Bunna Bank

ቡና ባንክ በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር አካሄደ፡፡

ቡና ባንክ ከአዲስ አበባ ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር፣ በኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር ማዕቀፍ ውስጥ “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላና የአካባቢ ጥበቃ ተግባራትን በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 በጎነት የመኖሪያ መንደር አካሄደ።

ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከልና የአረንጓዴ ልማትን ለማስፋፋት በየዓመቱ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብሮችን ታከናውናለች። በዚህ አገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር ማዕቀፍ ውስጥ፣ ቡና ባንክ በበኩሉ ለምግብነት የሚውሉ የቦካዶ እና የዘይቱና ችግኞችን በመትከል የከተማዋን ውበት ለማሳደግ፣ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቋቋምና ዘላቂ ልማትን ለማስፈን የሚደረገውን አገር አቀፍ ጥረት የሚያግዝ ተግባር አከናውኗል።

ይህ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር የተፈጥሮ- አካባቢን ውበት በመጠበቅ፣ ለነዋሪዎች ጤና ተስማሚ የሆነ አካባቢ ለመፍጠር እየተደረገ ያለውን ጥረት የሚያግዝ ነው ሲል ባንኩ ገልጿል።  ባንኩ በዚህ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር መሳተፉ፣ በፋይናንስ ዘርፍ ካለው ቀዳሚ ሚና ባሻገር፣ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ረገድ ለማህበረሰብ ልማትና ለአካባቢ ጥበቃ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳየ ተግባር ነው።

ስለሆነም የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር የኢትዮጵያን ዘላቂ ልማት ለማሳካት ወሳኝ መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት ቡና ባንክ ይህን ተግባር በመደገፍ ለአካባቢ ጥበቃና ለማህበረሰብ ልማት ያለውን ኃላፊነት እየተወጣ ይገኛል። ባንኩ የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ልማት ራዕይ እውን ለማድረግ በሚደረገው አገር-አቀፍ ጥረት ውስጥ በተመሳሳይ መርሀ-ግብሮች ተሳትፎውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል። 

ይህ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር ለማህበረሰባችን ኑሮ ተስማሚ አካባቢን ለመፍጠርና የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የምናደርገው የጋራ ጥረት መገለጫ ነው ያለው ባንኩ በቀጣይም የልደታ ክፍለ ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤትን ጨምሮ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ሌሎች የችግኝ ተከላና የአካባቢ ጥበቃ መርሀ-ግብሮች ላይ ለመሳተፍ ዝግጁነቱን ገልጿል።

ነሃሴ 08 ቀን 2017 ዓ.ም.

በቡና ባንክ ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽንና ፕሮሞሽን

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This will close in 0 seconds

You cannot copy content of this page