Bunna Bank

bunna

“አቦል ደሞዜ ” የተሰኘ የቅድመ ደሞዝ ብድር አገልግሎት በይፋ ተጀመረ

አዲስ አበባ: – ታህሳስ 12, 2017 – ቡና ባንክ እና ካቻ ዲጂታል ፋይናንሻል ሰርቪስ የቅድመ ደሞዝ ብድር አገልግሎት ተጠቃሚ የሚያደርግ “አቦል ደሞዜ” የተሰኘ የዲጂታል ብድር እና ቁጠባ አገልግሎት በዛሬው እለት በይፋ አስጀምረዋል ። ለተቀጣሪ ደመወዝተኛ የህብረተሰብ ክፍል አገልግሎት እንዲሰጥ የተነደፈው “አቦል ደሞዜ” ለሰራተኞች የደሞዝ መደረሻ የገንዘብ ፍላጎትን ለማርካት የተዘጋጀ የቅድመ ደመወዝ ብድር አገልግሎት ሲሆን ሰራተኞች ከክፍያ ቀናቸው በፊት በሚገጥማቸው የገንዘብ እጥረት ወቅት የወር ደሞዛቸውን የተወሰነ ክፍል ያለምንም ማስያዣ በብድር እንዲያገኙ የሚያስችል የፋይናንሺያል አገልግሎት ነው። በዚህ አዲስ አገልግሎት ተጠቃሚዎች የደመወዛቸውን 33% ወይም 50% በቀላሉ ካሉበት ሆነው በካቻ የሞባይል አፕሊኬሽን ማግኘት ሲችሉ ምቹ በሆነ የአከፋፈል ዘዴ በተቀመጠው ቀነ ገደብ መሰረት ብድራቸውን መክፈል የሚችሉበት አማራጭም ተቀምጦላቸዋል ። ሰራተኞች አገልግሎቱን ለማግኘት የቡና ባንክ ወይም የካቻ ደንበኞች መሆን እንደሚጠበቅባቸው የቡና ባንክ ቺፍ ባንኪንግ ኦፊሰር አቶ መንክር ሀይሉ ሲገልፁ “’አቦል ደሞዜ የደንበኞቻችንን ተለዋዋጭ ፍላጎት የሚያሟሉ አዳዲስ እና ተደራሽ የሆኑ የፋይናንስ መፍትሄዎችን ለማቅረብ ያለንን ቁርጠኝነት ያንፀባርቃል” ነው ያሉት ። አገልግሎቱን ያበለፀገው የካቻ ዲጂታል ፋይናንሻል ሰርቪስ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አብርሀም ጥላሁን በበኩላቸው “ካቻ በተለመደው የፋይናንስ አገልግሎት ተጠቃሚ ያልነበረውን ሰፊ የህብረተሰብ ክፍል ለማገልገል የዲጂታል ፋይናንስ አገልግሎትን እንደ አማራጭ ይዞ የመጣ ኩባንያ መሆኑን ገልጸው ከቡና ባንክ ጋር በመቀናጀት ይህንን የደሞዝ መዳረሻ ብድር አገልግሎትን ሲያቀርብ ታላቅ ኩራት እየተሰማው ነው ” ብለዋል ። ቡና ባንክ እና ካቻ ዲጂታል ፋይናንሺያል ሰርቪስ የባንክ አገልግሎት አሰጣጥና ተደራሽነት የሚያሰፉ አዳዲስ አገልግሎቶችን ለማበልፀግና ለማገልገል ዘላቂ አጋርነት የፈጠሩ ኩባንያዎች ሲሆኑ “አቦል ደሞዜ” ከዚህ ትብብር የተወለደ የመጀመሪያው አገልግሎት መሆኑም በማስጀመሪያ መርሀግብሩ ላይ ተገልጿል ። ከተመሰረተ 15 ዓመታት ያስቆጠረው ቡና ባንክ በባንክ ኢንዱስትሪው ዘርፍ ላለፉት 15 ዓመታት አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝና ከ4 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን ያፈራ የፋይናንስ ተቋም ሲሆን በአጋርነት አገልግሎቱን ያበለፀገው ካቻ ዲጂታል ፋይናንሺያል ሰርቪስ አ.ማ ደግሞ የብሔራዊ ክፍያ ስርዓትን ለመደንገግ በወጣው አዋጅ ቁጥር 718/2003 እና የክፍያ መፈፀሚያ ሰነድ አውጪዎችን ለማስተዳደር በኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በወጣው መመሪያ ቁጥር ONPS/01/2020 መሰረት የሞባይል ገንዘብ ዝውውር አገልግሎትን ጨምሮ የተለያዩ የክፍያ ሰነዶችን ለማውጣት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቁጥር NPS/PII/002/2022 ፈቃድ ያገኘ የመጀመሪያው የግል የክፍያ ሰነድ አውጪ በመሆን አገልግሎቱን ማቅረብ ከጀመረ ሁለት አመት ተኩል አስቆጥሯል።

“አቦል ደሞዜ ” የተሰኘ የቅድመ ደሞዝ ብድር አገልግሎት በይፋ ተጀመረ Read More »

Bunna Bank held its annual general meeting of shareholders

Bunna Bank S.C. held its 15th Annual General Meeting of Shareholders on Sunday, December 15, 2024, at the Addis Park-Millennium Hall. A large number of shareholders attended the meeting, where the Chairperson of the Board of Directors, Ambassador Alemayehu Sewagen, presented the bank’s 2023/24 annual report. At the annual meeting, Ambassador Alemayehu Sewagen shared that the bank recorded a profit before tax of 930.1 billion birr for the fiscal year. The bank’s deposits reached 43.87 billion birr, showing a 20 percent increase from the previous fiscal year. Of the total deposits mobilized during the fiscal year, 2.79 billion birr was received from savings deposits, 1.55 billion birr from demand deposits, 2.62 billion birr from time deposits, and 307.0 million birr from interest-free banking services. Ambassador Alemayehu emphasized in his speech that the Ethiopian banking sector faced significant challenges during the past fiscal year due to high inflation, foreign exchange shortages, overlapping regulatory guidelines, and conflicts in various regions. These issues severely impacted not only banks’ lending but also their deposit collection activities. Despite these challenges, Bunna Bank maintained its profitability and competitiveness. According to the report, the bank disbursed 4.1 billion birr in loans to various economic sectors, increasing the total loan amount by 11.8 percent to 38.87 billion birr. The decline in remittances from abroad and the significant slowdown in export activities negatively affected the bank’s performance in terms of foreign exchange earnings, which totaled 167.6 million USD for the year ended June 30, 2024. The bank’s total assets increased by 8.14 billion birr during the fiscal year, reaching 54.53 billion birr. The paid-up capital grew by 549.2 million birr, bringing the total to 4.83 billion birr. Bunna Bank increased its number of deposit account customers by 968,819 during the fiscal year, registering a growth of 31.8 percent, bringing the total customer base to 4,019,072. The number of cash payment machines installed at branches, hotels, and commercial service points reached 200 in the 2023/24 fiscal year. The total number of card banking users increased to 413,892, with 1.39 billion birr transacted through these machines. Additionally, mobile and internet banking users facilitated over 21.1 billion birr in cash transactions. The bank with its service brand called “KHADIM” for its interest-free banking, mobilized deposits totalling 1.93 billion birr. The bank implemented a risk management program in line with the National Bank of Ethiopia’s standards and approved a five-year corporate strategic plan for 2023-2027, along with human resources, digital transformation, and information technology strategies. The Chairman emphasized the bank’s next strategic focus areas, including monitoring the implementation of the five-year plan, strengthening resource mobilization, and expanding digital banking services. He thanked the National Bank of Ethiopia for its support and encouraged the Bunna Bank community to work together towards continued success. Founded 15 years ago, Bunna Bank serves over 14,000 shareholders and more than 4,100 permanent employees. The bank offers conventional, digital, and interest-free banking services through its 474 branches nationwide.                      December 15-2024 | Adjourned!

Bunna Bank held its annual general meeting of shareholders Read More »

ቡና ባንክ ዓመታዊ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔውን አካሄደ

ከግብር በፊት ብር 930.1 ሚሊዮን ብር አትርፏል ። የባንኩ አጠቃላይ ሀብት ብር 54.53 ቢሊዮን ደርሷል፡፡ የተቀማጭ  ደንበኞቹን ቁጥርም 4, 019, 072 ማድረስ ችሏል። ቡና ባንክ አ.ማ ዓመታዊውን የባለአክሲዮኖች 15ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ እሁድ ታህሳስ 6 ቀን 2017 ዓ.ም አካሂዷል። በአዲስ ፓርክ ሚሊኒየም አዳራሽ በተካሄደውና በርካታ ቁጥር ያላቸው ባለአክሲዮኖች በታደሙበት በዚሁ ጉባዔ ላይ የቡና ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር አምባሳደር ዓለማየሁ ሰዋገኝ የባንኩን የ2023/24 ዓመታዊ ሪፖርት ለባለአክሲዮኖች በንባብ አቅርበዋል። ሪፖርቱ በቀረበበት ወቅት እንደተገለጸው ባንኩ በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ከግብር በፊት 930.1 ቢሊየን ብር ትርፍ ያስመዘገበ ሲሆን በቀረበው ሪፖርት ላይ ይፋ እንደተደረገው ባንኩ እ.ኤ.አ ሰኔ 30 ቀን 2024 በተጠናቀቀው የበጀት ዓመት የባንኩ ተቀማጭ ገንዘብ ካለፈው በጀት ዓመት 20 በመቶ ዕድገት በማሳየት 43.87 ቢሊዮን ብር ሊደርስ ችሏል። ከዚህም በበጀት ዓመቱ ከተሰበሰበው አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ውስጥ ከቁጠባ ሂሳብ 2.79 ቢሊዮን ብር ፣ ከተንቀሳቃሽ ሂሳብ 1.55 ቢሊዮን ብር ፣ ከጊዜ ገደብ ተቀማጭ 2.62 ቢሊዮን ብር ያገኘ ሲሆን ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎትም 307.0 ሚሊዮን ብር ድርሻ እንዳለቸው ሪፖርቱ ያሳያል። አምባሳደር ዓለማየሁ በንግግራቸው እንዳሰመሩበት ከሆነ ባለፈው የበጀት ዓመት እንደሃገር በተከሰተው ከፍተኛ የዋጋ ንረት ፣ በውጭ ምንዛሬ እጥረት፣ ተደራራቢ የሆኑ የተቆጣጣሪ አካላት መመሪያዎች መውጣትና ተግባራዊ መሆን፣ እንዲሁም በተለያዩ ክልሎች የተከሰቱ ግጭቶችና ከፍተኛ የዋጋ ግሽበት የፈጠረው የኑሮ ውድነት ሳቢያ የኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ ከፍተኛ የሆነ ተግዳሮት ተጋርጦበት ነበር ያሉ ሲሆን እነዚህ ችግሮች የባንኮችን የማበደር ብቻ ሳይሆን ተቀማጭ የማሰባሰብ እንቅስቃሴም በእጅጉ ፈትነውታል። ይህም በውጤቱ የባንኮችን የመክፈል እና የማበደር አቅም በእጅጉ ተፈታትኖታል። አክለውም ይሁንና ባንካችን  በኢንደስትሪው ላይ የተጋረጡትን ፈተናዎች ተቋቁሞ በዚህ ጠንካራ ውድድር ውስጥ መዝለቅ በመቻሉም አትራፊነቱን አስጠብቆ ቀጥሏል ብለዋል። በቦርድ ሊቀመንበሩ የቀረበው ሪፖርት ላይ እንደተመለከተው ባንኩ በዓመቱ ውስጥ ለተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች በአጠቃላይ 4.1 ቢሊዮን ብር አበድሯል። ይህም ቡና ባንክ በአጠቃላይ ለተለያዩ የኢኮኖሚ ዘርፎች ያበደረውን የገንዘብ መጠን በ11.8 በመቶ በማሳደግ 38.87 ቢሊዮን ብር አድርሶታል። ከውጭ ሃገር የሚላክ ሀዋላ ከላይ በተገለጹት ዓለምአቀፋዊና ሃገራዊ ችግሮች ባስከተሉት ተጽእኖ ሳቢያ መቀነሱ እንዲሁም የኤክስፖርት ስራ ጉልህ በሆነ መልኩ መቀዛቀዙ በውጭ ምንዛሪ ግኝት በኩል የባንኩን አፈፃፀም በታቀደው መልኩ እንዳይከናወን አሉታዊ ጫና ያሳደረ ሲሆን የቦርድ ሊቀመንበሩ ሪፖርት በዓመቱ የባንኩ የውጭ ምንዛሬ ግኝት 167.6ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር መሆኑንም ጠቁሟል።   ያለፈው ዓመት የውጭ ምንዛሪ እጥረት ኢንደስትሪው ላይ የፈጠረው ጫና የባንኩን የውጭ ምዛሬ ግኝቱን ያሳነሰው ቢሆንም በቀጣይ የደንበኞቹን ፍላጎት በማርካት የውጭ ምንዛሪ ግኝቱን በበለጠ ለማሳደግ ካለው ፍላጎት አንፃር ከታወቁ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች እና ባንኮች ጋር የጀመረውን ስራ አጠናክሮ  እንደሚቀጥል ሪፖርቱ አመልክቷል። በቦርዱ ሊቀመንበር አምባሳደር ዓለማየሁ ሰዋገኝ ሪፖርት ውስጥ ከተካተተው አንዱ የባንኩን ጠቅላላ ሃብት የተመለከተ መረጃ ሲሆን እንደሪፖርቱ የባንኩ ጠቅላላ ሃብት በበጀት ዓመቱ የ8.14 ቢሊዮን ብር ዕድገት አሳይቶ 54.53 ቢሊዮን ብር ደርሷል። ሊቀመንበሩ ባቀረቡት የዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት እንደተብራራው የባንኩ የተከፈለ ካፒታል በበጀት ዓመቱ የብር 549.2 ሚሊየን ብር እድገት አሳይቷል። ይህም የባንኩን አጠቃላይ የተከፈለ ካፒታል መጠን 4.83 ቢሊዮን ብር አድርሶታል፡፡ በቀረበው ሪፖርት ቡና ባንክ ለደንበኞቹ ያለውን ተደራሽነት ብሎም የተቀማጭ ማሰባሰቡን ሥራ ለማሳደግ የጀመረውን ጥረት አጠናክሮ በመቀጠል ምቹ የባንክ አገልግሎቶችን በማቅረብና አዳዲስ ደንበኞችን በማፍራት ረገድ በተደረገው እንቅስቃሴ ባንኩ በበጀት ዓመቱ የተቀማጭ ሂሳብ ደንበኞቹን ቁጥር በ 968,819 ከፍ በማድረግ የ31.8 በመቶ ዕድገት ማስመዝገብ መቻሉም ተብራርቷል። ይህም አፈጻጸም የባንኩን አጠቃላይ የደንበኞች ቁጥር በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ወደ 4,019,072 ከፍ አድርጎታል። የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎትን በተመለከተ በ2023/24 በጀት ዓመት በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ የባንኩ ቅርንጫፎች፣ ሆቴሎች፣ እና የንግድ አገልግሎት መስጫ ቦታዎች ላይ የተተከሉ የገንዘብ መክፈያ ማሽኖች ቁጥር 200 ደርሷል።  በተመሳሳይም ሪፖርቱ እንደጠቆመው የባንኩ አጠቃላይ የካርድ ባንኪንግ ተጠቃሚዎች ቁጥር 413,892 የደረሰ ሲሆን በባንኩ የገንዘብ መክፈያ ማሽኖች በበጀት ዓመቱ 1.39 ቢሊየን ብር ማንቀሳቀስ መቻሉም ተጠቁሟል። በተያያዘ የሞባይልና ኢንተርኔት ባንኪንግ ተጠቃሚዎች ቁጥር ማደጉን ፣ በዚህም በድምሩ 21.1 ቢሊየን ብር በላይ የገንዘብ ልውውጥ መደረጉን ሪፖርቱ ገልጻል፡፡ ቡና ባንክ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የራሱ ልዩ መለያ እና የንግድ ስም እንዲኖረው በማስቻል “ኻዲም” (KHADIM)” የተሰኘ የአገልግሎት መለያ በመያዝ በአጭር ጊዜ ውስጥ ውጤታማ ስራ መስራት መቻሉን ሪፖርቱ ይገልጻል፡፡ ይህም በባንኩ ከወለድ ነፃ የባንክ አገልግሎት የተገኘውን አጠቃላይ የተቀማጭ ገንዘብ መጠን ብር 1.93ቢሊዮን አድርሶታል ብሏል ሪፖርቱ። ሪፖርቱ በዋናነት ካካተታቸው አብይ ተግባራት መካከል ስጋት ተጋላጭነትን መቋቋም እና ኮምፕሊያንስን በሚመለከት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባቀመጠው መስፈርተ መሰረት ከኮርፖሬት ቢዝነስ ስትቴጂው ጋ የሚጣጣም ይስጋ አስተዳደር ፐሮግራም መተግበሩ የተገለጸ ሲሆን እ.ኤ.አ ከ2023-2007 የባንኩን የአምስት ዓመት ኮርፖሬት ስትራቴጂክ ዕቅድ፣ የሰው ሀብት ስትራቴጂ፣ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ስትራቴጂና የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ስትራቴጂዎችን ማጽደቁም ተገልጿል። የቦርድ ሊቀመንበሩ እንደተናገሩት ባንኩ ቀጣይ የባንኩ ስትራቴጂያዊ የትኩረት አቅጣጫዎችነ የተቀሱ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ  የአምስት ዓመቱን ኮርፖሬት ስተራጂክ ዕቅድ ትግበራ መከታተል፣ የሀብት ማሰባበሰብ ስራን ማጠናከር የዲጂታል ባንክና የአይቲ ቴክኖሎጂ አገልግሎቶችን ማስፋፋትና ሌሎችም እንደሚገኙበት ሪፖርቱ ያሳያል፡፡ በመጨረሻም የቦርድ ሊቀመንበሩ ባስተላለፉት መልዕክት ሁሉም የቡና ኮሚዩኒቲ አባላት እጅ ለእጅ ተያይዘው ባንኩን ወደተሻለ ደረጃ ለማሻገር እንዲሰሩ የጠየቁ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እንደሁልጊዜው ለባንኩ ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ በመስጠት በዘርፉ ጤናማ ውድድር እንዲኖር ከፍተኛ አስተዋፅኦ ማድረጉን በማመስገን ሁሉም የቡና ኮሚዩኒቲ ይህንኑ ስኬታማ ጉዞ ለማሳካት እንዲሰራ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡ የባለራዕዮች ባንክ የሆነው እና ከተመሰረተ 15 ዓመታትን ያስቆጠረው ቡና ባንክ ከ14 ሺህ በላይ ባለአክሲዮኖችና ከ4100 በላይ ቋሚ ሰራተኞች ያሉት በመላው የአገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ 474 ቅርንጫፎቹ የኮንቬንሽናል፣ ዲጂታል አንዲሁም ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎቶችን የሚሰጥ ባንክ ነው።                         

ቡና ባንክ ዓመታዊ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔውን አካሄደ Read More »

ቡና ባንክ የቪዛ ካርድ አገልግሎት መስጠት ጀመረ 🌐💳

የዲጂታል መዳረሻዎቹን በየጊዜው በማስፋት የደንበኞቹን ፍላጎት በማሟላት ላይ የሚገኘው ቡና ባንክ የአለምአቀፍ ቪዛ ካርድ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ይፋ አድርጓል። ዛሬ ታህሳስ 1 ቀን 2017 ዓ.ም ባንኩ ዋና መስሪያ ቤት በተካሄደ ስነስርዓት ቡና ባንክ የቪዛ ኢንተርናሽናል አባል መሆኑንና የቪዛ ካርድ አገልግሎቶችን መስጠት በይፋ መጀመሩን አብስሯል። ቡና ባንክ የአምስት አመት የዲጂታል ስትራተጂ ቀርጾ ወደስራ ከገባ አንድ አመት እንደሞላውና ይህ አዲስ አገልግሎትም የዚሁ ስትራቴጂ አካል መሆኑ በማስጀመሪያ ስነስርዓቱ ላይ ተገልጿል። ቡና ባንክ በቀረጸው የዲጂታል መሪ ዕቅድ የክፍያ መዳረሻዎችን በመጨመርና ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የክፍያ ሥርዓቶች ጋር በመተባበር ለደንበኞቹ አዳዲስ አማራጮችን በማቅረብ ላይ ይገኛል ተብሏል፡፡ በዚህ መሰረትም ቡና ባንክ ከነዚህ አለምአቀፍ የክፍያ ስርዓት አሳላጮች መካከል ቀዳሚ ከሆነውና ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ባለው ቪዛ ኢንተርናሽናል (Visa International) አባል በመሆን የቪዛ ካርድ አገልግሎት መስጠት መጀመሩም ተገልጿል። የቡና ባንክ ቡና ባንክ ይህን መስተጋብር መጠቀሙ የክፍያ ካርድ ለደንበኞች ማቅረብ እንዲሁም አለምዓቀፍ የክፍየ ካርድ መቀበል አስችሎታል ፡፡ ቡና ባንክ ከሚሰጣቸው የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎቶች በተጨማሪ በነጋዴ መዳረሻዎች (Merchant ) የቪዛ ኢንተርናሽናል ካርዶችን መቀበል መቻሉ ለሀገር ተጨማሪ የውጭ ምንዛሬ ማስገኘት የሚያስችለው መሆኑም ተጠቁሟል። ከዚህ በተጨማሪም የኢትዮጵያ የብሄራዊ ባንክ በቅርቡ ያወጣውን የውጭ ምንዛሬ አፈፃፀም መሰረት በማድረግ ለትምህርት፣ ለጉብኝት እንዲሁም ለህክምና ወደውጭ ሀገር ለሚጓዙ መንገደኞች የውጭ ምንዛሬ በክፍያ ካርድ መስጠት መጀመሩም ተገልጿል። ይህ ሂደት ባንኩ ከዚህ ቀደም በእጅ ይሰጥ የነበረውን የውጭ ምንዛሬ በካርድ በመስጠት ደንበኞቹን የተሻለ ተጠቃሚ ያደርጋቸዋል ነው የተባለው፡፡ ይህም በክፍያ መቀበያ ማሽን፣ በኦንላይን(e-commerce) እንዲሁም በተለያዩ ከንክኪ ነፃ በሆኑ መዳረሻዎች በቀላሉ ክፍያዎችን መፈፀም ያስችለዋል ነው የተባለው። ባንኩ አዲስ ያስተዋወቀው የክፍያ ካርድ የቪዛ እውቅና ያለው በመሆኑ በንክኪም ሆነ ከንክኪ ውጭ የሚሰራ እንደሆነም ተጠቁሟል። ቡና ባንክ ከዚህ በኋላ ለሀገር ውስጥ አገልግሎት የሚያቀርቧቸው የክፍያ ካርዶች የቪዛ መገለጫ ያላቸው በመሆኑ የክፍያ ካርድ ቁጥራቸውን በመጠቀም ከውጭ ሀገር ገንዘብ መቀበልና በቀላሉ ወደ ደንበኛው ሂሳብ ማስገባት ወይም መላክ የሚያስችሉ ናቸው ተብሏል። ከዚህ በተጨማሪም ደንበኞች እነዚህን ካርዶች በመጠቀም የተመረጡ የኦንላይን ግብይቶችንም መፈፀም እንደሚያስችላቸው በስነስርዓቱ ላይ ተነግሯል። ቡና ባንክ ከቪዛ ኢንተርናሽናል ጋር መስተጋብር በመፍጠሩ ለነጋዴዎች አማራጭ የክፍያ ስርዓት ከመዘርጋት በተጨማሪ በባንኩ ቅርንጫፎች ወይም በአቅራቢያ ባስቀመጣቸው የኤ.ቲ.ኤም ማሽኖች አለምአቀፍ የቪዛ ኢንተርናሽናል ካርዶችን መቀበል መቻሉም ተገልጿል ።

ቡና ባንክ የቪዛ ካርድ አገልግሎት መስጠት ጀመረ 🌐💳 Read More »

Bunna Bank SC Joins Visa International as Associate Member

Bunna Bank SC Joins Visa International as Associate Member Addis Ababa, Ethiopia – December 10, 2024 – In a significant advancement for the Ethiopian banking sector, Bunna Bank SC has officially become an Associate Member of Visa International. During a launch ceremony held at Bunna Bank’s headquarter today; this collaboration was hailed as a milestone for the bank, marking a significant advancement in its digital strategy objectives. This strategic partnership will enable Bunna Bank to enhance its international payment solutions and expand access to a global financial network for its customers.The collaboration with Visa International is set to provide numerous benefits, including seamless and secure transactions for customers, who will now have the convenience of using Visa’s extensive network of millions of merchants and financial institutions worldwide. This initiative underscores Bunna Bank’s commitment to delivering top-tier financial services and innovative solutions.To meet evolving customer needs, Bunna Bank has launched a comprehensive digitalization plan aimed at expanding payment options. This includes partnerships with various international payment systems, notably Visa International, which will allow the bank to offer a range of payment cards and accept international transactions. The partnership is expected to contribute to the generation of additional foreign currency for Ethiopia by enabling Visa International acceptance at merchant locations. In line with directives from the National Bank, Bunna Bank has also begun issuing foreign currency payment cards for travelers, facilitating payments for education, tourism, and medical purposes. Customers can now withdraw foreign currency using their cards, enhancing convenience and security by minimizing cash handling. Bunna Bank’s new Visa-certified payment cards support both contact and contactless transactions, making them suitable for domestic and international use. Customers can receive funds from abroad and easily deposit or transfer money using their payment card numbers. Additionally, the bank offers an alternative payment system for merchants, allowing them to accept Visa International cards at branches or nearby ATMs. “We are delighted to become an Associate Member of Visa International,” said Ato Mulugeta Alemayehu, CEO of Bunna Bank SC. at the Bunna -Visa partnership kickoff ceremony held at the Bank’s HQ. “This partnership empowers us to deliver world-class payment solutions and aligns with our vision of establishing Bunna Bank as a leading financial service provider in Ethiopia. Our clients can now leverage the advantages of a globally recognized payment system, renowned for its security, reliability, and convenience.” Ato Yared Endale, Country Director of Visa International, expressed enthusiasm about the partnership, stating, “Today we celebrate a significant milestone in the journey of Bunna Bank as we announce the launch of its Visa cards, marking a new era in digital banking solutions for the Ethiopian market. This launch is more than just the introduction of a new product; it’s a significant step forward towards a more inclusive and digitized financial ecosystem.” The partnership will be rolled out in phases, beginning with the introduction of Visa debit and credit cards, followed by expanded services such as online and mobile banking solutions. This membership allows Bunna Bank to introduce a variety of Visa-branded products, featuring advanced capabilities like contactless payments, 24/7 global customer support, and competitive exchange rates for international transactions. Joining Visa International positions Bunna Bank at the forefront of financial technology adoption, reinforcing its strategy to modernize services and infrastructure in response to the evolving needs of its customers. This development highlights Bunna Bank’s dedication to innovation and excellence in the Ethiopian banking sector. Bunna Bank SC, known for its strong local presence and customer-centric approach, continues to strengthen its market position. The partnership with Visa International is a testament to its ongoing efforts to enhance customer experience and foster growth in both the local and international community. As Bunna Bank SC embarks on this new chapter, it remains committed to providing exceptional banking services and supporting the economic well-being of its clients and the wider community.

Bunna Bank SC Joins Visa International as Associate Member Read More »

ቡና ባንክ አ.ማ የ ISO/IEC 27001፡2022 ሰርተፍኬት አገኘ

ቡና ባንክ አክስዮን ማህበር የኢንፎርሜሽን ደህንነት አስተዳደር ሲስተምስ (አይኤስኤምኤስ) ስታንዳርድ የሆነውን የISO/IEC 27001፡2022 ስታንዳርድ በተሟላ ሁኔታ በማሳካት ሰርተፍኬት ማግኘቱን ይፋ አድርጓል።ይህ በዓለም-አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ያለው ሰርቲፊኬሽን ባንኩ ያሉትን መረጃዎች ለመጠበቅ እና የደንበኞቹን እና የባለድርሻ አካላትን የመረጃ ደህንነት ደረጃውን በጠበቀ አሰራር ደህንነታቸውን ለማረጋገጥ ያለውን የማያወላውል ቁርጠኝነት ያሳያል ተብሏል። የ ISO/IEC 27001፡2022 የምስክር ወረቀት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለመረጃ ደህንነት አስተዳደር መለኪያ ሆኖ የሚያገለግል የተመሰከረለት ሰርቲፊኬት መሆኑ ይታወቃል። ቡና ባንክ አ.ማ ይህንን የደህንነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማሳካት በመቻሉ ከሳይበር አደጋዎች የሚከላከሉ ጠንካራ የደህንነት ቁጥጥሮችን ተግባራዊ ለማድረግ ያለውን አቅምና ፍላጎት ያሳየ መሆኑ ተገልጿል። የቡና ባንክ አ.ማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሙሉጌታ አለማየሁ ሰርቲፊኬቱን ሲቀበሉ እንደተናገሩት “ይህን የምስክር ወረቀት በማግኘታችን በጣም ተደስተናል፤ ይህ ፕሮጀክት የባንክ መረጃዎቻችንን ደህንነት የማስጠበቅ እርምጃዎቻችንን በቀጣይነት በማጎልበት የደንበኞቻችንን እምነት አስጠብቆ ለመቀጠል ያለንን ቁርጠኝነት ያንፀባርቃል፤ ይህም ስኬታማ አፈጻጸም የቡድናችንን ጥረት እና ትጋት የሚያሳይ ነው። የባንክ ቢዝነስ ስራ ውጤት እና የአይቲ ደህንነት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች በመሆናቸው ይህንን ሰርተፊኬት ማግኘታችን ትልቅ ስኬት ነው ” ብለዋል፡፡ ሰርቲፊኬሽን የሰጠው ሰርቲ-ትረስት ድርጅት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ማይክ ካማው በበኩላቸው በፕሮግራሙ ላይ እንደተናገሩት ቡና ባናክ የሚጠበቅበትን ሁሉንም የሴኪዩሪቲ መስፈርቶች መቶ በመቶ ያሟላ የመጀመሪያው ተቋም ነው ያሉ ሲሆን ይህም ባንኩ ለኢንፎርሜሽን ሴኩዩሪቲ ማኔጅመንት ሲስተም የሰጠውን ልዩ ትኩረት የሚያሳይ አስደናቂ ስኬት ነው ብለዋል፡፡ አክለውም ባንኩ የባለራዕዮች ባንክ እንደመሆኑ ራዕዩን በዕውን እየተገበረ መሆኑን በግልጽ መናገር ይቻላል ብለዋል፡፡  ይህ አድካሚ የሰርተፊኬሽን ሂደት በርካታ የባንኩን የደህንነት ቁጥጥር ዘዴዎች ማለትም ተቋማዊ፣ ቴክኒካል፣ የአይቲ መሰረተ-ልማትና አስተዳደራዊ ቁጥጥር እና አሠራሮችን አጠቃላይ ግምገማ ያካተተ ነበር። የኦዲት ስራው የተከናወነው ገለልተኛ በሆነ ሰርቲፊኬሽን ሰጪ ድርጅት ሲሆን በስራውም ገለልተኛና የላቀ ሙያዊ አቅሙን በመጠቀም የባንኩን አሰራር እንዲገመግም ተደርጓል፡፡ በተሳካ ሁኔታ የተከናወነው ሰርቲፊኬሽን የቡና ባንክ አክሲዮን ማህበር የመረጃ ደህንነትን በተመለከተ ያለውን ቀድሞ በማሰብ ተገቢውን የጥንቃቄ እርምጃ የመውሰድ አካሄድ እና ሊከሰቱ የሚችሉ ስጋቶችን አስቀድሞ ለማስወገድ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል። ቡና ባንክ ከኢንፎርሜሽን ደህንነት አስተዳደር ሲስተምስ ጋር ተያይዞ በርካታ የተለያዩ የተሻሻሉ የደህንነት እርምጃዎችን ተግባራዊ አድርጓል። ISO/IEC 27001፡2022 ሰርቲፊኬሽኑን ተከትሎ ባንኩ ከደንበኞች፣ የቢዝነስ አጋሮች እና ከተቆጣጣሪ አካላት ጋር ያለውን ግንኙነት የበለጠ ያጠናክራል ተብሎ ይታሰባል። የእውቅና ማረጋገጫው ባንኩ ሚስጥራዊ መረጃዎችን ለመጠበቅ እና ተያያዥ አደጋዎችን ለመቀነስ ሁሉንም አስፈላጊ የጥንቃቄ እርምጃዎች እየወሰደ መሆኑን ማረጋገጫ የሚሰጥ ነው ተብሏል። ይህም በመሆኑ የባንኩ ደንበኞች መረጃቸው በከፍተኛ ጥንቃቄ እና ደህንነት እንደተያዘ እምነት እንዲኖራቸው ያደርጋል። ቡና ባንክ አክስዮን ማህበር ያስመዘገበው ይህ ስኬት በአገራችን የባንክ ዘርፍ የመረጃ ደህንነትን በማስፈን ደረጃውን ከፍ ያደረገ አሰራር ሲሆን ባንኩን በፋይናንሺያል ሴክተሩ የሳይበር ደህንነት ጥበቃ ረገድ ግንባር ቀደም አድርጎታል ማለት ይቻላል። ባንኩ በመረጃ ደኅንነት ግንባር ቀደም ሆኖ መቀጠሉን በማረጋገጥ በዘመናዊ የደህንነት ቴክኖሎጂዎች እና አሰራሮች ላይ ኢንቨስት ማድረጉን እንደሚቀጥል አሳውቋል።

ቡና ባንክ አ.ማ የ ISO/IEC 27001፡2022 ሰርተፍኬት አገኘ Read More »

Bunna Bank SC Achieves ISO/IEC 27001:2022 Certification

Bunna Bank SC has proudly announced its successful certification with the latest ISO/IEC 27001:2022 standard for Information Security Management Systems (ISMS). This prestigious certification underscores the bank’s unwavering commitment to safeguarding its information assets and ensuring the highest standards of data protection for its customers and stakeholders. The ISO/IEC 27001:2022 certification is recognized globally as the benchmark for information security management. By achieving this certification, Bunna Bank SC has demonstrated its capability to implement robust security controls that protect against evolving cyber threats.“We are thrilled to receive this certification,” said Mulugeta Alemayehu, CEO of Bunna Bank SC. “It reflects our dedication to maintaining the trust and confidence of our customers by continuously enhancing our security measures. This achievement is a testament to the hard work and dedication of our entire team. It’s a great achievement as business performance and IT security are two sides of a coin.” Mike Kamau, Managing Director of the certifying organization CERTI-TRUST, stated during the handover ceremony, “Bunna Bank is our first customer organization to tick all the boxes and score 100 percent, which is a remarkable achievement demonstrating the maturity of the bank’s security management system. As a bank of the visionaries, it is clear that the bank is truly living its vision.”The rigorous certification process involved a comprehensive assessment of the bank’s organizational, technical, physical, and administrative controls. The audit was conducted by an independent certification body, ensuring the highest level of impartiality and expertise. The successful certification highlights Bunna Bank SC’s proactive approach to information security and its commitment to staying ahead of potential threats. Bunna Bank SC has implemented a comprehensive suite of enhanced security measures as part of its Information Security Management System (ISMS). Achieving the ISO/IEC 27001:2022 certification demonstrates the Bank’s commitment to safeguarding sensitive information and mitigating risks. This milestone strengthens the Bank’s relationships with customers, partners, and regulators by providing assurance that robust security practices are in place. Customers can trust that their data is managed with the highest standards of care and security. Bunna Bank SC’s achievement underscores its dedication to information security and positions the Bank as a proactive player in Information security within the financial sector. This certification highlights the Bank’s commitment to maintaining robust security measures and adopting best practices. Moving forward, the Bank plans to continue investing in advanced security technologies and processes to uphold its strong stance on protecting sensitive information.

Bunna Bank SC Achieves ISO/IEC 27001:2022 Certification Read More »

የኢ.አር.ፒ እና አቦል ዲጂታል ባንኪንግ ውጤታማ ትግበራን ተከትሎ ዕውቅናና ሽልማት ተሰጠ

በፕሮጀክቶቹ ከ 5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ማዳን ተችሏል! ቡና ባንክ ኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ ፕሮጀክትና አቦል ዲጂታል ባንኪንግ መተግበሪያን ሙሉ በሙሉ ወደስራ ማስገባቱን ተከትሎ እነዚህ ሁለት ፕሮጀክቶች በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቁ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የባንኩ ሰራተኞች ዕውቅናና ሽልማት ሰጠ፡፡ ሐምሌ 29 ቀን 2016 ዓ.ም. የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ አለማየሁ እና የኤክስኪዩቲቭ ማኔጅመንት አባላት በተገኙበት በተካሄደው የሽልማት ፕሮግራም ለ70 ባለሙያዎች ምስጋናና ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡ የቡና ባንክ አቦል ዲጂታል ባንኪንግ መተግበሪያ በባንኩ ቺፍ ኢንፎርሜሽን ዘርፍ በተቋቋመው ቡድን በባንኩ ባለሙያዎች የራስ አቅም እንደአዲስ የተዘጋጀ መተግበሪያ ሲሆን አሁን ላይ በስኬታማነት አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተነግሯል፡፡ መተግበሪያው በራስ አቅም መልማቱ የባንኩ ሰራተኞች ልምድ እንዲያካብቱ ከማድረጉም በላይ ባንኩ 1.2 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ከወጪ እንዲያድን ማድረጉ ተነግሯል፡፡ ይህንን መተግበሪያም ሆነ የኢአርፒ ስርዓትን ወደትግበራ ለማስገባት በነበረው ጥረት የባንኩ ኤክስኪዩቲቭ ማኔጅመንት የቅርብ ክትትልና ዕገዛ በማድረግ እንዲሁም ተገቢውን አቅጣጫ በወቅቱ በመስጠት የማይተካ ሚና ተጫውቷል ተብሏል። አሁን የተተገበረው የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ ሲይስተም በዉጭ ምንዛሬ ሊያሶጣ የሚችለዉን ከ 4 ሚሊዮን ዶላር  በላይ ገንዘብ ማዳን ተችሏል። ይህ የዕውቅናና ምስጋና ፕሮግራም መዘጋጀቱ ለፕሮጀክቱ ስኬታማነት አስተዋጽኦ ያበረከቱትን ከማመስገን ባለፈ ሌሎች የባንኩ ሰራተኞችና ባለሙያዎችን ለበለጠ ስራ ለማነሳሳትና ለማትጋት የሚረዳ መሆኑም ተገልጿል፡፡ በተያያዘም ባንኩ ኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግን በተቋም ደረጃ በውጤታማት የተተገበረ ሲሆን ይህንን ፕሮጀክት ስኬታማ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱና ክትትል ሲያደርጉ ለነበሩ የሚመለከታቸው የባንኩ የስራ ክፍሎችና ባለሙያዎች ዕውቅና ተሰጥቷል፡፡ በዕለቱ የዕውቅና ፕሮግራም ላይ የተገኙት የባንንኩ ዋና ሰራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ አለማየሁ ባስተላለፉት መልዕክት የሁለቱ ፕሮጀክቶች በዚህ መልክ መጠናቀቅ ለወደፊቱ መሰል የባንካችን የሥራ ከፍሎችና ባለሙያዎች አርዓያ ከመሆኑ በተጨማሪ  ውጤታማ ፕሮጀክቶችን ዕውን ለማድረግ የሚያነሳሳ ምሳሌ የሆነ ስራ በመሆኑ ሊበረታታ የሚገባው ተግባር ነው ብልዋል። በፕሮጀክቶቹ ትግበራ ላይ ከተካፈሉ ባለሙያዎችም ምስጋና አቅርበዋል። ፡ ዋና ስራ አስፈጻሚው የሲስተሞቹን ውጤታማ ዘላቂነት ለማረጋገጥ የሚመለከታቸው የባንኩ የሥራ ክፍሎች ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተገቢውን ክትትል ማድረግ እንደሚገባቸውም አጽንኦት ሰጥተው አሳስበዋል፡፡

የኢ.አር.ፒ እና አቦል ዲጂታል ባንኪንግ ውጤታማ ትግበራን ተከትሎ ዕውቅናና ሽልማት ተሰጠ Read More »

This will close in 0 seconds

You cannot copy content of this page