የኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ባለስልጣን በቁጥር 1047/2017 ባወጣው መመሪያ መሰረት የባለአክሲዮኖች የአክሲዮን ባለቤትነት ምስክር ወረቀት ወደ ኤሌክትሮኒክ የባለቤትነት ማረጋገጫ መቀየር እና የባለአክሲዮኖች መረጃ ወደ ማዕከላዊ የሠነደ ሙዓለ ንዋዮች ግምጃ ቤት መላክ እንዳለበት ተደንግጓል፡፡ በመሆኑም የወጣውን አስገዳጅ መመሪያ ለመፈጸም እንዲቻል የቡና ባንክ ባለአክሲዮኖች (ግለሰቦች ) የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ካርድ ኮፒ፣ የፋይዳ ካርድ ቁጥር (FAN)፣ የትውልድ ቀን(እ.ኤ.አ) ፣ አድራሻ (ክልል፣ ክ/ከተማ፣ ወረዳ/ቀበሌ፣ የቤት ቁጥር፣ ተንቀሳቃሽ ስልክ ቁጥር፣ ኢ-ሜል) ፣የታክስ መክፈያ መለያ ቁጥር (TIN)፤ ባለአክሲዮኑ ሕጋዊ ሰውነት ያለው ድርጅት ከሆነ የምዝገባ ቁጥር ፣ የታክስ መክፈያ መለያ ቁጥር (TIN) ፣ ሙሉ አድራሻ እና የወኪሉ ሰው ሙሉ መረጃ በዋናው መ/ቤት 6ኛ ፎቅ አክሲዮን አስተዳደር ክፍል ወይም በአቅራቢያዎ በሚገኝ የቡና ባንክ ቅርንጫፍ እስከ ሰኔ 10 ቀን 2018 ዓ.ም. በመቅረብ እንዲሰጡ በአክብሮት እንጠይቃለን፡፡
ቡና ባንክ
የባለራዕዮች ባንክ