Bunna Bank

Solomon mekbib

የነዳጅ ክፍያን በቀላሉ

🚗💨 የምስራች!በቡና ባንክ አቦል ሞባይል ባንኪንግ የነዳጅ ክፍያ ተጀመረ!አሁኑኑ መተግበሪያውን አውርደው በቅጽበት ይክፈሉ፡፡ ⛽️📱🔥 Fuel payment? Done in seconds with Abol Mobile Banking!No more long lines, no more cash.Just tap, pay, and go! 🕶💳👉 Download now:https://play.google.com/store/apps/details?id=com.bunnabanksc.bunnamobile&pcampaignid=web_share AbolMobile #BunnaBank #DigitalFuelPay #NoMoreLines #CashlessEthiopia #SmartBanking #FintechEthiopia #ነዳጅበአቦል #ቀላልክፍያ #አንድለመንገድ #አዲስአማራጭ

የነዳጅ ክፍያን በቀላሉ Read More »

ቡና ባንክ ቄራ ቅርንጫፍ የተከፈተበትን 8ኛ አመት አከበረ

ግንቦት 12 ቀን 2017 ዓ.ም፤ የቡና ባንክ ቄራ ቅርንጫፍ የተመሰረተበትን 8ኛ አመት በአል በደማቅ ዝግጅት አክብሮ ዉሏል፡፡ በዝግጅቱ ላይ የቅርንጫፉ ደንበኞች፤ የዲስትሪክት ሀላፊዎች፤ የቅርንጫፍ ሰራተኞች እንዲሁም ከዚህ በፊት በቅርንጫፉ ይሰሩ የነበሩ ሰራተኞች ተሳትፈዉበታል፡፡በዝግጅቱ ላይ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክትን ያስተላለፉት የቄራ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ አደስ በየነ ፤ በንግግራቸዉ ፕሮግራሙ ላይ ተሳታፊ ለሆኑ ሁሉ ላቅ ያለ ምስጋናቸዉን አቅርበዋል፡፡ ለቄራ ቅርንጫፍ ስኬታማ መሆን ቁልፍ ምክንያቱ በሰራተኞች መካከል ያለዉ መልካም ግንኙነት እንደሆነ ገልፀዉ፤ በዝግጅቱ ላይ ለነበሩ የቄራ ቅርንጫፍ ሰራተኞችና የረጅም ጊዜ ደንበኞች ላላቸዉ መልካም ግንኙነት ከፍተኛ ክብር እና ምስጋና አቅርበዋል፡፡በበአሉ መጨረሻ ላይ ንግግር ያደረጉት አቶ መልሰዉ አጉመስ፤ የደቡብ አዲስ አበባ ዲስትክት የባንክ ቢዝነስ ክፍል ኃላፊ(manager-south addis ababa bank business division)፤ ለቄራ ቅርንጫፍ ሰራኞች የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን ፤ እንደዚህ አይነት ዝግጅቶች ለሌሎች ቅርንጫፎች ተምሳሌት ሊሆኑ እንደሚገባ መልክታቸዉን አስተላልፈዋል፡፡

ቡና ባንክ ቄራ ቅርንጫፍ የተከፈተበትን 8ኛ አመት አከበረ Read More »

ቡና ባንክ አ.ማ የ ISO/IEC 27001፡2022 ሰርተፍኬት አገኘ

ቡና ባንክ አክስዮን ማህበር የኢንፎርሜሽን ደህንነት አስተዳደር ሲስተምስ (አይኤስኤምኤስ) ስታንዳርድ የሆነውን የISO/IEC 27001፡2022 ስታንዳርድ በተሟላ ሁኔታ በማሳካት ሰርተፍኬት ማግኘቱን ይፋ አድርጓል።ይህ በዓለም-አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ያለው ሰርቲፊኬሽን ባንኩ ያሉትን መረጃዎች ለመጠበቅ እና የደንበኞቹን እና የባለድርሻ አካላትን የመረጃ ደህንነት ደረጃውን በጠበቀ አሰራር ደህንነታቸውን ለማረጋገጥ ያለውን የማያወላውል ቁርጠኝነት ያሳያል ተብሏል። የ ISO/IEC 27001፡2022 የምስክር ወረቀት በዓለም አቀፍ ደረጃ ለመረጃ ደህንነት አስተዳደር መለኪያ ሆኖ የሚያገለግል የተመሰከረለት ሰርቲፊኬት መሆኑ ይታወቃል። ቡና ባንክ አ.ማ ይህንን የደህንነት ማረጋገጫ ሰርተፊኬት ማሳካት በመቻሉ ከሳይበር አደጋዎች የሚከላከሉ ጠንካራ የደህንነት ቁጥጥሮችን ተግባራዊ ለማድረግ ያለውን አቅምና ፍላጎት ያሳየ መሆኑ ተገልጿል። የቡና ባንክ አ.ማ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ሙሉጌታ አለማየሁ ሰርቲፊኬቱን ሲቀበሉ እንደተናገሩት “ይህን የምስክር ወረቀት በማግኘታችን በጣም ተደስተናል፤ ይህ ፕሮጀክት የባንክ መረጃዎቻችንን ደህንነት የማስጠበቅ እርምጃዎቻችንን በቀጣይነት በማጎልበት የደንበኞቻችንን እምነት አስጠብቆ ለመቀጠል ያለንን ቁርጠኝነት ያንፀባርቃል፤ ይህም ስኬታማ አፈጻጸም የቡድናችንን ጥረት እና ትጋት የሚያሳይ ነው። የባንክ ቢዝነስ ስራ ውጤት እና የአይቲ ደህንነት የአንድ ሳንቲም ሁለት ገፅታዎች በመሆናቸው ይህንን ሰርተፊኬት ማግኘታችን ትልቅ ስኬት ነው ” ብለዋል፡፡ ሰርቲፊኬሽን የሰጠው ሰርቲ-ትረስት ድርጅት ማኔጂንግ ዳይሬክተር ማይክ ካማው በበኩላቸው በፕሮግራሙ ላይ እንደተናገሩት ቡና ባናክ የሚጠበቅበትን ሁሉንም የሴኪዩሪቲ መስፈርቶች መቶ በመቶ ያሟላ የመጀመሪያው ተቋም ነው ያሉ ሲሆን ይህም ባንኩ ለኢንፎርሜሽን ሴኩዩሪቲ ማኔጅመንት ሲስተም የሰጠውን ልዩ ትኩረት የሚያሳይ አስደናቂ ስኬት ነው ብለዋል፡፡ አክለውም ባንኩ የባለራዕዮች ባንክ እንደመሆኑ ራዕዩን በዕውን እየተገበረ መሆኑን በግልጽ መናገር ይቻላል ብለዋል፡፡  ይህ አድካሚ የሰርተፊኬሽን ሂደት በርካታ የባንኩን የደህንነት ቁጥጥር ዘዴዎች ማለትም ተቋማዊ፣ ቴክኒካል፣ የአይቲ መሰረተ-ልማትና አስተዳደራዊ ቁጥጥር እና አሠራሮችን አጠቃላይ ግምገማ ያካተተ ነበር። የኦዲት ስራው የተከናወነው ገለልተኛ በሆነ ሰርቲፊኬሽን ሰጪ ድርጅት ሲሆን በስራውም ገለልተኛና የላቀ ሙያዊ አቅሙን በመጠቀም የባንኩን አሰራር እንዲገመግም ተደርጓል፡፡ በተሳካ ሁኔታ የተከናወነው ሰርቲፊኬሽን የቡና ባንክ አክሲዮን ማህበር የመረጃ ደህንነትን በተመለከተ ያለውን ቀድሞ በማሰብ ተገቢውን የጥንቃቄ እርምጃ የመውሰድ አካሄድ እና ሊከሰቱ የሚችሉ ስጋቶችን አስቀድሞ ለማስወገድ ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል። ቡና ባንክ ከኢንፎርሜሽን ደህንነት አስተዳደር ሲስተምስ ጋር ተያይዞ በርካታ የተለያዩ የተሻሻሉ የደህንነት እርምጃዎችን ተግባራዊ አድርጓል። ISO/IEC 27001፡2022 ሰርቲፊኬሽኑን ተከትሎ ባንኩ ከደንበኞች፣ የቢዝነስ አጋሮች እና ከተቆጣጣሪ አካላት ጋር ያለውን ግንኙነት የበለጠ ያጠናክራል ተብሎ ይታሰባል። የእውቅና ማረጋገጫው ባንኩ ሚስጥራዊ መረጃዎችን ለመጠበቅ እና ተያያዥ አደጋዎችን ለመቀነስ ሁሉንም አስፈላጊ የጥንቃቄ እርምጃዎች እየወሰደ መሆኑን ማረጋገጫ የሚሰጥ ነው ተብሏል። ይህም በመሆኑ የባንኩ ደንበኞች መረጃቸው በከፍተኛ ጥንቃቄ እና ደህንነት እንደተያዘ እምነት እንዲኖራቸው ያደርጋል። ቡና ባንክ አክስዮን ማህበር ያስመዘገበው ይህ ስኬት በአገራችን የባንክ ዘርፍ የመረጃ ደህንነትን በማስፈን ደረጃውን ከፍ ያደረገ አሰራር ሲሆን ባንኩን በፋይናንሺያል ሴክተሩ የሳይበር ደህንነት ጥበቃ ረገድ ግንባር ቀደም አድርጎታል ማለት ይቻላል። ባንኩ በመረጃ ደኅንነት ግንባር ቀደም ሆኖ መቀጠሉን በማረጋገጥ በዘመናዊ የደህንነት ቴክኖሎጂዎች እና አሰራሮች ላይ ኢንቨስት ማድረጉን እንደሚቀጥል አሳውቋል።

ቡና ባንክ አ.ማ የ ISO/IEC 27001፡2022 ሰርተፍኬት አገኘ Read More »

ቡና ባንክ የ5 ቢሊዮን የተከፈለ ካፒታል መጠኑን ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ አስቀድሞ አሳካ

ቡና ባንክ አ.ማ. በብሔራዊ ባንክ የተሻሻለውን የ5 ቢሊዮን አነስተኛ የተከፈለ ካፒታል መጠን በማሳከት ከከኢንዱስትሪ መሪዎቹ ተርታ መሰለፉ ተገለጸ። እ.ኤ.አ. ሚያዝያ 12 ቀን 2021 በወጣው መመሪያ ቁጥር SBB /78/2021 መሰረት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚሰሩ ባንኮች የተከፈለ ካፒታላቸውን እ.ኤ.አ. እስከ ሰኔ 30 ቀን 2026 በትንሹ ወደ 5 ቢሊዮን ብር እንዲያሳድጉ መወሰኑ ይታወሳል።መመሪያው በተላለፈበት ወቅት ከተቀመጠው ገደብ በታች የተከፈለ ካፒታል የነበራቸው ነባር ባንኮች መመርያው ሥራ ላይ ከዋለ በኋላ ባሉት 30 ቀናት ውስጥ የካፒታል ማሳደጊያን የተመለከተ የድርጊት መርሃ ግብር ለብሔራዊ ባንክ እንዲያቀርቡ ተደርጓል። ቡና ባንክ አ.ማ ግን ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ ቀደም ብሎ የተቀመጠውን መስፈርት በማሳካት ከመሪዎቹ ተርታ ተሰልፏል። ይህ ስኬት ባንኩ ለጠንካራ የፋይናንሺያል አፈጻጸም ጤናማነት አፅንዖት መስጠቱን ብቻ ሳይሆን ለተቆጣጣሪ አካላት መመሪያዎች ተገዢነት ያለውን ቁርጠኝነት ያሳያል። ሊሟላ የሚገባው የተከፈለ ካፒታል መጠን ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ ቀደም ብሎ መሟላቱ በቡና ባንክ አ.ማ የዕድገት ጉዞ ላይ እንደ አንድ ትልቅ የዕድገት ምዕራፍ የሚታይ ሲሆን በኢትዮጵያ የባንክ ኢንደስትሪ የሚኖረውን ቁልፍ ሚና ያጠናክራል ተብሎ ይታሰባል። ይህም ስኬት የባለሃብቶችንና የደንበኞችን እምነት የሚያጠናክር ሲሆን የባንኩን አቅም በማጎልበት በዘርፉ የታቀዱ የኢኮኖሚ ልማት ውጥኖችን ለማሳካትም ደጋፊ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። Bunna Bank Surpasses Capital Requirement Milestone Ahead of ScheduleIn a remarkable achievement for the Ethiopian banking sector, Bunna Bank S.C. has successfully met the revised paid-up capital requirements set by the National Bank of Ethiopia. In accordance with Directive No. SBB/78/2021, issued on April 12, 2021, banks operating in Ethiopia were mandated to raise their paid-up capital to a minimum of Birr 5 billion by June 30, 2026.Existing banks that fell short of this threshold were required to submit an action plan for capital increase to the National Bank within 30 days after the directive’s effective date. Bunna Bank S.C., however, has emerged as one of the trailblazer by achieving the minimum requirement well ahead of the stipulated deadline. This accomplishment not only underscores the bank’s robust financial health but also reflects its proactive approach to regulatory compliance.The early fulfillment of the capital requirement marks a significant milestone in Bunna Bank S.C.’s growth trajectory and solidifies its position as a key player in Ethiopia’s banking landscape. This achievement is expected to bolster investor confidence and enhance the bank’s capacity to support economic development initiatives across the nation.

ቡና ባንክ የ5 ቢሊዮን የተከፈለ ካፒታል መጠኑን ከተቀመጠው የጊዜ ገደብ አስቀድሞ አሳካ Read More »

የብድር ወለድ ምጣኔ ማሻሻያ

ቡና ባንክ በፋይናንስ ዘርፍ የሚገባውን ሚና እንዲጫወት ለማስቻል ለሚሰጠው የብድር አገልግሎት ወጪውን ታሳቢ ያደረገ መጠነኛ የብድር ወለድ ምጣኔ ማሻሻያ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል።፡ በዚህም መሰረት እ.ኤ.አ. ከማርች 7 ቀን 2025 ጀምሮ ባንካችን የወለድ ማሻሻያ ተግባራዊ እንደሚያደርግ እያስታወቅን፣ ክቡራን ደንበኞቻችን በአቅራቢያችሁ በሚገኝ የቡና ባንክ ቅርንጫፍ ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የምትችሉ መሆኑን በአክብሮት እንገልጻለን፡፡ቡና ባንክየባለራዕዮች ባንክ!!

የብድር ወለድ ምጣኔ ማሻሻያ Read More »

እንኳን ለታላቁ የረመዷን ወር በሰላም አደረሳችሁ

ለመላው የእስልምና ዕምነት ተከታዮች እንኳን ለ1446ኛው ታላቁ የረመዷን ወር በሰላም አደረሳችሁ እያልን ባንካችን ያዘጋጀውን የተለያዩ ከተሞች የፆም እና የሶላት የጊዜ ሰሌዳ በአቅራቢያዎ በሚገኙ የወለድ ነጻ ቅርንጫፎቻችን እንዲሁም ከዚህ በታች የተቀመጠውን ፋይል መጠቀም የሚችሉ መሆኑን በደስታ እንገልጻለን።ረመዷን ሙባረክ!

እንኳን ለታላቁ የረመዷን ወር በሰላም አደረሳችሁ Read More »

Bunna Bank: 15 Years of Resilience & Growth

In a nation where the banking sector fiercely competes to sustain profitability and financial institutions grapple with maintaining their momentum amidst economic volatility, Bunna Bank stands out as a beacon of resilience and growth. As it celebrates its 15th anniversary, recent reports highlight the Bank’s remarkable performance in the 2023/24 financial year, with significant increases in total assets and deposits—all despite challenging market conditions. Under the astute leadership of Mulugeta Alemayehu, Bunna Bank not only demonstrates impressive financial health but also underscores its commitment to innovation and community engagement through strategic partnerships. Interested in learning how this transformative journey is unfolding? Dive into the summarized news story of the Addis Fortune newspaper, latest Sunday edition to discover the impactful strategies driving Bunna Bank’s success and its vision for the future. News Summary: Addis Fortune, Sunday Edition Feb 23, 2025As Bunna Bank marks its 15th anniversary, it has made headlines for its impressive performance during the 2023/24 financial year, showcasing resilience in a competitive banking landscape affected by inflation and economic strain. Here are the key highlights and major accomplishments:

Bunna Bank: 15 Years of Resilience & Growth Read More »

ቡና ባንክ በታማኝ ከፍተኛ ግብር ከፋይነት የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ ሆነ

6ኛ ዙር የታማኝ ግብር ከፋዮች የምስጋናና የዕውቅና ሽልማት መርሐ ግብር ትናንት መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም በአንድነት ፓርክ ተካሂዷል። በዚህ መርሃ ግብር ላይም ቡና ባንክ በ2016 የበጀት ዓመት ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ ግብር በመክፈል የበጀት አመቱ ታማኝ ከፍተኛ ግብር ከፋይ የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ ሆኗል። የኢፌዲሪ ጠቅላይ ሚኒስትርን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሃገሪቱ ባለስልጣናት በተገኙበትና በአዲስ ፓርክ (ብሄራዊ ቤተመንግስት) ግብር አዳራሽ በተካሄደው በዚሁ ስነስርዓት በተለያዩ መስፈርቶች የተመረጡ 550 ተቋማት ሽልማት ተበርክቶላቸዋል። ከነዚህ መካከልም 66 ኩባንያዎች በፕላቲኒየም፣ 165 ኩባንያዎች በወርቅ እንዲሁም 319 ኩባንያዎች በብር ደረጃ ተሸላሚ ሆነዋል። ቡና ባንክ አምና በ2015 ዓ.ም በተካሄደው ተመሳሳይ መርሃ ግብር በታማኝ ከፍተኛ ግብር ከፋይነት የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ እንደነበር ይታወሳል።

ቡና ባንክ በታማኝ ከፍተኛ ግብር ከፋይነት የፕላቲኒየም ደረጃ ተሸላሚ ሆነ Read More »

15th Years of Anniversary

Dear Valued Shareholders and Customers, We congratulate you on Bunna Bank’s 15th years of anniversary. As we celebrate the 15th anniversary of Bunna Bank, we want to take this opportunity to express my sincere gratitude for your support and trust over the years. This milestone reflects not only our growth and achievements but also the strong relationships we have built with you.#Bunna_Bank #Bank_of_the_Visionaries #15_years_anniversary

15th Years of Anniversary Read More »

This will close in 0 seconds

Open Your Bank Account Today!

አካውንት ይክፈቱ የክፍያ ካርድዎን ያዝዙ ፣ ፈጣን አገልግሎት ማግኘት ይጀምሩ! ዛሬውኑ ይቀላቀሉን!

Open Bunna Account

You cannot copy content of this page