መልካም የመውሊድ በዓል!
እንኳን ለ1450ኛው የመውሊድ በዓል በሰላም አደረሳችሁ!! መውሊድ አል-ነቢ!
ማለዳ፣ መነሻ፣ ራዕይ እና ንጋት ባንካችን ለናንተ ለክቡራን ደንበኞቹ ካዘጋጃቸው የዲጂታል ብድር አይነቶች ውስጥ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ እነዚህ የብድር አይነቶች መደበኛ እና ኢመደበኛ ንግድ ላይ የተሰማሩ ማንኛውም የማህበረሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ያደርጋሉ፡፡ ደንበኞች የሚጠበቅባቸውን መረጃዎች ብቻ አሟልተው ሲመጡ ወዲያውኑ እስከ 100 ሺ ብር ብድር ከባንካችን ማግኘት ይችላሉ ፡፡አሁኑኑ በአቅራቢያዎት ወደሚገኝ የቡና ባንክ ቅርንጫፍ ይሂዱ፤ የአገልግሎታችን የተሟላ ዝርዝር መረጃ በማግኘት ተጠቃሚ ይሁኑ!ለበለጠ መረጃ ወደ ጥሪ ማዕከላችን 8501 ይደዉሉ ! አቦል ላይ ይድረሱ! ቡና ባንክ- የባለራዕዮች ባንክ
ያለምንም ማስያዣ እስከመቶ ሺ ብር ልናበድርዎ ነው! Read More »
ቡና ባንክ ከአዲስ አበባ ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር፣ በኢትዮጵያ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር ማዕቀፍ ውስጥ “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል የችግኝ ተከላና የአካባቢ ጥበቃ ተግባራትን በልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 በጎነት የመኖሪያ መንደር አካሄደ። ኢትዮጵያ የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከልና የአረንጓዴ ልማትን ለማስፋፋት በየዓመቱ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብሮችን ታከናውናለች። በዚህ አገር አቀፍ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር ማዕቀፍ ውስጥ፣ ቡና ባንክ በበኩሉ ለምግብነት የሚውሉ የቦካዶ እና የዘይቱና ችግኞችን በመትከል የከተማዋን ውበት ለማሳደግ፣ የአየር ንብረት ለውጥ ተጽዕኖን ለመቋቋምና ዘላቂ ልማትን ለማስፈን የሚደረገውን አገር አቀፍ ጥረት የሚያግዝ ተግባር አከናውኗል። ይህ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር የተፈጥሮ- አካባቢን ውበት በመጠበቅ፣ ለነዋሪዎች ጤና ተስማሚ የሆነ አካባቢ ለመፍጠር እየተደረገ ያለውን ጥረት የሚያግዝ ነው ሲል ባንኩ ገልጿል። ባንኩ በዚህ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር መሳተፉ፣ በፋይናንስ ዘርፍ ካለው ቀዳሚ ሚና ባሻገር፣ ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ረገድ ለማህበረሰብ ልማትና ለአካባቢ ጥበቃ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳየ ተግባር ነው። ስለሆነም የአረንጓዴ አሻራ መርሀ-ግብር የኢትዮጵያን ዘላቂ ልማት ለማሳካት ወሳኝ መሆኑን ግምት ውስጥ በማስገባት ቡና ባንክ ይህን ተግባር በመደገፍ ለአካባቢ ጥበቃና ለማህበረሰብ ልማት ያለውን ኃላፊነት እየተወጣ ይገኛል። ባንኩ የኢትዮጵያን የአረንጓዴ ልማት ራዕይ እውን ለማድረግ በሚደረገው አገር-አቀፍ ጥረት ውስጥ በተመሳሳይ መርሀ-ግብሮች ተሳትፎውን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስታውቋል። ይህ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር ለማህበረሰባችን ኑሮ ተስማሚ አካባቢን ለመፍጠርና የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የምናደርገው የጋራ ጥረት መገለጫ ነው ያለው ባንኩ በቀጣይም የልደታ ክፍለ ከተማ ውበትና አረንጓዴ ልማት ጽ/ቤትን ጨምሮ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በመተባበር ሌሎች የችግኝ ተከላና የአካባቢ ጥበቃ መርሀ-ግብሮች ላይ ለመሳተፍ ዝግጁነቱን ገልጿል። ነሃሴ 08 ቀን 2017 ዓ.ም. በቡና ባንክ ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽንና ፕሮሞሽን
ቡና ባንክ በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ-ግብር አካሄደ፡፡ Read More »
ቡና ባንክ በአቦል ሞባይል ባንኪንግ ዲጂታል የነዳጅ ክፍያ አገልግሎት መስጠት ጀመረ ቡና ባንክ በኢትዮጵያ የፋይናንስ እና ቴክኖሎጂ እድገት ጉልህ እርምጃ ያለውን አዲስ የዲጂታል ነዳጅ ክፍያ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ። ከትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር የተቀረጸው አገልግሎቱ ከብሔራዊ የነዳጅ ስርጭት መከታተያ ስርዓት ጋር በመቀናጀት በአገር አቀፍ ደረጃ የነዳጅ አቅርቦት ሰንሰለትን ግልፅነት እና ቅልጥፍና ለማሻሻል የሚያስችል ዘመናዊ የክፍያ አማራጭ ነው ። ይህ ኢኒሼቲቭ በየጊዜው ተለዋዋጭና ፈጣን ለሆነው የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ፍላጎት ምላሽ በመስጠት ረገድ ለደንበኞች አስተማማኝ እና ፈጣን የነዳጅ ክፍያ አማራጭን ይዞ የቀረበ አገልግሎት ነው፤ ይህም አገልግሎት ጥሬ ገንዘብ ከመያዝ ጋር የተያያዙ ስጋቶች፣ ግልጽ ያልሆነ ግብይት እና በነዳጅ ማደያዎች ውስጥ የሚስተዋሉ ረጃጅም ወረፋዎችን የመሳሰሉ ተግዳሮቶችን ለመፍታት እየተደረጉ ያሉ ጥረቶችን የሚያግዝ ነው። ስለሆነም ይህ የዲጂታል ክፍያ አገልግሎት መጀመሩ ቡና ባንክ በቴክኖሎጂ የተደገፈ የባንክ አገልግሎት ከባቢያዊ ሁኔታን ለመደገፍ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል። ደንበኞች ቡና ባንክን ተጠቅመዉ የነዳጅ ግዢን መፈጸም የሚችሉት፤ ከነዳጅ ማደያዉ *820# በመጠቀም ስልካቸዉ ላይ በሚደርሳቸዉ የማረጋገጫ መልእክት፣ አቦል የሞባይል ባንኪንግ መተግበሪያ ዉስጥ በመግባት QR ኮድን ተጠቅሞ ስካን በማድረግ ወይም በነዳጅ ማደያው የቀረበውን የማጣቀሻ ቁጥር (Reference Number system) በመጠቀም ነው። ይህ ባለብዙ አማራጭ ዲጂታል ፕላትፎርም በማንኛውም አይነት ሞባይል ስልክ እንዲሁም በኢንተርኔት ወይንም ያለኢንተርኔት በመላው ኢትዮጵያ ለሚገኙ ሁሉም ደንበኞች ሰፊና ተደራሽ አገልግሎት ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል። አገልግሎቱ የተሻሻለ የክፍያ አማራጭን በማቅረብ የአሽከርካሪዎችን ፍላጎት ያሟላ ሲሆን ለነዳጅ ማደያዎች ደግሞ ስራቸውን ፈጣንና ቀልጣፋ እንዲሆን ያግዛቸዋል፤ በተጨማሪም የመንግስት አካላትን የቁጥጥር ስርዓት በማሻሻል ረገድ የበኩሉን አስተዋጽኦ ያበረክታል ተብሎ ይጠበቃል። ባንኩ በተወሰኑ የተመረጡ የነዳጅ ማደያዎች የጀመረውን ይህን አገልግሎት በመላ ሀገሪቱ ከሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ጋር በመተባበር ለማስፋፋት አቅዷል፡፡ ቡና ባንክ የኢትዮጵያን የባንክ መሠረተ ልማት የማዘመን እና አስፈላጊ አገልግሎቶችን ዲጂታል የማድረግ ብሔራዊ ጥረቶችን ለመደገፍ ተልእኮውን አንግቦ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል። ከዚህ ጋር ተያይዞ ባንኩ ከዲጂታል ነዳጅ ክፍያ በተጨማሪ በመላ አገሪቱ ቀልጣፋ እና ተደራሽ አገልግሎትን በስፋት ለማቅረብ ለያዘው ዕቅድ ደህንነታቸው የተጠበቀ እና እየሰፉ የሚሄዱ የተለያዩ የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎቶች ላይ ኢንቨስት ማድረጉን ቀጥሏል። ደንበኞች የነዳጅ ክፍያ አገልግሎቱን ለመጠቀም በቅድሚያ የቡና ባንክ ሞባይል ባንኪንግ አገልግሎትን መመዝገብ ያለባቸዉ ሲሆን በመቀጠል በመረጡት አማራጭ ክፍያቸዉን መፈፀም ይችላሉ፡፡ ደንበኞች ለተጨማሪ መረጃ 8501 ላይ በመደወል የደንበኞች አገልግሎት ሰራተኞችን ማነጋገርና መረጃ ማግኘት ይችላሉ። ቡና ባንክ ከ14ሺህ በላይ የሚሆኑ ባለአክሲዮኖች ያሉት ከ15 ዓመታት በፊት የተቋቋመና 454 በሚሆኑ ቅርንጫፎቹ በኢትዮጵያ ሁሉም ክልሎች አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኝ የባለራዕዮች ባንክ ነው፡፡ ባንካችን የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን አቅም ያገናዘበ ልዩ ልዩ የቁጠባና ብድር አገልግሎቶችን በማቅረብ ተዓማኒነትን አትርፏል፡፡ ሐምሌ 21-2017 በቡና ባንክ ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽንና ፕሮሞሽን ዋና ክፍል የተዘጋጀ
ጋዜጣዊ መግለጫ |Press release Read More »
ቡና ባንክ ለእናንተ ለውድ ቤተሰቦቻችን የደሞዝ መዳረሻ ብድር እና የዲጂታል ቁጠባ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንገኛለን። 💸🫰አቦል ደሞዜ የደሞዝ መዳረሻ ብድርን ለማግኘት የካቻ መተግበሪያን ከGoogle Play ወይም ከApp Store በማውረድ በባንካችን በኩል እንደደሞዝዎ መጠን በፐርሰንት መርጠው መበደር ይችላሉ።🤑💰ደሞዝ ደርሷል! 💲💲💲ሙሉ መረጃውን ለማግኘት በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ ቅርንጫፍ ይሂዱ ወይም ወደ 8501 ይደውሉ።ቡና ባንክየባለራዕዮች ባንክ!ይፍጠኑ አሁኑኑ ይሞክሩት 👇For Android (https://play.google.com/store/apps/details…)For Iphone (https://apps.apple.com/us/app/kacha-customer/id6449651203) BunnaBank#kacha #CustomerFirst #Testimony #DigitalFinance #EthiopianBanks
ቡና ባንክ የዲያስፖራ ማህበረሰቦች በኢትዮጵያ እድገት ውስጥ ለሚጫወቱት ጉልህ ሚና ትልቅ ቦታ ይሰጣል፤ ገንዘብ ወደ ቤተሰብ እየላኩ ወይም ሀብትዎን ለማሳደግ ዘመናዊ የገንዘብ መላኪያ መንገዶችን ከፈለጉ፣ የቡና ዲያስፖራ አካውንት ለወዳጅ ዘመዶችዎና ለማህበረሰብዎ ኑሮ መሻሻል ብሎም ለኢትዮጵያ ዕድገት እውነተኛ ተፅእኖ እንዲፈጥሩ ያግዝዎታል።🌍 ቀላል እና አዋጪ የገንዘብ ልውውጦችገንዘብ ከውጭ አገር ወደ አገር ቤት መላክ በኢትዮጵያ ውስጥ ትምህርትና የጤና እንክብካቤን ለማሻሻል እና የአነስተኛ ንግዶችን ዕድገት ለማገዝ ይረዳል። እ.ኤ.አ. በ 2023 በኢትዮጵያ ከውጭ ወደ ሀገር ውስጥ የተላከው ገንዘብ በ16 በመቶ ከፍ ያለ ዕድገት ያስመዘገበ ሲሆን ይህም የዲያስፖራ ቤተሰብ አባላትን ለመርዳት ብሎም ኢኮኖሚውን ለማሳደግ የማይናቅ ሚና ነበረው።በቡና ዲያስፖራ አካውንት ገንዘብ መላክ ቀላል፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ወጪ ቆጣቢ ነው፤ ባንካችን የሚያቀርበው ተመጣጣኝ የምንዛሪ ዋጋ ተመን እና ዝቅተኛ የአገልግሎት ክፍያ የሚልኩት ገንዘብ ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ ለቤተሰብዎ እንዲደርስ ወይንም ለሚፈልጉት ዓላማ እንዲዉል ያግዛል፤ በአለም ላይ ከየትኛውም ቦታ ሆነው ገንዘብ ለመላክ ሲያስቡ የባንካችንን ቀላል የሞባይል እና የኦንላይን የባንክ አገልግሎት አማራጮች ይጠቀሙ።💼 ዘመናዊ የፋይናንስ መገልገያ ዘዴዎች ለዲያስፖራ ባለሀብቶችከውጭ አገር ወደ አገር ውስጥ ገንዘብ ከመላክ በተጨማሪ የቡና ዳያስፖራ አካውንቶች ለኢትዮጵያ ልማት አስተዋፅዖ እያደረጉ ሀብትዎን እንዲያሳድጉ የሚያግዝ አስተማማኝ የፋይናንስ አገልግሎት ይሰጥዎታል፡- 🔑 ቡና ዲያስፖራ አካውንትን ለምን ይመርጡታል? From Remittances to Investments: Why Bunna Diaspora Accounts Are Made for Impact At Bunna Bank, we celebrate the vital role diaspora communities play in shaping Ethiopia’s future. Whether you’re sending remittances to support loved ones or exploring smart financial opportunities, Bunna Diaspora Accounts empower you to create lasting impact—for your family, your community, and Ethiopia’s growth.🌍 How Bunna Diaspora Accounts Simplify RemittancesRemittances are lifelines for millions of Ethiopians abroad, fueling education, healthcare, and small businesses back home. In 2023, global remittance flows to low- and middle-income countries reached $669 billion, with Ethiopia experiencing a 16% increase in inflows, reinforcing economic resilience.Bunna Diaspora Accounts make remittances simple, secure, and cost-effective. With competitive exchange rates and low fees, more of your money reaches those who need it most. Our intuitive digital platforms—accessible via mobile and online banking—enable effortless transfers, no matter where you are in the world.💼 Smart Financial Tools for Diaspora InvestorsBeyond remittances, Bunna Diaspora Accounts give you access to verified financial services that help grow your wealth while contributing to Ethiopia’s development:
ከሬሚታንስ እስከ ኢንቨስትመንት፡ የቡና ዲያስፖራ አካውንት ተጽዕኖ ምን ይመስላል? Read More »
ዘመናዊ የክፍያ አማራጭ ለዘመናዊ ጉዞ ዛሬ ሁሉ ነገር ፈጣንና ተለዋዋጭ በሆነባት ዓለማችን፣ ጊዜ እና ምቾት ከምንግዚ በላይ ወሳኝ ጉዳዮች ናቸው! ስለሆነም ቡና ባንክ የተሽከራካሪ ጉዞዎን ለማስቀጠል ከጎንዎ አለሁ ይላል። ባንካችን ያቀረበው ዲጂታል የነዳጅ ክፍያ አማራጭ ነዳጅ ሲቀዱ ያለውን ወረፋ ፈጣን፣ ቀላል እና ከጭንቀት ነጻ ለማድረግ ታስቦ የተነደፈ መላ ነው። ⚙️ የአገልግሎቱ ዋና ጥቅሞች የባንካችን የክፍያ አማራጭ ለእርስዎ ምቹና ተስማሚ የሆኑ ዲጂታል የክፍያ መንገዶችን በመጠቀም በቡና ባንክ ሂሳብዎ በቀጥታ የነዳጅ ክፍያዎን እንዲፈጽሙ ያስችልዎታል። ወደ ሥራ እየተጓዙም ሆነ ከአንድ ቦታ ወደ ሌላ ቦታ ለመጓዝ፣ ይህ የነዳጅ ክፍያ አገልግሎት ሕይወትዎን ለማቅለል የተዘጋጀ አማራጭ ነው። አገልግሎቱን ልዩ የሚያደርገው ፡- 🔄 ፈጣን እና ቀላል ለክፍያ መጉላላትን በማስቀረት በሰከንዶች ውስጥ በስልክዎ ወይም በቡና ባንክ መተግበሪያ ለመክፈል ስለሚያስችል፤ 📍 በአቅራቢያዎ ስለሚገኝ ከባንካችን ጋር አጋርነት ባላቸው ሁሉም የነዳጅ ማደያዎች ተቀባይነት ያለው በመሆኑ፤ 🔐 ደህንነቱ የተረጋገጠ የግብይትዎን ደህንነት ለመጠበቅ በባንካችን አስተማማኝ የደህንነት መጠበቂያ ጥብቅ ክትትል ስለሚደረግ፤ 📲 በእንቅስቃሴ ያልተገደበ ከቡና ባንክ ሂሳብዎ ጋር በቀጥታ የተገናኘ በመሆኑ ክፍያዎችን በማንኛውም ጊዜ እና ቦታ ለማስተዳደር ቀላል ያደርገዋል።ያለምንም ችግር ጉዞዎን ይቀጥሉ 🚀 ያለምንም ችግር ጉዞዎን ይቀጥሉ የቡና ባንክ የነዳጅ ክፍያ አማራጭ ከመክፈያ ዘዴም በላይ ያለማቋረጥ ከቦታ ወደ ቦታ የመንቀሳቀስ ነፃነትን የሚሰጥ የክፍያ ዘዴ ጭምር ነው። በተጨናነቀ የጉዞ መርሐግብር ላይ እየተዘዋወሩም ሆነ የመንገድ ላይ ጉዞ ለማድረግ እያቀዱ ከሆነ ይህ አገልግሎት ነዳጅ መሙላትን እጅግ ፈጣን፣ ምቹ እና ከአኗኗር ዘይቤዎ ጋር የተስማማ እንዲሆን ይረዳዎታል። 👉 አሁኑኑ የቡና ባንክ መተግበሪያን ያውርዱ፡ https://play.google.com/store/apps/details?id=com.bunnabanksc.bunnamobile&hl=en#ቡናባንክ #ነዳጅክፍያ #ዲጂታልባንኪንግ #ብልህመንገድ 🚗 Fuel Up Smarter with Bunna Bank’s Digital Fuel Payment Modern Banking for Modern Movement In today’s fast-moving world, time and convenience matter. That’s why Bunna Bank offers a digital fuel payment option that helps you refuel faster, easier, and more securely. ⚙️ Key Benefits of Our Fuel Payment Option 🔄 Fast and Simple Pay for fuel in seconds using your mobile phone or Bunna’s banking app. 📍 Widely Available Accepted at all Bunna Bank–partnered fuel stations across the country. 🔐 Secure and Reliable Built with trusted security protocols to keep every transaction safe. 📲 Integrated Flexibility Pay anytime, anywhere—directly from your Bunna Bank account. 🚗 Drive Your Way, Hassle-Free The Bunna Fuel Payment option is more than just a transaction—it’s freedom on the go. Whether you’re commuting, delivering, or traveling, this service saves time and fits right into your daily routine. 👉 download the Bunna Bank App to get started today: https://play.google.com/store/apps/details?id=com.bunnabanksc.bunnamobile&hl=enStay ahead with Bunna. 🚗💨 #BunnaBank #FuelSmarter #DigitalBankingMadeEasy #ScanAndGo
🚗 ነዳጅ ለመቅዳት ብልህ መላ፡ የቡና ባንክ ዲጂታል የነዳጅ ክፍያ አማራጭ Read More »
Entering a New Fiscal Year with Purpose and Progress “As we begin a new fiscal year, I want to thank all our customers, staff, and partners for your trust and continued support. Over the past year, Bunna Bank has grown stronger—expanding access, embracing digital solutions, and reinforcing our commitment to inclusive banking. We’ve made solid progress, and we’re just getting started. This year, we’re focused on doing more: driving innovation, deepening customer experience, and growing sustainably. Our vision remains clear—to build a modern, accessible, and people-first bank for all Ethiopians, as stated “To be one of the top three financial service providers by the year 2030”. Let’s keep building together.” Mulugeta Alemayehu CEO
Strategic Outlook for the 2025/26 Fiscal Year Read More »
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ለባንካችን የዲጂታል ፋይናንስ ሰርቪስ የሰጠውን የሙከራ ፈቃድ ጨርሰን ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት የሚያስችለንን የንግድ ስራ ፈቃድ | Business Trade License ማግኘታችንን ስንገልፅ በታላቅ ደስታ ነው፡፡ክቡራን ደንበኞቻችን ባንካችን ብዙሃን የማህበረሰብ ክፍሎችን ያማከለ የዲጂታል ብድር በመላው ኢትዮጵያ እየሰጠ በመሆኑ በተለይም በአነስተኛ እና ጥቃቅን ንግድ ላይ የተሰማሩ ሴቶችን በግብርና ስራ ላይ የተሰማሩ የማህበረሰብ ክፍሎችን እንዲሁም አነስተኛ ገቢ ያላቸው ግለሰቦችን ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ ይገኛል፡፡እርስዎም ዛሬውኑ አቦል አፕሊኬሽንን በማውረድ አልያም ወደሚቀርብዎ የባንኩ ቅርንጫፍ በመሄድ የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ይሁኑ፡፡አቦል ላይ ይድረሱ!#AbolDigitalFinance #BunnaBank #Visionaries #Ethiopia #MSME #Entrepreneurs
እንኳን ደስ አላችሁ! እንኳን ደስ አለን! Read More »
👏👏👏👏እንኳን ደስ አላችሁ👌ቡና ባንክ የናሽናል QR አገልግሎትን መስጠት ጀመረ፡፡ በሀገራችን ከሚገኙ ከሁሉም ባንኮች የቡና ባንክ QR ኮድን ስካን በማድረግ ብቻ በቀላሉ ክፍያዎትን ይቀበሉ፡፡ ግለሰቦች እና ድርጅቶች አሁኑኑ የአገልግሎታችን ተጠቃሚ በመሆን ለደንበኞቻችሁ ምቹ፤አስተማማኝ እና ቀልጣፋ የክፍያ ስርአትን ይዘርጉ፡፡ 🌐 Introducing the National QR Code Payment Service Accept Payments from All Banks in Ethiopia — Instantly and Securely! Say goodbye to limitations and hello to nationwide possibilities! With the National QR Code Service, businesses and individuals can now receive payments from any bank across Ethiopia with a simple scan. ለበለጠ መረጃ ወደ 8501 ይደዉሉ BunnaBank#ScanAndPay#NationalQR#RecivePayment#Merchant
National QR Code Payment Read More »
This will close in 0 seconds
አካውንት ይክፈቱ የክፍያ ካርድዎን ያዝዙ ፣ ፈጣን አገልግሎት ማግኘት ይጀምሩ! ዛሬውኑ ይቀላቀሉን!
Open Bunna AccountYou cannot copy content of this page