Bunna Bank

Solomon mekbib

ቡና ቤተሰብ

ልክ እንደ ቤተሰብ፣ በቡና ዙሪያ እንደመሰብሰብ። ከእናንተ ከደንበኞቻችን፣ ከሰራተኞቻችን እና ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠር፣ በመደጋገፍና በጋራ ስኬት እናምናለን። እኛ ከባንክ በላይ ማህበረሰብ ነን። ይቀላቀሉን! #ቡናቤተሰብ #Bunna Bank #የባለራዕዮች_ባንክ Facebook፡ https://lnkd.in/ezy8STY6 Telegram፡ https://t.me/bunnabanksc Twitter፡ https://lnkd.in/ehRShZw Instagram፡ https://lnkd.in/eFUR6cs YouTube: https://lnkd.in/eSTq7UvJ LinkedIn: https://lnkd.in/ejgeD9zM TikTok: https://lnkd.in/eUXRDDCw

ቡና ቤተሰብ Read More »

ቡና ደራሽ

በቡና ባንክ እና በደራሽ የውሃ፣ የመብራትና የታክስ ሂሳብዎን ያለምንም እንግልት ይክፈሉ! ባሉበት ሆነው ያለምንም ወረፋ፣ ስልክዎን/ታብሌትዎን/ኮምፒውተርዎን ብቻ መጠቀም ይችላሉ። በቡና እና ደራሽ ደህንነቱ የተጠበቀ ፈጣን አገልግሎት በመዘግየት ከሚመጣ የክፍያ ቅጣት ራስዎን በመከላከል ገንዘብዎን ይቆጥቡ። በድረ-ገጹ ይመዝገቡ፣ መተግበሪያውን ያውርዱ ወይም በአቅራቢያዎ የሚገኝ የባንካችንን ቅርንጫፍ ይጎብኙ። በቡና ባንክ እና በደራሽ ምቾቱ የተጠበቀ ቀልጣፋ አገልግሎት ህይወትዎን ያቅልሉ። #Derash #BunnaBank #DigitalBanking

ቡና ደራሽ Read More »

Bunna Merchant Pay

ወደ ንግድ ማዕከላት ለግብይት ሲወጡ በካሽ ገንዘብ አልያዝኩም ብለው እንዳይጨነቁ!!! ቡና ባንክ ምቹ፣ ቀልጣፋና ዘመናዊ የግብይት ስርዓት መፈፀሚያ በእጅ ስልክዎ እንዲያከናዉኑ ሁኔታዎችን አመቻችቷል!!! ወደገበያ ማዕከላት ሲሄዱና የሚፈልጉትን ሲገበያዩ የቡና ባንክ “ቡና መርቻንት ፔይ” መተግበሪያ በተንቀሳቃሽ ስልክዎ መኖሩን ብቻ እርግጠኛ ይሁኑ፡፡ ሁሉንም ግብይት ደስ እያልዎት ያከናውናሉ፡፡ በዚህ ቀልጣፋ እና ጊዜ ቆጣቢ ዘመናዊ አገልግሎታችን የሞባይል ስልክዎ ላይ ባለው መተግበሪያ የነጋዴዎችን አጭር መለያ ቁጥር በማስገባት ወይም በ QR Code ማመሳከሪያ በመጠቀም ክፍያዎን ይፈፅሙ፡፡ ቡና መርቻንት ፔይ (Bunna Merchant Pay) ቡና ባንክ የባለራእዮች ባንክ!!

Bunna Merchant Pay Read More »

ቡና ባንክ የጉዞዎ አጋር!!

የፐብሊክ ትራንስፖርት አገልግሎት ድርጅት በከፍተኛ ወጪ ከውጪ ባስመጣቸውና ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን በጠበቁ እጅግ ዘመናዊ አገር አቋራጭ የህዝብ ትራንስፖርት ወደተለያዩ ከተሞች ጉዞ ማድረግ ይችላሉ፡፡ ለቀጣይ ወደተለያዩ የአገራችን ከተሞች ጉዞ ለማድረግ ሲያስቡ የዚህን ዘመናዊ የትራንስፖርት አገልግሎት ትኬት ለመቁረጥ ሌሊት መነሳት፣ ወረፋ መጠበቅ እና መጉላላት አይጠበቅብዎትም። ለራስዎም ሆነ ለወዳጅ ዘመድ ቲኬቱን መቁረጥ ሲፈልጉ ፈጣንና አስተማማኝ የሆነውን መንገድ ይምረጡ። በአካባቢዎ ባለ የትኛውም የቡና ባንክ ቅርንጫፍ ሄደው ወይም ሰው ልከው የጉዞ ትኬትዎን ቆርጠው በእጅዎ ማስገባት ይችላሉ። መልካም ጉዞ! #TravelEasy #publicbus #Bunnabank

ቡና ባንክ የጉዞዎ አጋር!! Read More »

በእምነት ሳይሆን በፍላጎት!

ከአልኮል መጠጥ ማምረትና ንግድ፣ ከዓሳማ ማርባትና የዓሳማ ሥጋ ንግድ፣ ከቁማርና ቁማር ነክ የሥራ ዘርፎች፣ ከወሲብ ንግድ፣ እንዲሁም በአጠቃላይ ለህብረተሰብ ጎጂ ተብለው በሸሪዓው ከተለዩ የሥራ ዘርፎች ውጪ ተሰማርተው ምንም ዓይነት ወለድ በመስጠትም ሆነ በመቀበል ላይ ያልተመሰረተ የፋይናንስ አገልግሎት ማግኘት ይፈልጋሉ? እንግዲያውስ ቡና ባንክ ፍላጎትዎን እንጂ እምነትዎን ሳይጠይቅ፣ በሚከተሉት ሃይማኖት ያልተገደበ የኻዲም ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት አዘጋጅቶ በብቃት ሊያገለግልዎ በደስታ ይጠብቅዎታል። ባንካችን ከብሔራዊ ባንክ ባገኘው ፈቃድ መሰረት በመላ ሀገሪቱ በከፈታቸው ቅርንጫፎች ተለይተው በተዘጋጁ መስኮቶች እና ሙሉ ለሙሉ ከወለድ ነጻ የባንክ አገልግሎት በሚሰጡ ቅርንጫፎች ይህን የተቀላጠፈ የባንክ አገልግሎት እንዲጠቀሙ ይጋብዛል፡፡ #BunnaKhadim #BunnaBank #InterstFreeBanking

በእምነት ሳይሆን በፍላጎት! Read More »

ሂሳብዎ ላይ እገዛ ይፈልጋሉ?

በ8501 ሲደውሉ የቡና ባንክ የጥሪ ማዕከል ለመርዳት ዝግጁ ሆኖ ይጠብቅዎታል፡- ለፈጣን መልሶች፡ ለአፈጣኝ መፍትሄ ከማዕከሉ ወኪሎች ጋር ወዲያውኑ ይገናኛሉ፣ ለግል አገልግሎት፡ ለሂሳብ መለያዎ የተዘጋጀ ልዩ እገዛ ያገኛሉ፣ ለአጠቃላይ መረጃ፡ ስለባንኩ ምርቶች፣ ተመኖች እና አገልግሎቶች ያውቃሉ፣ ለምቹ ግብይት፡ ቀሪ ሒሳብ ለማጣራት እና በስልክ ለማስተላለፍ ከተቸገሩ በማዕከላችን ይስተናገዳሉ፣ ለአስተያየት፡ ጥቆማዎችን ማቅረብ ወይም ችግሮችን ሪፖርት ማድረግ ይችላሉ፣ በ8501 ነጻ የስልክ መስመር በመደወል የአገልግሎታችንን ጥራት እንድናሻሽል ያግዙን። ለበለጠ መረጃ፡ የቡና ባንክ ድረ-ገጽን ወይም በአቅራቢያዎ የሚገኝን ቅርንጫፍ ይጎብኙ። ቡና ባንክ የባለራዕዮች ባንክ! #contactusnow #bunnabankcontactcenter #8501

ሂሳብዎ ላይ እገዛ ይፈልጋሉ? Read More »

ቡና ባንክ በ3ኛው የ”ይቆጥቡ ይሸለሙ” ፕሮግራም ላይ ለተሳተፉ የዕጣ አሸናፊ መምህራን እና የጤና ባለሙያዎች ሽልማት ሰጠ!

• ወ/ሮ ፈንታዬ ደምሌ የዘመናዊ የቤት አውቶሞቢል አሸናፊ ሲሆኑ ሌሎች አሸናፊዎችም ሽልማቶቻቸውን ተረክበዋል፡፡ቡና ባንክ አክሲዮን ማህበር ለወራት ሲያካሂድ የቆየውን ሶስተኛውን ዙር የመምህራንና የጤና ባለሙያዎች ይቆጥቡ ይሸለሙ መርኀ-ግብር ማጠናቀቂያ ምክንያት በማድረግ ያዘጋጃቸውን ሽልማቶች ዛሬ ታህሳስ 23 ቀን 2016 ዓ.ም. ለዕድለኛ ደንበኞቹ በይፋ አስረከበ፡፡በቡና ባንክ ዋና መስሪያ ቤት በተካሄደው በዚሁ የሽልማት አሰጣጥ ስነ-ስርዓት ላይ አሸናፊ ለሆኑ ባለዕድለኞች የአውቶሞቢል፣ ላፕቶፕ፣ ታብሌት እና ዘመናዊ የስልክ ቀፎ ሽልማቶችን አበርክቷል፡፡የኢትዮጵያ የሶስተኛ ትውልድ ሀገር በቀል የፋይናንስ ተቋም የሆነው ቡና ባንክ መምህንና የጤና ባለሙያዎች በቡና ባንክ በመቆጠብ ላሳዩት ያላሰለሰ ጥረት እና በቡና ባንክ ቁጠባና ሽልማት ፕሮግራም በመሳተፍ የዕጣ አሸናፊ በመሆቸው የቁጠባ ፕሮግራሙ ተሸላሚ ሆነዋል።እነዚህ የተከበሩ የአገር ባለውለታዎች የቁጠባ ልማዳቸውን እና አስተዋይነት የተሞላበት የፋይናንስ ውሳኔዎቻቸውን ለማበረታታት እና ለመሸለም በተቀረጸው ኢኒሼቲቭ መነሻነት ቡና ባንክ ዛሬ በተካሄደው ታላቅ የሽልማት ስነ – ስርአት የቁጠባና የሽልማት ፕሮግራም ለሶስተኛው ዙር አሸናፊዎች ሽልማት አበርክቷል።ቡና ባንክ የሀገራችን የወደፊት እጣ ፈንታ በመቅረጽ ረገድ ትልቅ ሚና የሚጫወቱትን ድንቅ ሙያተኞችን በማክበሩ ኩራት ይሰማዋል። እነዚህ ባለሙያዎች ለትምህርት እና ለጤና አጠባበቅ ዘርፎች ያበረከቱት የማይናቅ አስተዋፅዖ በእውነት አበረታች በመሆኑ በቁጠባ ላይ ያላቸውን ቁርጠኝነት እንደ ቡና ባንክ በቋሚነት የምናስተዋውቀውና የምናበረታታው የፋይናንስ ተቋም ኃላፊነትን ማሳያ ነው።ቁጠባ ለግለሰብ ፋይናንሺያል ደህንነት ብቻ ሳይሆን ለሀገራዊ እድገት ለውጥ የሚያመጣ ወሳኝ ሚና ይጫወታል። የቁጠባ ልማዶችን በአነዚህ ጥንቁቅና ቁርጠኛ ባለሙያዎች ዘንድ እንዲዳብር በማድረግ ባንካችን የፋይናንስ ግባቸውን እንዲያሳኩ እና ለኢትዮጵያ አጠቃላይ የኢኮኖሚ ዕድገትና ብልፅግና የሚጠበቅባቸውን አስተዋፅኦ እንዲያበረክቱ በማድረግ ላይ ይገኛል።ቡና ባንክ መምህራንን እና የጤና ባለሙያዎችን ለመደገፍ ያላሰለሰ ሙያዊ ድጋፍና ጥረት በማድረግ የፋይናንሺያል እውቀታቸው እንዲያድግ እና የቁጠባ ባህልን በመላው ኢትዮጵያ ለማጎልበት ያለውን ቁርጠኝነት በድጋሚ ያረጋግጣል።ባንካችን ከእነዚህ ውድ የአገራችን ባለሙያዎች ጎን በመቆም የፋይናንሺያል ደህንነታቸውን ለማረጋገጥ እና በሙሉ ልባቸው በክቡር ሙያቸው ላይ እንዲያተኩሩ ለማድረግ ጥረቱን አጠናክሮ ይቀጥላል። እንደ አንድ የፋይናንስ ተቋም የቁጠባ ልማዶችን እንዲስፋፉ በማስተዋወቅ የፋይናንስ ብልጽግና ለሁሉም ተደራሽ የሆነባትን ኢትዮጵያ በጋራ መገንባት እንደምንችል በፅኑ እናምናለን።ይህ የይቆጥቡ ይሸለሙ የቁጠባ እና የሽልማት መርሃ ግብር የቡና ባንክ ለማህበራዊ ሃላፊነት ያለውን የማያወላውል ቁርጠኝነት እና ኃላፊነት በተሞላበት የፋይናንስ አሰራር ግለሰቦችን ለማብቃት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይ ተግባር ነው። ስለሆነም ባንኩ የቁጠባ ልማዶችን ለማስተዋወቅ እና ለኢትዮጵያ ዘላቂ የኢኮኖሚ እድገትና ልማት የበኩሉን አስተዋፅኦ ለማድረግ ጥረቱን አጠናክሮ የሚቀጥል ይሆናል።ቡና ባንክ በኢትዮጵያ የሶስተኛ ትውልድ ሀገር በቀል የፋይናንስ ተቋም ሲሆን ከ2 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን በቅርንጫፎች፣ በኤቲኤም እና በተለያዩ የዲጂታል አማራጮች ማበረሰቡን እያገለገለ ይገኛል። ባንኩ አዳዲስ የፋይናንሺያል አገልግሎት አማራጮችን ለማቅረብ፣ የፋይናንስ አካታችንትን ለማስተዋወቅ እና ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እድገት የበኩሉን አስተዋፅኦ ለማድረግ የበኩሉን ጥረት በማድረግ ላይ ነው፡፡ ቡና ባንክ በኢትዮጵያውያን ዘንድ የቁጠባ ባህልን በማስተዋወቅ ረገድ ፈር ቀዳጅ ከሆኑ የፋይናንስ ተቋማት መካከል አንዱ ሲሆን የቡና ባንክ ቁጠባና ሽልማት ፕሮግራምም ለዚህ አንዱ ማሳያ ነው።ቡና ባንክ ከ14ሺህ በላይ በሆኑ ባለአክሲዮኖች ያሉት ከ14ዓመታት በፊት የተቋቋመና 476 በሚሆኑ ቅርንጫፎቹ በኢትዮጵያ ሁሉም ክልሎች አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ የቡና ቤተሰቦችን ያሰባሰብ የባለራዕዮች ባንክ ነው፡፡ ባናካችን የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን አቅም ያገናዘበ ልዩ ልዩ የቁጠባና ብድር አገልግሎቶችን በማቅረብ ተዓማኒነትን ያተረፈ የግል ባንክ ነው፡፡,,,,,,,ቡና ባንክ ! የባለራዕዮች ባንክ!,,,,,

ቡና ባንክ በ3ኛው የ”ይቆጥቡ ይሸለሙ” ፕሮግራም ላይ ለተሳተፉ የዕጣ አሸናፊ መምህራን እና የጤና ባለሙያዎች ሽልማት ሰጠ! Read More »

[ivory-search id="5747" title="Custom Search Form"]

This will close in 0 seconds

error: