በየአካባቢያችሁ ባሉ የባንኩ ቅርንጫፎች ቀርባችሁ መግዛት የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡ በተጨማሪም ከተደለደለላችሁ አክሲዮን በላይ ተጨማሪ አክሲዮን መግዛት የምትፈልጉ ከላይ በተጠቀሰው ቀን ውስጥ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን በዚሁ አጋጣሚ እንገልጻለን፡፡
- ከላይ በተራ ቁጥር 3 በተጠቀሰው የጊዜ ሰሌዳ ውስጥ ቀርቦ አክሲዮኖቹን ያልገዛ ባለአክሲዮን የመግዛት የቅድሚያ መብቱን በፈቃዱ እንደተወ ስለሚቆጠር የአክሲዮን ድልድል ድርሻውን ባንኩ ለሌሎች ተጨማሪ አክሲዮን ለሚፈልጉ ነባር ባለአክሲዮኖች ወይም ለሌሎች አዲስ አክሲዮን ገዢዎች ለሽያጭ የሚያቀርብ መሆኑን አስቀድመን እናስታውቃለን፡፡
ማሳሰቢያ፡
- ከላይ በተገለፀው መልኩ የተደለደለላችሁን አክሲዮኖች ለመግዛት በግምባር የምትቀርቡ ባለአክሲዮኖች የኢትዮጵያ ዜጋ መሆናችሁን የሚያረጋግጥ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ /ፖስፖርት/ መንጃ ፈቃድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ ይዛችሁ መቅረብ የሚጠበቅባችሁ ሲሆን፤ በግምባር መቅረብ የማትችሉ ባለአክሲዮኖች አግባብነት ባለው አካል ተረጋግጦ የተመዘገበና የተሰጠ የውክልና ስልጣን ይዘው በሚቀርቡ ወኪሎቻችሁ በኩል የተደለደለላችሁን አክሲዮን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- የባለአክሲዮን ወኪሎች የራሳቸውን ሕጋዊ መታወቂያና የውክልና ስልጣን ማስረጃ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ እንዲሁም ወካይ ባለአሲዮኖች የኢትዮጵያ ዜጋ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የታደሰ የቀበሌ መታወቂያ /ፖስፖርት/ መንጃ ፈቃድ ፎቶ-ኮፒ ይዘው መቅረብ የሚጠበቅባቸው ሲሆን፤ ተወካዩ የወካይ ባለአክሲዮን ዜግነት ለማረጋገጥ ከላይ በተገለፀው መልኩ ስለሚያቀርቡት ሰነድ ትክክለኛነት ባንኩ በሚያዘጋጀው ፎርም ላይ በመፈረም ማረጋገጥ የሚጠበቅባቸው መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡፡
ለተጨማሪ መረጃ የባንኩን አክሲዮን አስተዳደር በ0111-580880 ደውላችሁ ማነጋገር የምትችሉ መሆኑን አንገልፃለን፡፡