Bunna Bank

ቡና ባንክ በ2026/27 በጀት ዓመት 1ኛ ሩብ ዓመት የላቀ አፈጻጸም ላሳዩ ቅርንጫፎችና ዲስትሪክቶች የዋንጫና የማበረታቻ ሽልማት አበረከተ

የቡና ባንክ አ.ማ. ከጥቅምት 19-20 2019 ዓ.ም ለሁለት ቀናት ሲያካሂድ የቆየውን የ2026/27 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት የሥራ አፈጻጸም ግምገማ በደማቅ የሽልማትና የእውቅና ሥነ-ሥርዓት አጠናቋል።

በዚሁ የሽልማት መርሃ-ግብር ላይ በሩብ ዓመቱ ከተቀመጠላቸው የውጤት መለኪያ አንጻር 100% እና ከዚያ በላይ በማስመዝገብ የላቀ አፈጻጸም ያሳዩ 66 ቅርንጫፎች በሙሉ የልዩ ምስክር ወረቀት መሆናቸው ታውቋል። ከእነዚህም መካከል 22 ቅርንጫፎች ከደቡብ አዲስ አበባ፣ 19 ከምዕራብ አዲስ አበባ፣ 17 ከምስራቅ አዲስ አበባ እንዲሁም 8 ቅርንጫፎች ከአዳማ ዲስትሪክት የተውጣጡ ናቸው።

ባንኩ ባዘጋጀው በዚሁ የሽልማት እና ማበረታቻ መርሃግብር ላይ በእነዚህ 4 ዲስትሪክቶች ስር የላቀ ውጤት በማስመዝገብ ከ1ኛ እስከ 3ኛ ደረጃ ይዘው ያጠናቀቁትን የቅርንጫፍ ኮከቦች ይፋ አድርጓል፦በዚህ መሰረት ፣

ከአዳማ ዲስትሪክት፦ የደረጃው ከፍተኛ የላቀ ዋንጫ እና የገንዘብ ተሸላሚ የአዳማ ቦኩ ቅርንጫፍ  ሲሆን፤ የአዳማ አራዳ ቅርንጫፍ 2ኛ እንዲሁም የቀርሳ ቅርንጫፍ 3ኛ ደረጃን በመያዝ አጠናቀዋል።

ከምዕራብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት፦ የእሪ በከንቱ ቅርንጫፍ በላቀ አፈፃፀም የዋንጫ እና የገንዘብ ተሸላሚ ሲሆን፤ የመሀል መርካቶ ቅርንጫፍ 2ኛ እንዲሁም የልደታ ቅርንጫፍ 3ኛ ደረጃን ይዘዋል።

ከደቡብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት፦ በሁሉም የደረጃ ስብስቦች ሴት የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች ያሸነፉበት ይህ ዲስትሪክት፤ የአፍሪካ ህብረት ቅርንጫፍ  1ኛ በመሆን የላቀ ዋንጫውን ሲወስድ፤ የስታዲየም ቅርንጫፍ 2ኛ እንዲሁም የጎተራ ቅርንጫፍ 3ኛ ደረጃን አግኝተዋል።

ከምስራቅ አዲስ አበባ ዲስትሪክት፦ የከበደ ሚካኤል ቅርንጫፍ በላቀ አፈፃፀም ዋንጫና የ1ኛ ደረጃ ሽልማትን ሲቀዳጅ፤ የሃያሁለት ማዞሪያ ቅርንጫፍ 2ኛ እንዲሁም የሻላ ቅርንጫፍ 3ኛ ደረጃን ይዘው የገንዘብና የምስጋና ምስክር ወረቀት ተሸላሚ ሆነዋል።

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ እንደተገለጸው፤ የተሰጡት ዋንጫዎች ተዘዋዋሪ ሲሆኑ፣ በበጀት ዓመቱ መጨረሻ ላይ በአራቱም ሩብ ዓመታት አማካይ ውጤት ከአጠቃላይ ዲስትሪክቱ አንደኛ የወጣው ቅርንጫፍ ዋንጫውን በቋሚነት የራሱ እንደሚያደርግ ተብራርቷል።

በዲስትሪክቶች ደረጃ የተመዘገበውን ውጤት ተከትሎ፣የባንኩ ቺፍ ፋይናንስ እና ኮርፖሬት ሰርቪስ ኦፊሰር አቶ ለውጤ ጥሩሰውን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች ሽልማቱን ያበረከቱ ሲሆን፤ በተቀመጠው የዉጤት መለኪያ መሰረት ግቡን እጥፍ በማድረግ 198.8% ያስመዘገበው የደብረማርቆስ ዲስትሪክት የሩብ ዓመቱ ታላቅ ኮከብ 1ኛ ደረጃ ተሸላሚ በመሆን የገንዘብ ሽልማትና የእውቅና ደብዳቤ ወስዷል። የደቡብ አዲስ አበባ ዲስትሪክት ግቡን 123.8% በማሳካት 2ኛ ደረጃን፣ የባህር ዳር ዲስትሪክት የግቡን 110.7% በማሳካት 3ኛ ደረጃን እንዲሁም የደብረ ብርሃን ዲስትሪክት የግቡን 106.2% በማሳካት 4ኛ ደረጃን በመያዝ የላቀ አፈጻጸም ያሳዩ የባንኩ የጥንካሬ ምሶሶዎች መሆናቸውን በማስመስከር ሽልማታቸዉን ወስደዋል።

በማጠቃለያው የባንኩ ከፍተኛ አመራሮች ለተሸላሚዎች በሙሉ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን፣ የተመዘገቡት ስኬቶች በቀጣዮቹ ሩብ ዓመታትም ይበልጥ ተጠናክረው እንዲቀጥሉና መላው የባንኩ ሰራተኛ ባንኩን ወደ ላቀ ከፍታ ለማውጣት በጋራ እንዲረባረብ አቅጣጫ በማስቀመጥ መርሃ-ግብሩ በስኬት ተጠናቋል።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

This will close in 0 seconds

Open Your Bank Account Today!

አካውንት ይክፈቱ የክፍያ ካርድዎን ያዝዙ ፣ ፈጣን አገልግሎት ማግኘት ይጀምሩ! ዛሬውኑ ይቀላቀሉን!

Open Bunna Account

You cannot copy content of this page