Bunna Bank

ቡና ባንክ የISO/IEC 27001:2022 ዓለም አቀፍ የመረጃ ደህንነት ኦዲትን በስኬት ማጠናቀቁን አስታወቀ

በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ በዘመናዊ አሰራሩ የሚታወቀው ቡና ባንክ፣ የISO/IEC 27001:2022 የመረጃ ደህንነት አስተዳደር ሥርዓት (ISMS) የክትትል ኦዲትን በስኬት ማጠናቀቁን በይፋ አስታውቋል። ይህ ከፍተኛ ዓለም አቀፍ እውቅና የተገኘው ባንኩ የመጀመሪያውን የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት በተቀበለ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ሲሆን፣ ይህም ተቋሙ ለላቀ የዲጂታል ስታንዳርድ እና ለመረጃ ጥራት የሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት የሚያሳይ ትልቅ ስኬት ተደርጎ ተወስዷል። የተካሄደው የክትትል ኦዲትም የባንኩ የመረጃ ደህንነት መዋቅር አሁንም ድረስ እጅግ አስተማማኝ፣ ወቅታዊ እና አዳዲስ የዓለም አቀፍ መስፈርቶችን በሚገባ የሚያሟላ መሆኑን ዳግም ያረጋገጠበት ሆኗል።

በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም የሳይበር ጥቃቶች ስልታቸውን እየቀያየሩና ይበልጥ እየረቀቁ በመምጣታቸው፣ ቡና ባንክ ለዚህ ጉዳይ የሰጠው ትኩረት ተራ የቁጥጥር ስራን ማለፍ ብቻ ሳይሆን ደንበኞቹን ካልተጠበቀ አደጋ ለመታደግ ያለውን ዝግጁነት የሚያንፀባርቅ ነው። ባንኩ ይህንን የላቀ ደረጃ ማሟላቱ የደንበኞቹን የግልና የፋይናንስ መረጃዎች በከፍተኛ ጥንቃቄና በሚስጥር ለመጠበቅ ያለውን ጽኑ አቋም የሚያሳይ ሲሆን፣ ከዚህም በተጨማሪ ማንኛውንም አይነት የደህንነት ስጋቶች አስቀድሞ የመለየት፣ የመከላከል እና ድንገተኛ አደጋዎች ቢከሰቱም እንኳ የባንኩን መደበኛ ስራ ሳይስተጓጎል በፍጥነት የማስቀጠል አቅሙን (Operational Resilience) በሚገባ አሳድጓል። ይህ ስኬት ባንኩ በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ በፋይናንስ ተቋማት ላይ የሚጣሉ ጥብቅ የደህንነት መመሪያዎችንና የሕግ ማዕቀፎችን በሚገባ ማክበሩን ለባለድርሻ አካላት ማረጋገጫ የሰጠበት አጋጣሚ ሆኖ አልፏል።

ለዚህ አመርቂ ውጤት መገኘት የባንኩ አመራሮችና መላው ሰራተኞች ላሳዩት ከፍተኛ ትጋትና ቅንጅት የባንኩ ከፍተኛ አመራር ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ይህ ስኬት የጋራ ጥረት ውጤት መሆኑን በመጥቀስ፣ የተገኘው የብቃት ማረጋገጫ ከደንበኞች፣ ከአጋር ድርጅቶችና ከመንግስት ተቆጣጣሪ አካላት ጋር ያለውን የቆየ እምነትና ታማኝነት ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ገልጸዋል። በመሆኑም ቡና ባንክ የISO/IEC 27001:2022 ዓለም አቀፍ ማዕቀፍን እንደ መርህ በመጠቀም፣ የመረጃ ደህንነትን ከባንኩ የዕለት ተዕለት ተግባራትና ከእያንዳንዱ ዲጂታል ግብይት ጋር በማስተሳሰር፣ በቀጣይም በቴክኖሎጂ የታገዘና አስተማማኝነቱ የተረጋገጠ የባንክ አገልግሎት ለህዝቡ ለማቅረብ ቁርጠኝነቱን በድጋሚ አረጋግጧል።

Bunna Bank Reaffirms Security Excellence with Successful ISO/IEC 27001:2022 Audit

Bunna Bank is proud to announce that it has successfully passed the ISO/IEC 27001:2022 Surveillance Audit, marking a significant milestone in its journey toward digital excellence and data integrity.
Coming just one year after the bank’s initial certification, this successful audit confirms that Bunna Bank’s Information Security Management System (ISMS) remains robust, up-to-date, and fully compliant with the latest international standards.

Strengthening the Trust Foundation
In an era where cyber threats are increasingly sophisticated, this achievement underscores Bunna Bank’s proactive approach to safeguarding its information assets. The successful surveillance audit is not just a regulatory checkmark; it is a testament to the bank’s commitment to:
• Protecting Customer Data: Ensuring the highest levels of confidentiality and integrity for client information.
• Operational Resilience: Strengthening the bank’s ability to detect, respond to, and recover from security incidents.
• Regulatory Compliance: Meeting and exceeding both local and international benchmarks for financial data security.

A Collaborative Success
The bank’s leadership extended its gratitude to the entire staff for their role in this achievement.
“This milestone reflects our continued commitment to maintaining a world-class ISMS and strengthening the trust we share with our customers, partners, and regulators. A sincere thank you to our management and teams for their dedication, collaboration, and ongoing efforts to sustain these international standards.”
By adhering to the ISO/IEC 27001:2022 framework, Bunna Bank ensures a culture of continual improvement, ensuring that security is woven into the fabric of every digital transaction and internal process.

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This will close in 0 seconds

You cannot copy content of this page