Bunna Bank

ቡና ባንክ የ5 ቢሊዮን የተከፈለ ካፒታል መጠኑን ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ አስቀድሞ አሳካ

ቡና ባንክ አ.ማ. በብሔራዊ ባንክ የተሻሻለውን የ5 ቢሊዮን አነስተኛ የተከፈለ ካፒታል መጠን በማሳከት ከከኢንዱስትሪ መሪዎቹ ተርታ መሰለፉ ተገለጸ።

እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 12 ቀን 2021 በወጣው መመሪያ ቁጥር SBB /78/2021 መሰረት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰሩ ባንኮች የተከፈለ ካፒታላቸውን እ.ኤ.አ. እስከ ሰኔ 30 ቀን 2026 በትንሹ ወደ 5 ቢሊዮን ብር እንዲያሳድጉ መወሰኑ ይታወሳል።
መመሪያው በተላለፈበት ወቅት ከተቀመጠው ገደብ በታች የተከፈለ ካፒታል የነበራቸው ነባር ባንኮች መመርያው ሥራ ላይ ከዋለ በኋላ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ የካፒታል ማሳደጊያን የተመለከተ የድርጊት መርሃ ግብር ለብሔራዊ ባንክ እንዲያቀርቡ ተደርጓል።

ቡና ባንክ አ.ማ ግን ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ ቀደም ብሎ የተቀመጠውን መስፈርት በማሳካት ከመሪዎቹ ተርታ ተሰልፏል። ይህ ስኬት ባንኩ ለጠንካራ የፋይናንሺያል አፈጻጸም ጤናማነት አፅንዖት መስጠቱን ብቻ ሳይሆን ለተቆጣጣሪ አካላት መመሪያዎች ተገዢነት ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል።

ሊሟላ የሚገባው የተከፈለ ካፒታል መጠን ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ ቀደም ብሎ መሟላቱ በቡና ባንክ አ.ማ የዕድገት ጉዞ ላይ እንደ አንድ ትልቅ የዕድገት ምዕራፍ የሚታይ ሲሆን በኢትዮጵያ የባንክ ኢንደስትሪ የሚኖረውን ቁልፍ ሚና ያጠናክራል ተብሎ ይታሰባል።

ይህም ስኬት የባለሃብቶችንና የደንበኞችን እምነት የሚያጠናክር ሲሆን የባንኩን አቅም በማጎልበት በዘርፉ የታቀዱ የኢኮኖሚ ልማት ውጥኖችን ለማሳካትም ደጋፊ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

Bunna Bank Surpasses Capital Requirement Milestone Ahead of Schedule
In a remarkable achievement for the Ethiopian banking sector, Bunna Bank S.C. has successfully met the revised paid-up capital requirements set by the National Bank of Ethiopia. In accordance with Directive No. SBB/78/2021, issued on April 12, 2021, banks operating in Ethiopia were mandated to raise their paid-up capital to a minimum of Birr 5 billion by June 30, 2026.
Existing banks that fell short of this threshold were required to submit an action plan for capital increase to the National Bank within 30 days after the directive’s effective date. Bunna Bank S.C., however, has emerged as one of the trailblazer by achieving the minimum requirement well ahead of the stipulated deadline. This accomplishment not only underscores the bank’s robust financial health but also reflects its proactive approach to regulatory compliance.
The early fulfillment of the capital requirement marks a significant milestone in Bunna Bank S.C.’s growth trajectory and solidifies its position as a key player in Ethiopia’s banking landscape. This achievement is expected to bolster investor confidence and enhance the bank’s capacity to support economic development initiatives across the nation.

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This will close in 0 seconds

error: