Bunna Bank

Uncategorized

የኢ.አር.ፒ እና አቦል ዲጂታል ባንኪንግ ውጤታማ ትግበራን ተከትሎ ዕውቅናና ሽልማት ተሰጠ

በፕሮጀክቶቹ ከ 5 ሚሊዮን ዶላር በላይ ማዳን ተችሏል! ቡና ባንክ ኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ ፕሮጀክትና አቦል ዲጂታል ባንኪንግ መተግበሪያን ሙሉ በሙሉ ወደስራ ማስገባቱን ተከትሎ እነዚህ ሁለት ፕሮጀክቶች በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቁ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የባንኩ ሰራተኞች ዕውቅናና ሽልማት ሰጠ፡፡ ሐምሌ 29 ቀን 2016 ዓ.ም. የባንኩ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ አለማየሁ እና የኤክስኪዩቲቭ ማኔጅመንት አባላት በተገኙበት በተካሄደው የሽልማት ፕሮግራም ለ70 ባለሙያዎች ምስጋናና ዕውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡ የቡና ባንክ አቦል ዲጂታል ባንኪንግ መተግበሪያ በባንኩ ቺፍ ኢንፎርሜሽን ዘርፍ በተቋቋመው ቡድን በባንኩ ባለሙያዎች የራስ አቅም እንደአዲስ የተዘጋጀ መተግበሪያ ሲሆን አሁን ላይ በስኬታማነት አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተነግሯል፡፡ መተግበሪያው በራስ አቅም መልማቱ የባንኩ ሰራተኞች ልምድ እንዲያካብቱ ከማድረጉም በላይ ባንኩ 1.2 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ ከወጪ እንዲያድን ማድረጉ ተነግሯል፡፡ ይህንን መተግበሪያም ሆነ የኢአርፒ ስርዓትን ወደትግበራ ለማስገባት በነበረው ጥረት የባንኩ ኤክስኪዩቲቭ ማኔጅመንት የቅርብ ክትትልና ዕገዛ በማድረግ እንዲሁም ተገቢውን አቅጣጫ በወቅቱ በመስጠት የማይተካ ሚና ተጫውቷል ተብሏል። አሁን የተተገበረው የኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግ ሲይስተም በዉጭ ምንዛሬ ሊያሶጣ የሚችለዉን ከ 4 ሚሊዮን ዶላር  በላይ ገንዘብ ማዳን ተችሏል። ይህ የዕውቅናና ምስጋና ፕሮግራም መዘጋጀቱ ለፕሮጀክቱ ስኬታማነት አስተዋጽኦ ያበረከቱትን ከማመስገን ባለፈ ሌሎች የባንኩ ሰራተኞችና ባለሙያዎችን ለበለጠ ስራ ለማነሳሳትና ለማትጋት የሚረዳ መሆኑም ተገልጿል፡፡ በተያያዘም ባንኩ ኢንተርፕራይዝ ሪሶርስ ፕላኒንግን በተቋም ደረጃ በውጤታማት የተተገበረ ሲሆን ይህንን ፕሮጀክት ስኬታማ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱና ክትትል ሲያደርጉ ለነበሩ የሚመለከታቸው የባንኩ የስራ ክፍሎችና ባለሙያዎች ዕውቅና ተሰጥቷል፡፡ በዕለቱ የዕውቅና ፕሮግራም ላይ የተገኙት የባንንኩ ዋና ሰራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ አለማየሁ ባስተላለፉት መልዕክት የሁለቱ ፕሮጀክቶች በዚህ መልክ መጠናቀቅ ለወደፊቱ መሰል የባንካችን የሥራ ከፍሎችና ባለሙያዎች አርዓያ ከመሆኑ በተጨማሪ  ውጤታማ ፕሮጀክቶችን ዕውን ለማድረግ የሚያነሳሳ ምሳሌ የሆነ ስራ በመሆኑ ሊበረታታ የሚገባው ተግባር ነው ብልዋል። በፕሮጀክቶቹ ትግበራ ላይ ከተካፈሉ ባለሙያዎችም ምስጋና አቅርበዋል። ፡ ዋና ስራ አስፈጻሚው የሲስተሞቹን ውጤታማ ዘላቂነት ለማረጋገጥ የሚመለከታቸው የባንኩ የሥራ ክፍሎች ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ተገቢውን ክትትል ማድረግ እንደሚገባቸውም አጽንኦት ሰጥተው አሳስበዋል፡፡

የኢ.አር.ፒ እና አቦል ዲጂታል ባንኪንግ ውጤታማ ትግበራን ተከትሎ ዕውቅናና ሽልማት ተሰጠ Read More »

የተሻሻለውን የቡና መተግበሪያ ሞክረውታል?

አዲሱን የቡና ባንክ የሞባይል መተግበሪያ አውርደዋል? 🚀✨ ውድ የቡና ቤተሰቦች የተሻሻለውን መተግበሪያችንን ዛሬውኑ አውርደው በእንከን የለሽ፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ቀላልና ፈጣን የባንክ አገልግሎታችን እፎይ ብለው ደስታዎን ያጣጥሙ። 📱💰 Play Store (https://play.google.com/store/apps/details?id=com.bunnabanksc.bunnamobile) App Store (https://apps.apple.com/se/app/bunna-bank-abol-mobile-banking/id6502711479?l=en-GB) #BunnaBank #MobileBanking #UpgradeNow

የተሻሻለውን የቡና መተግበሪያ ሞክረውታል? Read More »

እንኳን ለ1445ኛው የኢድ-አል-አድሐ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

ቡና ባንክ ለመላው የእስልምና ዕምነት ተከታይ የቡና ቤተሰቦች እንኳን ለ1445ኛው ዓመተ ሂጅራ የኢድ-አል-አድሐ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ በማለት መልካም ምኞቱን ይገልጻል። መልካም በዓል!

እንኳን ለ1445ኛው የኢድ-አል-አድሐ (አረፋ) በዓል በሰላም አደረሳችሁ! Read More »

አስተያየትዎን በመግለጽ ይሸለሙ!

መጠይቁን ሞልተዋል? ቡና ባንክ በአገልግሎት አሰጣጥ ዙሪያ መረጃዎችን ለመሰብሰብ ያዘጋጀውን መጠይቅ ከስር ከተቀመጡት ሊንኮች መካከል እርሶን የተመለከተውን በመንካት ጠቃሚ ሀሳብዎን ያጋሩን፡፡ 1. ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት ደንበኞች (https://forms.gle/MpFLxXZMkJG6KViE9) 2. ለዓለም አቀፍ የባንክ አገልግሎት ደንበኞች የቀረበ መጠይቅ (https://forms.gle/VPi5xFGzm6MwegKy7) 3. ለብድር አገልግሎት ደንበኞች (https://forms.gle/ey8wJdrjoJnz3UVq6) 4. ለቁጠባ ሂሳብ የባንክ አገልግሎት ደንበኞች (https://forms.gle/RjxoJU7faAUW9MW59) 5. ለዲጂታል የባንክ አገልግሎት ደንበኞች (https://forms.gle/866QWhpsoAS9ar479) ስለተሳትፎዎ እናመሰግናለን! መጠይቁን ሞልተው ከሚልኩ ደንበኞች መካከል በዕጣ በመለየት ወርሃዊ ያልተገደበ ኢንተርኔት የምንሸልም ሲሆን የሽልማት ዕጣ ውስጥ ለመካተት ስልክ ቁጥርዎን ወይም ኢሜይል ማስገባትዎን አይርሱ! ይህንን መልዕክት ለሌሎች ያጋሩ! ቡና ባንክ የባለራዕዮች ባንክ!

አስተያየትዎን በመግለጽ ይሸለሙ! Read More »

እጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ጥቆማ ለመቀበል የወጣ ማስታወቂያ

ለቡና ባንክ አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ እጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ጥቆማ ለመቀበል የወጣ ማስታወቂያ የቡና ባንክ አ.ማ የባላክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔ ህዳር 30 ቀን 2016 ባካሄደው 14ኛ መደበኛ ስብሰባ ያቋቋመው የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ጥቆማና አስመራጭ ኮሚቴ ከሰኔ 01 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ጥቆማ በመቀበል ላይ የሚገኝ ሲሆን የቦርድ አባላትን ለመጠቆም የሚያስችለውን የጥቆማ መሙያ ቅጽ በቡና ባንክ አ.ማ ድረ ገጽ https://www.bunnabanksc.com ወይም የባንኩ ዋና መሥሪያ ቤት በሚገኝበት ቦሌ መንገድ ሩዋንዳ መታጠፊያ አካባቢ ባለው የቡና ባንክ አ.ማ ሕንፃ 8ኛ ፎቅ በሚገኘው የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ ጽ/ቤት ቢሮ ወይም በባንኩ ቅርንጫፎች ማግኘት ይቻላል፡፡ ስለሆነም ባለአክሲዮኖች ለዳይሬክተሮች የቦርድ አባልነት ብቁ የሆኑትን ለባንኩ ሁለንተናዊ እድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከት የሚችሉትን እና ከታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉትን እጩዎች በቅጹ ላይ በጥንቃቄ በመሙላት እስከ ጳጉሜ 05 ቀን 2016 ዓ.ም  ድረስ ብቻ ከላይ በተገለፀው የኮሚቴው ጽ/ቤት በአካል በማቅረብ ወይም አድራሻውን ለቡና ባንክ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ  አባላት ጥቆማ አስመራጭ ኮሚቴ በማለት በባንኩ የፓ.ሣ.ቁጥር 1743 ኮድ 1110  በአደራ ደብዳቤ መላክ ወይም የተሞላውን ቅፅ ስካን በማድረግ ለዚሁ ዓላማ በተዘጋጀው በባንኩ ኢሜል bibnomination@bunnabanksc.com አያይዘዉ መላክ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ ተጠቋሚ እጩ የቦርድ አባላት የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል፤ የባንኩ ባላክሲዮን የሆነ/ነች እድሜው 30 ዓመት  በላይ የሆነ/ነች የዳይሬክተሮች የቦርድ አባል ሆኖ/ሆና ቢመረጥ/ብትመረጥ ለመሥራት ፈቃደኛ የሆነ/ች፣ ከታወቀ የከፍተኛ የትምህርት ተቋም ቢያንስ የመጀመሪያ ዲግሪ ያጠናቀቀ/ች፣ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት ስብስብ በባንክ ሥራ፤ በፋይናንስ፤ በአካውንቲንግ፤በማኔጅመንት፤ በኢኮኖሚክስ፤በህግ፤በቢዝነስ አስተዳደር፤በኦዲቲንግ፤በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ወይንም በኢንቨስትመንት ማኔጅመንት መሰረታዊ ክህሎትን /ችሎታን ያካተተና የጾታ ስብጥርን ያገናዘበ  ቢሆን ይመረጣል፣ የፋይናንስ ድርጀት የቦርድ ዳይሬክተር ያልሆነ/ነች ወይም ዳይሬክተሩ/ሯ 10% ወይም  ከዚያ በላይ የባለቤትነት ድርሻ ያልያዘበት/ችበት የንግድ ድርጅት፤ የማንኛውም ባንክ ተቀጣሪ ሠራተኛ ያልሆነ/ነች፤ የቡና ባንክ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ አስመራጭ ኮሚቴ አባል ያልሆነ/ነች፤ በግሉ/ሏ ወይም ሌላ ባላክሲዮንን በመወከል በቡና ባንክ አክሲዮን ማህበርን ለስድስት ዓመታት በቦርድ አባልነት አገልግሎ/ላ የለቀቀበት/ቀቀችበት ጊዜ ጀምሮ ስድስት ዓመታት ያለፈው/ያለፋት፤ በብሄራዊ ባንክ እምነት መሰረት ታማኝ፤ሐቀኛ ጠንቃቃና መልካም ዝና ያለው/ያላት፤ መልካም የፋይናስ ታሪክና አቋም ያለው/ያላት፤ የንግድ ስራ ከመተግበር ወይም ድርጅትን ከመምራት አኳያ በፍርድ ቤት የመክሰር ውሳኔ ያልተላለፈበት/ባት፤ ከታክስና ከባንክ ክፍያዎች ጋር በተያያዘ ግዴታዎቹን/ቿን በአግባቡ የተወጣ/ች፤ መልካም ስነምግባር ያለው/ያላት ፤ከዚህ በፊት በንግድ ማህበር አደራጅነት ዳይሬክተርነት ፤ስራ አስኪያጅነት፤ ተቆጣጣሪነት ኦዲተርነት፤ ወይም በሌላ የአመራር ኃላፊነት ላይ ተመድቦ/ባ ሲሰራ/ስትሰራ ኃላፊነቱ/ቷ ጋር በተያያዘ ወይም በማናቸውም ሌላ ሁኔታ በኢትዮጲያ ውስጥም ሆነ ከኢትዮጲያ ውጭ በእምነት ማጉደል፤ በስርቆት፤ በማጭበርበር፤ በውንብድና፤ ወይም በሌላ ለቦርድ አባልነት ብቁ በማያደርግ ተመሳሳይ ወንጀል በፍ/ቤት ተከሶ/ሳ የጥፋተኝነት ውሳኔ ያልተሰጠበት/ባት፤ ከመንግስት ባለስልጣናት መረጃን በመደበቅ የተሳሳቱ የሂሳብ ወይም ሌሎች ሰነዶችን በመስጠት የተቆጣጣሪ አካላትን  ማረጋገጫዎች ባለመቀበል መስፈርቶችን ባለማሟላት የርምት ወይም የማስተካካያ እርምጃዎችን ባለመውሰድ ሪከርድ የሌለበት/ባት፤ በኢትዮጲያ ውስጥም ሆነ በውጭ  ሀገር በሚገኝ በማናቸውም በፈረሰ ባንክ ውስጥ ዳይሬክተር የነበረ/ረች ከሆነ በቅድሚያ በብሔራዊ ባንክ የፅሁፍ ፈቃድ ማቅረብ የሚችል/ምትችል ፤ ዕጩ ተጠቋሚው በህግ የሰውነት መብት የተሰጠው ድርጅት ከሆነ ድርጅቱን ወክሎ የሚያገለግል ተጠቋሚ ተወካይ (ጠተፈጥሮ ሰው) መመደብ ያለበት ሲሆን ይህ ተወካይ ሁሉንም መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅበታል፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር በ011-1-264357 በመደወል ባለአክሲዮኖች ማብራሪያ ማግኘት ይችላሉ፡፡ ማሳሰቢያ፤ አስመራጭ ኮሚቴው ከጳጉሜ 05 ቀን 2016 ዓ.ም በኋላ የሚቀርቡ ጥቆማዎችን የማይቀበል መሆኑን ከወዲሁ ያሳስባል፡፡  የቡና ባንክ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላት አስመራጭ ኮሚቴ

እጩ የዳይሬክተሮች ቦርድ አባላትን ጥቆማ ለመቀበል የወጣ ማስታወቂያ Read More »

ይደውሉልን! ☎️

በ8501 ሲደውሉ የቡና ባንክ የጥሪ ማዕከል እርስዎን ለማገዝ ዝግጁ ሆኖ ይጠብቅዎታል። 📌 ስለባንኩ ምርቶች፣ ተመኖች እና አገልግሎቶች አጠቃላይ መረጃ ለማግኘት፣ ለአፋጣኝ ምላሽ፣ ለግል አገልግሎት፣ ቀሪ ሒሳብ ለማጣራትና በስልክ ለማስተላለፍ፣ ለአስተያየትና ጥቆማዎች፣ እንዲሁም ችግሮችን ሪፖርት ለማድረግ ሲፈልጉ በ8501 ነጻ የስልክ መስመር በመደወል አንድም በሚፈልጉት አገልግሎት ታግዘው አንድም የአገልግሎታችንን ጥራት እንድናሻሽል አግዘው ቤተሰባዊነትዎን እንዲያጠናክሩ እንጋብዛለን። 🤝 ቡና ባንክ የባለራዕዮች ባንክ! ይጻፉልን፦ contactcenter@bunnabanksc.com #contactusnow #bunnabankcontactcenter #8501

ይደውሉልን! ☎️ Read More »

ቡና ባንክ ከ ኪ ሃውሲንግ ፋይናንሺያል ሶሉሽን ጋር የአጋርነት ስምምነት ተፈራረመ

ኪ ሃውሲንግ ፋይናንሺያል ሶሉሽን አነስተኛና መካከለኛ ገቢ ያላቸውን ቤት ፈላጊዎች የቤት ባለቤት ለማድረግ የ Key CHF ሞዴል በመቅረጽ ወደስራ የገባ ተቋም ነው። ይህ ተቋም በዕቁብ የመኖሪያ ቤት ለማግኘት የሚመዘገቡ ደንበኞቹ ክፍያቸውን በዝግ ሂሳብ በቡና ባንክ እንዲያስቀምጡ ከቡና ባንክ ጋር በጋራ ለመስራት ስምምነት ላይ ደርሶ ስራ ጀምሯል። በቡና ባንክ እና በኪ ሃውሲንግ ፋይናንሺያል ሶሉሽን የተደረሰው በጋራ የመስራት ስምምነት ይፋዊ የፊርማ ስነስርዓት ዛሬ ግንቦት 1 ቀን 2016 ዓ.ም በካፒታል ሆቴል እና ስፓ ተካሂዷል። ስምምነቱን ከቡና ባንክ ወገን የባንኩ ቺፍ . ኮርፖሬት ሰርቪስ ኦፊሰር አቶ ለውጤ ጥሩሰው ከኪ ሃውሲንግ ፋይናንሺያል ሶሎሽን መስራችና ስራ አስኪያጅ ጋር ተፈራርመዋል። በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ አቶ ለውጤ እንደተናገሩት ቡና ባንክ ከተቋሙ ጋር የገባበት ስምምነት በሁለት መንገድ የሚመጡ የደንበኞች ክፍያዎችን በማስቀመጥ የባንክ አገልግሎትን መስጠት ላይ ያተኮረ ነው። ይኸውም ተቋሙ ከደንበኞች የሚሰበስበውን የመኖሪያ ቤት መግዣ ቅድመ ክፍያ እንዲሁም ሌሎች ከግዢው ጋር የተያያዙ ክፍያዎች በደንበኛው ስም በባንኩ በተከፈተ ዝግ ሂሳብ ማስቀመጥና ደንበኛው የቤቱ ባለቤት ሲሆን ለተቋሙ መልቀቅ ፣ እንዲሁም የአገልግሎት ክፍያዎችን በባንኩ በተከፈተ የተቋሙ ተንቀሳቃሽ ሂሳብ መሰብሰብና የተመለደ የባንክ አገልግሎትን መስጠት ላይ ያተኮረ ነው። በተጨማሪም ቡና ባንክ ከተቋሙ ስራ ጋር የሚሄድና የደንበኞችን የባንክ አገልግሎት ማዘመን የሚያስችሉ ዘመናዊ አሰራሮችን ለመተግበር ዝግጁ መሆኑንም አቶ ለውጤ በስነስርዓቱ ላይ ጠቁመዋል። ኪ ሃውሲንግ ፋይናንሺያል ሶሉሽን በዕለቱ ከቡና ባንክ በተጨማሪ ከጸሃይ ባንክ እና ከቡና ኢንሹራንስ ጋር ስለገባው ስምምነት ገለጻ አድርጓል። ከአዲስ አበባ ሆቴልና ቱሪዝም ማህበር አባል ሰራተኞችን የቤት ባለቤት ለማድረግ በሚያስችለው አሰራር ዙሪያም ከተቋሙ ሰራተኞች እና ከማርኬቲንግ ኩባንያዎች ጋር ውይይት አድርጓልማርኬቲንግ ኩባንያዎች ጋር ውይይት አድርጓል። የተቋሙ ስራ የባንክ የኢንሹራንስ አጋርነት ያለው፤ በአነስተኛ ክፍያና አነስተኛ ወርሀዊ ቁጠባ በመቆጠብ ከወለድ ነፃ በሆነ የረዥም ጊዜ አከፋፈል አባላቶቹ የቤት ባለቤት የሚሆኑበት የዕቁብ (የተዘዋዋሪ ፈንድ) ሞዴል ተግባራዊ ያደረገ መሆኑም ተጠቁሟል።

ቡና ባንክ ከ ኪ ሃውሲንግ ፋይናንሺያል ሶሉሽን ጋር የአጋርነት ስምምነት ተፈራረመ Read More »

This will close in 0 seconds

Open Your Bank Account Today!

አካውንት ይክፈቱ የክፍያ ካርድዎን ያዝዙ ፣ ፈጣን አገልግሎት ማግኘት ይጀምሩ! ዛሬውኑ ይቀላቀሉን!

Open Bunna Account

You cannot copy content of this page