የሀዘን መግለጫ
ቡና ባንክ በቀድሞው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ኀዘን እየገለጸ ለመላው ኢትዮጵያውያን ወዳጆቻቸውና የእስልምና እምነት ተከታዮች መጽናናትን ይመኛል! 🪦
ቡና ባንክ በቀድሞው የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝደንት ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ኡመር ኢድሪስ ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ኀዘን እየገለጸ ለመላው ኢትዮጵያውያን ወዳጆቻቸውና የእስልምና እምነት ተከታዮች መጽናናትን ይመኛል! 🪦
አሁኑኑ በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ የቡና ባንክ ቅርንጫፍ በመሄድ ሙሉ መረጃ እና ምክረ ሀሳብ በመውሰድ፤ የአገልግሎታችን ተጠቃሚ ይሁኑ!ለበለጠ መረጃ ወደ ጥሪ ማዕከላችን 8501 ይደዉሉ ቡና ባንክ- የባለራዕዮች ባንክ!
• “ባንኩ ይህንን ፈንድ በማቅረብ ለማህበረሰብ አገልግሎቶች ዕድገት ያለውን • ቁርጠኝነትና አርአያነቱን በተግባር አሳይቷል” ተብሏል ቡና ባንክና ዓለም አቀፉ አኳ ፎር ኦል (Aqua for All) ለ WASH ዘርፍ የተሰጠ በሀገሪቱ የመጀመሪያ የሆነውን የሁለት ሚሊዮን ዩሮ የተዘዋዋሪ ብድር አቅርቦት (Revolving Credit Facility) ስምምነት ይፋ አደረጉ። ስምምነቱ በሂልተን አዲስ ሆቴል መስከረም 22 ቀን 2018 ዓ.ም የተፈረመ ሲሆን ከቡና ባንክ ወገን የባንኩ ቺፍ ስትራተጂና ፓርትነርሺፕ ኦፊሰር አቶ ሙሉነህ አያሌው እንዲሁም ከአኳ ፎር ኦል ወገን ደግሞ የተቋሙ የኢትዮጵያ ተወካይ አቶ ጋሻዬ ቸኮል ፈርመዋል፡፡ ስምምነቱ በኢትዮጵያ የውሃ፣ የንጽህና እና የጤና አጠባበቅ (WASH) አገልግሎቶችን የፋይናንስ ክፍተት በመሙላት ረገድ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ተጠቃሽ እርምጃ ሲሆን የፋይናንስ ድጋፉ ዘላቂ የWASH አገልግሎት ተደራሽነትን ማስፋት ላይ ያተኮረ መሆኑም ተገልጿል። የ1.5 ሚሊዮን ዩሮ የብድር አቅርቦቱ ከቡና ባንክ በተዘዋዋሪ ብድር (Revolving fund) መልክ የቀረበ ካፒታል ሲሆን ቀሪው 500,000 ዩሮ ደግሞ ከአኳ ፎር ኦል (በሆላንድ መንግሥት እና በኮንራድ ኤን. ሂልተን ፋውንዴሽን ድጋፍ) ከተገኘ የሥራ ማስጀመሪያ ካፒታል የተገኘ ነው፡፡ የቡና ባንክ ቺፍ ስትራቴጂና ፓርትነርሽፕ ኦፊሰር አቶ ሙሉነህ አያሌው በመክፈቻ ንግግራቸው “የWASH ዘርፍ ትላልቅ ፈተናዎች እንደሚገጠሙት እንረዳለን፤ በበተለይም ተደራሽነት፣ የአቅም ማነስ እና ዘላቂነት አሁንም መፍትሄ የሚሹ አስቸኳይ ችግሮች ናቸው” ብለዋል፡፡ አቶ ሙሉነህ እንዳሉት እነዚህን ፈተናዎች ለመፍታት አዳዲስ ፈጠራ የታከለባቸው መፍትሔዎች፣ ጠንካራ ትብብሮች እና ዘላቂ የፋይናንስ ሥርዓቶችን መዘርጋት አስፈላጊ ጉዳዮች ናቸው፡፡ የስምምነቱ ፋይዳም ይህንኑ መፍትሄ ወደስራ ማስገባት ነው ብለዋል፡፡ እንደአቶ ሙሉነህ ገለጻ ቡና ባንክ ለWASH ዘርፍ ታስቦ የተዘጋጀ ተዘዋዋሪ ብድር ያቀርባል፤ ይህ ብድር ለማይክሮፋይናንስ ተቋማት ጥቅል ብድሮችን በመስጠት በስሩ ተጠቃሚ የሚሆን እያንዳንዱ ቤተሰብ ተመጣጣኝ የውሃ፣ የንፅህና እና የጤና አገልግሎቶች እንዲያገኙ ያስችላል፣ እንዲሁም ለWASH ዘርፍ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ቀጥተኛ ብድሮችን በማቅረብ መሠረተ ልማቶችን ለማስፋትና አስፈላጊ አገልግሎቶችን ለማሻሻል ይረዳል፡፡ ቡና ባንክ ለዚሁ ዓላማ ታስቦ የተዘጋጀ ፈጠራ የታከለበት የፋይናንስ መፍትሄ በማቅረብ የኢትዮጵያን የውሃ እና የንፅህና ሁኔታ ለማሻሻል ያለውን ጽኑ ቁርጠኝነት አሳይቷል ነው ያሉት አቶ ሙሉነህ ። አቶ ሙሉነህ በንግግራቸው ማጠቃለያ “ ቡና ባንክ የባንክ አገልግሎት ከመስጠት በላይ ማህበረሰቦችን ለማጠናከር፣ የሰዎችን ኑሮ ለማሻሻል እና ለዘላቂ የወደፊት ህይወት መሠረት ለመጣል የለውጥ አነሳሽ ለመሆን ይተጋል፤ ይህ ሞዴል በኢትዮጵያ ውስጥ በፋይናንስ ተቋማት እና የልማት አጋሮች መካከል ሰፊ ትብብርን እንደሚያበረታታ ተስፋ እደርጋለሁ” ብለዋል። በስምምነቱ ላይ ንግግር ያደረጉት የAqua for All የኢትዮጵያ ተወካይ አቶ ጋሻዬ ቸኮል በበኩላቸው ተዘዋዋሪ የብድር አቅርቦት ኢትዮጵያ ለገጠማት የWASH ፈተናዎች መልስ የሚሰጥ መፍትሄ ነው ብለዋል፡፡ “ ይህ ዘላቂ የፋይናንስ ዘዴ ባንኮችን፣ ማይክሮፋይናንስ ተቋማትን፣ ኢንተርፕራይዞችን እና የልማት አጋሮችን በአንድ ላይ በማገናኘት የፋይናንስ ክፍተቱን ለመሙላት ይረዳል” ነው ያሉት አቶ ጋሻዬ፡፡አክለውም “ቡና ባንክ በአገሪቱ ይህን ልዩ የፋይናንስ ድጋፍ በማቅረብ በዘርፉ የመጀመሪያው የፋይናንስ ተቋም ነው፡፡ ባንኩ ይህንን ማድረጉ ለማህበረሰብ አገልግሎቶች ዕድገት ያለውን ቁርጠኝነትና መሪነቱን አጉልቶ ያሳየ አርዓያነት ያለው ተግባር ነው” ብለዋል፡፡ ይህ የብድር ፋሲሊቲ በፕሮጀክት ጊዜው ውስጥ ከ17,500 በላይ ደንበኞች እና 865 አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን ተጠቃሚ በማድረግ፣ ለኢትዮጵያ የWASH ግቦች መሳካት ቀጥተኛ እና ጉልህ አስተዋፅኦ ይኖረዋል። ፈንዱን በማስተዳደር ረገድ ግራንት ቶርተን (Grant Thornton) ኃላፊነቱን የወሰደ ሲሆን፣ የትግበራ አጋሮቹ ደግሞ በኢንተርፕራይዝ እና ፋይናንስ ሥነ-ምህዳር ድጋፍ ልምድ ያላቸው አይስ አዲስ (Ice Addis) እና ፌር ኤንድ ሰስቴይኔብል (Fair & Sustainable) ተቋማት መሆናቸው በስነስርዓቱ ላይ ተገልጿል፡፡ በይፋዊ የማስጀመሪያ መድረኩ ላይ የተገኙ ባለድርሻ አካላት እንደገለጹት በንግድ ፋይናንስ አማካኝነት ለWASH ዘርፍ ድጋፍ በማሰባሰብ ረገድ የኢትዮጵያ ሞዴል በአፍሪካ ቀጠና ሊስፋፋ የሚገባው አሰራር ነው፡፡ በስነስርዓቱ ላይ ከተለያዩ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት የተጋበዙ አንግዶች፣ የአነስተኛ ብድር አቅራቢ ተቋማት ሃላፊዎች፣ የWASH እና አኳ ፎርኦል ሃላፊዎች እና ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
Baga Ayyaana Irreechaa bara 2018 nagaan geessan! Irreechi mallattoo Nagaa, Tokkumaa fi Araaraati. እንኳን ለ 2018 ዓ.ም የኢሬቻ በዓል በሰላም አደረሳችሁ! ኢሬቻ የሰላም፣ የአንድነት እና የይቅርታ ምልክት ነው! Ayyaana Gaarii_መልካም የኢሬቻ በዓል! ቡና ባንክ – የባለራዕዮች ባንክ!
ቡና ባንክ ለመላው ህዝበ ክርስቲያን እንኳን ለብርሀነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላምና የፍቅር እንዲሆንላችሁ ከልብ ይመኛል።መልካም በዓል!ቡና ባንክየባለራዕዮች ባንክ!
በቡና ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ የተመራ ልዑክ ከስራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ጋር ተወያየ በቡና ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ አለማየሁ የተመራ የባንኩ ከፍተኛ የስራ አመራር ልዑክ ከስራና ክህሎት ሚኒስትር ክብርት ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል ጋር በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርጓል፡፡መስከረም 12 ቀን 2018 ዓ.ም በክብርት ሚኒስትሯ ቢሮ በተካሄደው በዚሁ ውይይት ለወጣቶች የስራ ፈጠራ አቅም ግንባታ እንዲሁም የፋይናንስ አካታችነትን ማስፋት በሚቻልባቸው መንገዶችና በቴክኖሎጂ ትብብርና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል፡፡ የውይይቱን መጠናቀቅ ተከትሎ ክብርት ሚኒስትሯ ወይዘሮ ሙፈሪያት ካሚል በይፋዊ የፌስቡክ ገጻቸው ባሰራጩት መረጃ “ከቡና ባንክ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በቅንጅት መስራት በምንችልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ውጤታማ ውይይት አካሂደናል፡፡ በውይይቱ በሥራ ዕድል ፈጠራ ስነ-ምህዳሩ ላይ የዜጎችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየተደረጉ ያሉ የተናጠል ጥረቶችን ተመልክተናል፡፡ በቀጣይም በክህሎት ልማት፣ ሥራ ዕድል ፈጠራ እና ሰላማዊ ኢንዱስትሪ ግንኙነት መስኩን ጨምሮ በጋራ በሚለዩ ስትራቴጂያዊ የትብብር መስኮች ተቀናጅቶ በመስራት ውጤቱን ለማላቅ ተግባብተናል” ብለዋል፡፡ “የቡና ባንክ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ክቡር አቶ ሙሉጌታ አለማየሁ እና የሥራ ባልደረቦቻቸው ከሚኒስቴሩ ጋር ተቀናጅቶ በመስራት የዜጎችን ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ላሳዩት ተነሳሽነትም ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ” ብለዋል፡፡ በውይይቱ ላይ ለባንካችን ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች የሚኒስቴሩን በሰውሰራሽ አስተውህሎት የበለጸገ የሰራተኛ ገበያ መረጃ ስርዓት (Labor market information system) በተመለከተ ክብርት ሚኒስትሯ ሰፋ ያለ ገለጻ አድርገዋል፡፡ የባንካችን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሙሉጌታ አለማየሁ በገለጻው ማጠቃለያ ላይ ባደረጉት ንግግር ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዘርፉን በማዘመንና በቴክኖሎጂ እንዲደገፍ በማድረግ በኩል ያከናወናቸውን ተግባራት አድንቀዋል፡፡ በተጨማሪም ክብርት ሚኒስትሯ በቢሯቸው ለርሳቸውና ለስራ አመራር ቡድኑ ላደረጉት ደማቅ አቀባበል አመስግነው በውይይቱ ወቅት ለቀረቡት ገንቢ ሃሳቦችም አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡ በውይይቱ ላይ የቡና ባንክ ፕሮዳክትና ሰርቪስ ኢኖቬሽን ተጠባባቂ ቺፍ ኦፊሰር አቶ ሰዋለ ቢተው፣ የባንኩ ከወለድ ነጻ የባንክ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መሃመድ ናስር እና የባንኩ ኢንተርናሽናል ባንኪንግ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጠና ሀይለማርያም ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
ቡና ባንክ ከስራና ክህሎት ሚኒስትር ጋር ተወያየ Read More »
ቡና ባንክ ዶ/ር እዮብ ተካልኝ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ ሆነው በመሾማቸው የተሰማውን ከልብ የመነጨ ደስታ ይገልፃል ። በፋይናንስና ኢኮኖሚ ዘርፎች የደረጀ ዕውቀትና የካበተ ልምድ ያላቸው ዶ/ር እዮብ ተካልኝ ወደዚህ ኃላፊነት መምጣታቸው ለሃገራችን የባንክና ፋይናንስ ዘርፍ ዕድገት የላቀ አበርክቶ ሊሆን እንደሚችል ባንካችን በፅኑ ያምናል። ለቀጣዩ የስራ ዘመናቸውም ስኬትን ይመኛል። BunnaBank #Finance #Banking #Economy #NBE #Governor #Visionaries
ዶ/ር እዮብ ተካልኝ – የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዢ Read More »
ቡና ባንክ ደንበኛ ተኮር የሆኑ አሰራሮችን ወደ ዘርፉ በማምጣት እና አገልግሎቱን በማዘመን በደንበኞቹ ዘንድ ተመራጭ ባንክ ለመሆን እየሰራ ይገኛል፡፡ዛሬ መስከረም 05፣2018 ዓ.ም ቡና ባንክ ፣ ቡና ‘ፍሌቨር ‘ ቅርንጫፍ ፥ በቦሌ ሩዋንዳ ዋናው መስሪያ ቤት በይፋ በመክፈት ስራ አስጀምሯል፡፡ አገልግሎቱ ዘመናዊ እና የዲጅታል አገልግሎት መስጪያ መሳሪያዎችን በመጠቀም ለደንበኞች ቀላል፣ እና ፈጣን የባንክ አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ነው፡፡ ይህ የአሰራር ማሻሻያ የደንበኞቻችንን የባንክ አገልግሎት እርካታ ለማሳደግ የተዘረጋ እና ባንካችን በዘርፉ ያለውን ተወዳዳሪነት ከፍ ለማድረግ ታቅዶ ወደ ተግባር የተቀየረ የአሰራር ስርዓት ነው፡፡ በቡና ‘ፍሌቨር’ ቅርናጫፍ ፣ የባንኩ ደንበኞች የፋይናንስ ምክረ ሃሳብ ለማግኘት እና ውይይት ለማከናውን የሚያስችላቸው ምቹ ሁኔታንም አመቻችቷል። ቡና ባንክ ከዚህ ጋር በተያያዘ በስድስት ማእከላት የአይ ቲ ኤም (ITM) አገልግሎት መስጥት መጀመሩን ይፋ አድርጓል፡፡ ማእከላቱ በቦሌ መድሃኒዓለም- ገልፍ አዚዝ ህንጻ፣ በኦሎምፒያ – ኦሜዳድ ሕንፃ ፣ላጋር- ኢትዮጵያ መድሕን ድርጅት፣ አራት ኪሎ ስላሴ – ስላሴ መንፈሳዊ ኮሌጅ ሕንጻ፣ ብስራተ ገብርዔል- አፍሪካ ኢንሹራስ ሕንጻ እና በባንካችን ዋናው መስሪያቤት ቦሌ ሩዋንዳ ተመርቀው ስራ ጀምረዋል፡፡ ኑ ቡና ጠጡ!ቡና ባንክ- የባለራዕዮች ባንክ! Bunna Bank Brews Up a New Banking Experience Bunna Bank S.C. has today announced the launch of its innovative “Bunna Flavor” branch model, a groundbreaking concept that fuses the traditional hospitality of Ethiopian coffee culture with the seamless efficiency of digital banking. The new branch is a testament to the bank’s commitment to being both a financial pioneer and a community-centric institution. The “Bunna Flavor” branch model reimagines the banking experience by creating an environment where a simple transaction can become a personal connection. Instead of cold counters and long queues, the branch offers a welcoming, communal vibe reminiscent of a traditional coffee ceremony, or “bunna.” This approach aims to make banking feel more accessible and comfortable, building trust and rapport with customers. At the heart of this new concept is a suite of advanced, hassle-free paperless digital banking services that streamline everything from deposits to transfers using ITM, ATM and other digital banking fixtures. This modern technology is complemented by a team of dedicated experts. The branch features a financial advisor to provide personalized investment guidance for individual clients and a private corporate consultation room for businesses seeking strategic financial solutions. “Customer centricity is at the core of our banking business; and we believe banking should be a relationship, not just a transaction,” said Ato Lewutie Tirusew, Chief Finance and Corporate Service Officer of the Bank. “The ‘Bunna Flavor Branch’ embodies this philosophy. It’s a place where you can grab a cup of coffee and have a meaningful conversation about your financial future, all while enjoying the speed and convenience of the latest technology. It’s the perfect blend of tradition and innovation.”The unveiling of the “Bunna Flavor Branch model” marks a significant milestone in Bunna Bank’s journey to be among the leaders of the digital transformation of Ethiopia’s financial sector, proving that modernization and cultural heritage can go hand-in-hand. Furthermore, the bank disclosed that it aims to expand this model in an extensive manner to other branches following customers’ feedback and reaction.
ኑ ቡና ደርሷል! ቡና ባንክ በአዲስ አቀራረብ ለደንበኞቹ አገልግሎት መስጠት ጀመረ! Read More »
Message from the CEO – 2018 Ethiopian New Year As we welcome the Ethiopian New Year 2018 E.C., Bunna Bank extends its heartfelt wishes for peace, prosperity, and progress to all our customers, partners, and other stakeholders. This moment is more than a celebration of a new beginning—it is a reaffirmation of our enduring commitment to those who walk this journey with us. The past year marked a period of meaningful transformation. With your trust and collaboration, Bunna Bank reinforced its foundation, modernized its services, and broadened its reach. Together, we achieved significant milestones—introducing advanced digital platforms that make banking more accessible, launching inclusive financial products tailored to diverse needs, and investing in the growth of our people. Each step forward reflects our shared pursuit of excellence and our belief that progress is most powerful when it is shared. As we enter this new year, we do so with clarity and conviction. Ethiopia’s financial landscape is evolving rapidly, shaped by global competition, technological innovation, and bold reforms such as the launch of the national capital market. Bunna Bank is prepared—not only with resilient systems and forward-looking strategies, but with a deep understanding of the communities we serve and a steadfast commitment to inclusive growth. Our focus for 2018 E.C. is to strengthen relationships, deliver tailored financial solutions, and expand access to banking services across all segments of society. We are investing in scalable infrastructure, enhancing our risk management capabilities, and fostering a culture of responsiveness and innovation. These efforts are designed not only to meet today’s needs, but to anticipate tomorrow’s opportunities. At Bunna Bank, we see every relationship not as a transaction, but as a partnership built on trust, purpose, and shared ambition. In the year ahead, we will continue to listen, adapt, and grow—together. Our promise is simple: to be your trusted financial ally, a catalyst for opportunity, and a committed partner in your success. Thank you for your continued confidence in Bunna Bank. The future is bright—and we are honored to build it with you. Mulugeta Alemayehu Chief Executive Officer Bunna Bank
A New Year, A Shared Vision: Building the Future Together Read More »
ቡና ባንክ ለመላው ኢትዮጵያውያን እንኳን ለ2018 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ፣ አደረሰን! እያለ መጪው ዓመት በሀገራችን የሰላም፣ የፍቅርና የስኬት ዘመን እንዲሆንልን ከልብ ይመኛል። የአቦል ዲጂታል ባንኪንግ አማራጮችን በመጠቀም በዓሉን በደስታ ያሳልፉ። ቡና ባንክ – የባለራዕዮች ባንክ!
This will close in 0 seconds
አካውንት ይክፈቱ የክፍያ ካርድዎን ያዝዙ ፣ ፈጣን አገልግሎት ማግኘት ይጀምሩ! ዛሬውኑ ይቀላቀሉን!
Open Bunna AccountYou cannot copy content of this page