Bunna Bank

Uncategorized

ቡና ባንክ ከስራና ክህሎት ሚኒስትር ጋር ተወያየ

በቡና ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ የተመራ ልዑክ ከስራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ጋር ተወያየ በቡና ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ አለማየሁ የተመራ የባንኩ ከፍተኛ የስራ አመራር ልዑክ ከስራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ጋር በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርጓል፡፡መስከረም 12 ቀን 2018 ዓ.ም በክብርት ሚኒስትሯ ቢሮ በተካሄደው በዚሁ ውይይት ለወጣቶች የስራ ፈጠራ አቅም ግንባታ እንዲሁም የፋይናንስ አካታችነትን ማስፋት በሚቻልባቸው መንገዶችና በቴክኖሎጂ ትብብርና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል፡፡ የውይይቱን መጠናቀቅ ተከትሎ ክብርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል በይፋዊ የፌስቡክ ገጻቸው ባሰራጩት መረጃ “ከቡና ባንክ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በቅንጅት መስራት በምንችልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውጤታማ ውይይት አካሂደናል፡፡ በውይይቱ በሥራ ዕድል ፈጠራ ስነ-ምህዳሩ ላይ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተደረጉ ያሉ የተናጠል ጥረቶችን ተመልክተናል፡፡ በቀጣይም በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት መስኩን ጨምሮ በጋራ በሚለዩ ስትራቴጂያዊ የትብብር መስኮች ተቀናጅቶ በመስራት ውጤቱን ለማላቅ ተግባብተናል” ብለዋል፡፡ “የቡና ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ክቡር አቶ ሙሉጌታ አለማየሁ እና የሥራ ባልደረቦቻቸው ከሚኒስቴሩ ጋር ተቀናጅቶ በመስራት የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ላሳዩት ተነሳሽነትም ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ” ብለዋል፡፡ በውይይቱ ላይ ለባንካችን ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች የሚኒስቴሩን በሰውሰራሽ አስተውህሎት የበለጸገ የሰራተኛ ገበያ መረጃ ስርዓት (Labor market information system) በተመለከተ ክብርት ሚኒስትሯ ሰፋ ያለ ገለጻ አድርገዋል፡፡ የባንካችን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ አለማየሁ በገለጻው ማጠቃለያ ላይ ባደረጉት ንግግር ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዘርፉን በማዘመንና በቴክኖሎጂ እንዲደገፍ በማድረግ በኩል ያከናወናቸውን ተግባራት አድንቀዋል፡፡ በተጨማሪም ክብርት ሚኒስትሯ በቢሯቸው ለርሳቸውና ለስራ አመራር ቡድኑ ላደረጉት ደማቅ አቀባበል አመስግነው በውይይቱ ወቅት ለቀረቡት ገንቢ ሃሳቦችም አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡ በውይይቱ ላይ የቡና ባንክ ፕሮዳክትና ሰርቪስ ኢኖቬሽን ተጠባባቂ ቺፍ ኦፊሰር አቶ ሰዋለ ቢተው፣ የባንኩ ከወለድ ነጻ የባንክ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መሃመድ ናስር እና የባንኩ ኢንተርናሽናል ባንኪንግ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጠና ሀይለማርያም ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ቡና ባንክ ከስራና ክህሎት ሚኒስትር ጋር ተወያየ Read More »

ዶ/ር እዮብ ተካልኝ – የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ

ቡና ባንክ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ሆነው በመሾማቸው የተሰማውን ከልብ የመነጨ ደስታ ይገልፃል ። በፋይናንስና ኢኮኖሚ ዘርፎች የደረጀ ዕውቀትና የካበተ ልምድ ያላቸው ዶ/ር እዮብ ተካልኝ ወደዚህ ኃላፊነት መምጣታቸው ለሃገራችን የባንክና ፋይናንስ ዘርፍ ዕድገት የላቀ አበርክቶ ሊሆን እንደሚችል ባንካችን በፅኑ ያምናል። ለቀጣዩ የስራ ዘመናቸውም ስኬትን ይመኛል። BunnaBank #Finance #Banking #Economy #NBE #Governor #Visionaries

ዶ/ር እዮብ ተካልኝ – የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ Read More »

ኑ ቡና ደርሷል! ቡና ባንክ በአዲስ አቀራረብ ለደንበኞቹ አገልግሎት መስጠት ጀመረ!

ቡና ባንክ ደንበኛ ተኮር የሆኑ አሰራሮችን ወደ ዘርፉ በማምጣት እና አገልግሎቱን በማዘመን በደንበኞቹ ዘንድ ተመራጭ ባንክ ለመሆን እየሰራ ይገኛል፡፡ዛሬ መስከረም 05፣2018 ዓ.ም ቡና ባንክ ፣ ቡና ‘ፍሌቨር ‘ ቅርንጫፍ ፥ በቦሌ ሩዋንዳ ዋናው መስሪያ ቤት በይፋ በመክፈት ስራ አስጀምሯል፡፡ አገልግሎቱ ዘመናዊ እና የዲጅታል አገልግሎት መስጪያ መሳሪያዎችን በመጠቀም ለደንበኞች ቀላል፣ እና ፈጣን የባንክ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ነው፡፡ ይህ የአሰራር ማሻሻያ የደንበኞቻችንን የባንክ አገልግሎት እርካታ ለማሳደግ የተዘረጋ እና ባንካችን በዘርፉ ያለውን ተወዳዳሪነት ከፍ ለማድረግ ታቅዶ ወደ ተግባር የተቀየረ የአሰራር ስርዓት ነው፡፡ በቡና ‘ፍሌቨር’ ቅርናጫፍ ፣ የባንኩ ደንበኞች የፋይናንስ ምክረ ሃሳብ ለማግኘት እና ውይይት ለማከናውን የሚያስችላቸው ምቹ ሁኔታንም አመቻችቷል። ቡና ባንክ ከዚህ ጋር በተያያዘ በስድስት ማእከላት የአይ ቲ ኤም (ITM) አገልግሎት መስጥት መጀመሩን ይፋ አድርጓል፡፡ ማእከላቱ በቦሌ መድሃኒዓለም- ገልፍ አዚዝ ህንጻ፣ በኦሎምፒያ – ኦሜዳድ ሕንፃ ፣ላጋር- ኢትዮጵያ መድሕን ድርጅት፣ አራት ኪሎ ስላሴ – ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ሕንጻ፣ ብስራተ ገብርዔል- አፍሪካ ኢንሹራስ ሕንጻ እና በባንካችን ዋናው መስሪያቤት ቦሌ ሩዋንዳ ተመርቀው ስራ ጀምረዋል፡፡ ኑ ቡና ጠጡ!ቡና ባንክ- የባለራዕዮች ባንክ! Bunna Bank Brews Up a New Banking Experience Bunna Bank S.C. has today announced the launch of its innovative “Bunna Flavor” branch model, a groundbreaking concept that fuses the traditional hospitality of Ethiopian coffee culture with the seamless efficiency of digital banking. The new branch is a testament to the bank’s commitment to being both a financial pioneer and a community-centric institution. The “Bunna Flavor” branch model reimagines the banking experience by creating an environment where a simple transaction can become a personal connection. Instead of cold counters and long queues, the branch offers a welcoming, communal vibe reminiscent of a traditional coffee ceremony, or “bunna.” This approach aims to make banking feel more accessible and comfortable, building trust and rapport with customers. At the heart of this new concept is a suite of advanced, hassle-free paperless digital banking services that streamline everything from deposits to transfers using ITM, ATM and other digital banking fixtures. This modern technology is complemented by a team of dedicated experts. The branch features a financial advisor to provide personalized investment guidance for individual clients and a private corporate consultation room for businesses seeking strategic financial solutions. “Customer centricity is at the core of our banking business; and we believe banking should be a relationship, not just a transaction,” said Ato Lewutie Tirusew, Chief Finance and Corporate Service Officer of the Bank. “The ‘Bunna Flavor Branch’ embodies this philosophy. It’s a place where you can grab a cup of coffee and have a meaningful conversation about your financial future, all while enjoying the speed and convenience of the latest technology. It’s the perfect blend of tradition and innovation.”The unveiling of the “Bunna Flavor Branch model” marks a significant milestone in Bunna Bank’s journey to be among the leaders of the digital transformation of Ethiopia’s financial sector, proving that modernization and cultural heritage can go hand-in-hand. Furthermore, the bank disclosed that it aims to expand this model in an extensive manner to other branches following customers’ feedback and reaction.

ኑ ቡና ደርሷል! ቡና ባንክ በአዲስ አቀራረብ ለደንበኞቹ አገልግሎት መስጠት ጀመረ! Read More »

A New Year, A Shared Vision: Building the Future Together

Message from the CEO   – 2018 Ethiopian New Year As we welcome the Ethiopian New Year 2018 E.C., Bunna Bank extends its heartfelt wishes for peace, prosperity, and progress to all our customers, partners, and other stakeholders. This moment is more than a celebration of a new beginning—it is a reaffirmation of our enduring commitment to those who walk this journey with us. The past year marked a period of meaningful transformation. With your trust and collaboration, Bunna Bank reinforced its foundation, modernized its services, and broadened its reach. Together, we achieved significant milestones—introducing advanced digital platforms that make banking more accessible, launching inclusive financial products tailored to diverse needs, and investing in the growth of our people. Each step forward reflects our shared pursuit of excellence and our belief that progress is most powerful when it is shared. As we enter this new year, we do so with clarity and conviction. Ethiopia’s financial landscape is evolving rapidly, shaped by global competition, technological innovation, and bold reforms such as the launch of the national capital market. Bunna Bank is prepared—not only with resilient systems and forward-looking strategies, but with a deep understanding of the communities we serve and a steadfast commitment to inclusive growth. Our focus for 2018 E.C. is to strengthen relationships, deliver tailored financial solutions, and expand access to banking services across all segments of society. We are investing in scalable infrastructure, enhancing our risk management capabilities, and fostering a culture of responsiveness and innovation. These efforts are designed not only to meet today’s needs, but to anticipate tomorrow’s opportunities. At Bunna Bank, we see every relationship not as a transaction, but as a partnership built on trust, purpose, and shared ambition. In the year ahead, we will continue to listen, adapt, and grow—together. Our promise is simple: to be your trusted financial ally, a catalyst for opportunity, and a committed partner in your success. Thank you for your continued confidence in Bunna Bank. The future is bright—and we are honored to build it with you. Mulugeta Alemayehu Chief Executive Officer Bunna Bank

A New Year, A Shared Vision: Building the Future Together Read More »

መልካም አዲስ ዓመት!

ቡና ባንክ ለመላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ለ2018 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን! እያለ መጪው ዓመት በሀገራችን የሰላም፣ የፍቅርና የስኬት ዘመን እንዲሆንልን ከልብ ይመኛል። የአቦል ዲጂታል ባንኪንግ አማራጮችን በመጠቀም በዓሉን በደስታ ያሳልፉ። ቡና ባንክ – የባለራዕዮች ባንክ!

መልካም አዲስ ዓመት! Read More »

ያለምንም ማስያዣ እስከመቶ ሺ ብር ልናበድርዎ ነው!

ማለዳ፣ መነሻ፣ ራዕይ እና ንጋት ባንካችን ለናንተ ለክቡራን ደንበኞቹ ካዘጋጃቸው የዲጂታል ብድር አይነቶች ውስጥ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ እነዚህ የብድር አይነቶች መደበኛ እና ኢመደበኛ ንግድ ላይ የተሰማሩ ማንኛውም የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ያደርጋሉ፡፡ ደንበኞች የሚጠበቅባቸውን መረጃዎች ብቻ አሟልተው ሲመጡ ወዲያውኑ እስከ 100 ሺ ብር ብድር ከባንካችን ማግኘት ይችላሉ ፡፡አሁኑኑ በአቅራቢያዎት ወደሚገኝ የቡና ባንክ ቅርንጫፍ ይሂዱ፤ የአገልግሎታችን የተሟላ ዝርዝር መረጃ በማግኘት ተጠቃሚ ይሁኑ!ለበለጠ መረጃ ወደ ጥሪ ማዕከላችን 8501 ይደዉሉ ! አቦል ላይ ይድረሱ! ቡና ባንክ- የባለራዕዮች ባንክ

ያለምንም ማስያዣ እስከመቶ ሺ ብር ልናበድርዎ ነው! Read More »

ቡና ባንክ በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር አካሄደ፡፡

ቡና ባንክ ከአዲስ አበባ ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር፣ በኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር ማዕቀፍ ውስጥ “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላና የአካባቢ ጥበቃ ተግባራትን በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 በጎነት የመኖሪያ መንደር አካሄደ። ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከልና የአረንጓዴ ልማትን ለማስፋፋት በየዓመቱ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብሮችን ታከናውናለች። በዚህ አገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር ማዕቀፍ ውስጥ፣ ቡና ባንክ በበኩሉ ለምግብነት የሚውሉ የቦካዶ እና የዘይቱና ችግኞችን በመትከል የከተማዋን ውበት ለማሳደግ፣ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቋቋምና ዘላቂ ልማትን ለማስፈን የሚደረገውን አገር አቀፍ ጥረት የሚያግዝ ተግባር አከናውኗል። ይህ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር የተፈጥሮ- አካባቢን ውበት በመጠበቅ፣ ለነዋሪዎች ጤና ተስማሚ የሆነ አካባቢ ለመፍጠር እየተደረገ ያለውን ጥረት የሚያግዝ ነው ሲል ባንኩ ገልጿል።  ባንኩ በዚህ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር መሳተፉ፣ በፋይናንስ ዘርፍ ካለው ቀዳሚ ሚና ባሻገር፣ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ረገድ ለማህበረሰብ ልማትና ለአካባቢ ጥበቃ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳየ ተግባር ነው። ስለሆነም የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር የኢትዮጵያን ዘላቂ ልማት ለማሳካት ወሳኝ መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት ቡና ባንክ ይህን ተግባር በመደገፍ ለአካባቢ ጥበቃና ለማህበረሰብ ልማት ያለውን ኃላፊነት እየተወጣ ይገኛል። ባንኩ የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ልማት ራዕይ እውን ለማድረግ በሚደረገው አገር-አቀፍ ጥረት ውስጥ በተመሳሳይ መርሀ-ግብሮች ተሳትፎውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል።  ይህ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር ለማህበረሰባችን ኑሮ ተስማሚ አካባቢን ለመፍጠርና የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የምናደርገው የጋራ ጥረት መገለጫ ነው ያለው ባንኩ በቀጣይም የልደታ ክፍለ ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤትን ጨምሮ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ሌሎች የችግኝ ተከላና የአካባቢ ጥበቃ መርሀ-ግብሮች ላይ ለመሳተፍ ዝግጁነቱን ገልጿል። ነሃሴ 08 ቀን 2017 ዓ.ም. በቡና ባንክ ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽንና ፕሮሞሽን

ቡና ባንክ በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር አካሄደ፡፡ Read More »

ጋዜጣዊ መግለጫ |Press release

ቡና ባንክ በአቦል ሞባይል ባንኪንግ ዲጂታል የነዳጅ ክፍያ አገልግሎት መስጠት ጀመረ ቡና ባንክ በኢትዮጵያ የፋይናንስ እና ቴክኖሎጂ እድገት ጉልህ እርምጃ ያለውን አዲስ የዲጂታል ነዳጅ ክፍያ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ። ከትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የተቀረጸው አገልግሎቱ ከብሔራዊ የነዳጅ ስርጭት መከታተያ ስርዓት ጋር በመቀናጀት በአገር አቀፍ ደረጃ የነዳጅ አቅርቦት ሰንሰለትን ግልፅነት እና ቅልጥፍና ለማሻሻል የሚያስችል ዘመናዊ የክፍያ አማራጭ ነው ። ይህ ኢኒሼቲቭ በየጊዜው ተለዋዋጭና ፈጣን ለሆነው የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፍላጎት ምላሽ በመስጠት ረገድ ለደንበኞች አስተማማኝ እና ፈጣን የነዳጅ ክፍያ አማራጭን ይዞ የቀረበ አገልግሎት ነው፤ ይህም አገልግሎት ጥሬ ገንዘብ ከመያዝ ጋር የተያያዙ ስጋቶች፣ ግልጽ ያልሆነ ግብይት እና በነዳጅ ማደያዎች ውስጥ የሚስተዋሉ ረጃጅም ወረፋዎችን የመሳሰሉ ተግዳሮቶችን ለመፍታት እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን የሚያግዝ ነው። ስለሆነም ይህ የዲጂታል ክፍያ አገልግሎት መጀመሩ ቡና ባንክ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የባንክ አገልግሎት ከባቢያዊ ሁኔታን ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል። ደንበኞች ቡና ባንክን ተጠቅመዉ የነዳጅ ግዢን መፈጸም የሚችሉት፤ ከነዳጅ ማደያዉ *820# በመጠቀም ስልካቸዉ ላይ በሚደርሳቸዉ የማረጋገጫ መልእክት፣ አቦል የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ ዉስጥ በመግባት QR ኮድን ተጠቅሞ ስካን በማድረግ ወይም በነዳጅ ማደያው የቀረበውን የማጣቀሻ ቁጥር (Reference Number system) በመጠቀም ነው። ይህ ባለብዙ አማራጭ ዲጂታል ፕላትፎርም በማንኛውም አይነት ሞባይል ስልክ እንዲሁም በኢንተርኔት ወይንም ያለኢንተርኔት በመላው ኢትዮጵያ ለሚገኙ ሁሉም ደንበኞች ሰፊና ተደራሽ አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል። አገልግሎቱ የተሻሻለ የክፍያ አማራጭን በማቅረብ የአሽከርካሪዎችን ፍላጎት ያሟላ ሲሆን ለነዳጅ ማደያዎች ደግሞ ስራቸውን ፈጣንና ቀልጣፋ እንዲሆን ያግዛቸዋል፤ በተጨማሪም የመንግስት አካላትን የቁጥጥር ስርዓት በማሻሻል ረገድ የበኩሉን አስተዋጽኦ ያበረክታል ተብሎ ይጠበቃል። ባንኩ በተወሰኑ የተመረጡ የነዳጅ ማደያዎች የጀመረውን ይህን አገልግሎት በመላ ሀገሪቱ ከሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ጋር በመተባበር  ለማስፋፋት አቅዷል፡፡ ቡና ባንክ  የኢትዮጵያን የባንክ መሠረተ ልማት የማዘመን እና አስፈላጊ አገልግሎቶችን ዲጂታል የማድረግ ብሔራዊ ጥረቶችን ለመደገፍ ተልእኮውን አንግቦ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል። ከዚህ ጋር ተያይዞ ባንኩ ከዲጂታል ነዳጅ ክፍያ በተጨማሪ በመላ አገሪቱ ቀልጣፋ እና ተደራሽ አገልግሎትን በስፋት ለማቅረብ ለያዘው ዕቅድ ደህንነታቸው የተጠበቀ እና እየሰፉ የሚሄዱ የተለያዩ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎቶች ላይ ኢንቨስት ማድረጉን ቀጥሏል። ደንበኞች የነዳጅ ክፍያ አገልግሎቱን ለመጠቀም በቅድሚያ የቡና ባንክ ሞባይል ባንኪንግ አገልግሎትን መመዝገብ ያለባቸዉ ሲሆን በመቀጠል በመረጡት አማራጭ ክፍያቸዉን መፈፀም ይችላሉ፡፡ ደንበኞች ለተጨማሪ መረጃ 8501 ላይ በመደወል የደንበኞች አገልግሎት ሰራተኞችን ማነጋገርና መረጃ ማግኘት ይችላሉ። ቡና ባንክ ከ14ሺህ በላይ የሚሆኑ ባለአክሲዮኖች ያሉት ከ15 ዓመታት በፊት የተቋቋመና 454 በሚሆኑ ቅርንጫፎቹ በኢትዮጵያ ሁሉም ክልሎች አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ የባለራዕዮች ባንክ ነው፡፡ ባንካችን የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን አቅም ያገናዘበ ልዩ ልዩ የቁጠባና ብድር አገልግሎቶችን በማቅረብ ተዓማኒነትን አትርፏል፡፡ ሐምሌ 21-2017 በቡና ባንክ ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽንና ፕሮሞሽን ዋና ክፍል የተዘጋጀ

ጋዜጣዊ መግለጫ |Press release Read More »

አቦል ደሞዜ

ቡና ባንክ ለእናንተ ለውድ ቤተሰቦቻችን የደሞዝ መዳረሻ ብድር እና የዲጂታል ቁጠባ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንገኛለን። 💸🫰አቦል ደሞዜ የደሞዝ መዳረሻ ብድርን ለማግኘት የካቻ መተግበሪያን ከGoogle Play ወይም ከApp Store በማውረድ በባንካችን በኩል እንደደሞዝዎ መጠን በፐርሰንት መርጠው መበደር ይችላሉ።🤑💰ደሞዝ ደርሷል! 💲💲💲ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ ቅርንጫፍ ይሂዱ ወይም ወደ 8501 ይደውሉ።ቡና ባንክየባለራዕዮች ባንክ!ይፍጠኑ አሁኑኑ ይሞክሩት 👇For Android (https://play.google.com/store/apps/details…)For Iphone (https://apps.apple.com/us/app/kacha-customer/id6449651203) BunnaBank#kacha #CustomerFirst #Testimony #DigitalFinance #EthiopianBanks

አቦል ደሞዜ Read More »

This will close in 0 seconds

Open Your Bank Account Today!

አካውንት ይክፈቱ የክፍያ ካርድዎን ያዝዙ ፣ ፈጣን አገልግሎት ማግኘት ይጀምሩ! ዛሬውኑ ይቀላቀሉን!

Open Bunna Account

You cannot copy content of this page