Bunna Bank

Solomon mekbib

🌙 Ramadan Mubarak from Bunna Bank 🌙

ለመላው የእስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለታላቁ እና የተቀደሰው 1447ኛው የረመዷን ጾም በሰላም አደረሳችሁ። ፆሙ የሰላምና የደስታ ይሆንላችሁ ዘንድ ቡና ባንክ ይመኛል። 🙏✨ Special Ramadan Offer – 4% Extra Bonus! ውድ የቡና ቤተሰቦች፣ በረመዷን ወቅት ከውጭ ሀገር ወዳጅ ዘመድ በሀዋላ አስተላላፊ ወኪሎች በኩል የተላከልዎትን ገንዘብ በባንካችን ሲቀበሉ እንዲሁም የውጭ አገር ገንዘብ ሲመነዝሩ ከእለታዊ የመግዣ ተመን ላይ 4% ተጨማሪ ጉርሻ ያገኛሉ። Visit your nearest Bunna Bank branch today! 💡 Bunna Bank – የባለራዕዮች ባንክ! #RamadanMubarak #BunnaBank #SpecialOffer #RemittanceBonus #BankingForYou #TrustedBank #ረመዳንሙባረክ #ቡናባንክ #ልዩእቅድ #ጉርሻ4% #የባለራዕዮችባንክ #ታማኝ_ባንክ

🌙 Ramadan Mubarak from Bunna Bank 🌙 Read More »

መልካም የአብይ ጾም!

✝️ ለመላዉ የክርስትና እምነት ተከታዮች እንኳን ለአብይ ፆም በሰላም አደረሳችሁ! ዘወረደ ብለን ጀምረን ለብርሀነ ትንሳኤዉ በሰላም እንድንደርስ ቡና ባንክ ምኞቱን ይገልፃል፡፡ ቡና ባንክ- የባለራዕዮች ባንክ #Bunnabank #Banking #ForYou #Visionaries #Ethiopian, #Ortodox, #Peace_Full_Time

መልካም የአብይ ጾም! Read More »

🚀 Stay ahead with real-time financial insights and updates!

Join our official Telegram channel @BunnaBankOfficial and experience seamless financial connectivity, instant updates, exclusive offers, and smart banking tips—all in one place. Be part of a growing digital community where convenience meets innovation, and your financial journey becomes faster, smarter, and more connected than ever. 👉 Join now and transform the way you bank. #DigitalBanking #TelegramChannel #FinancialServices #SmartBanking #MobileBanking #FinTech #OnlineBanking #BankingInnovation #EthiopiaBanking #CustomerExperience #FinancialUpdates #SecureBanking #DigitalFinance #BunnaBank #FinancialCommunity

🚀 Stay ahead with real-time financial insights and updates! Read More »

የባንክ ሒሳብ ቁጥርዎን ከብሔራዊ መታወቂያ ቁጥርዎ (ፋይዳ) ጋር ያስተሳስሩ!

https://verifayda.bunnabanksc.com የባንክ ሒሳብ ቁጥርዎን ከብሔራዊ መታወቂያ ቁጥርዎ (ፋይዳ) ጋር ያስተሳስሩ! 📲 ለተጨማሪ መረጃ ወደ ባንካችን ነፃ የጥሪ ማዕከል 8501 ይደውሉ። ቡና ባንክ የባለራዕዮች ባንክ #bunnabank #fyda #link #account #nationalID #bunnafayda #fydanumber

የባንክ ሒሳብ ቁጥርዎን ከብሔራዊ መታወቂያ ቁጥርዎ (ፋይዳ) ጋር ያስተሳስሩ! Read More »

መልካም የልደት በዓል! 🎈🎉

ቡና ባንክ ለመላው ህዝበ ክርስቲያን እንኳን ለጌታችንና ለመድሀኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ እያለ በዓሉ የሰላምና የፍቅር እንዲሆንልን ከልብ ይመኛል! መልካም ገና! 🥳🙌 ቡና ባንክ የባለራዕዮች ባንክ! #ethiopianchristmas🎄💚💛❤️ #xmas #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #bunnabank  

መልካም የልደት በዓል! 🎈🎉 Read More »

ቡና ባንክ የISO/IEC 27001:2022 ዓለም አቀፍ የመረጃ ደህንነት ኦዲትን በስኬት ማጠናቀቁን አስታወቀ

በኢትዮጵያ የባንክ ኢንዱስትሪ ውስጥ በዘመናዊ አሰራሩ የሚታወቀው ቡና ባንክ፣ የISO/IEC 27001:2022 የመረጃ ደህንነት አስተዳደር ሥርዓት (ISMS) የክትትል ኦዲትን በስኬት ማጠናቀቁን በይፋ አስታውቋል። ይህ ከፍተኛ ዓለም አቀፍ እውቅና የተገኘው ባንኩ የመጀመሪያውን የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት በተቀበለ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ሲሆን፣ ይህም ተቋሙ ለላቀ የዲጂታል ስታንዳርድ እና ለመረጃ ጥራት የሰጠውን ከፍተኛ ትኩረት የሚያሳይ ትልቅ ስኬት ተደርጎ ተወስዷል። የተካሄደው የክትትል ኦዲትም የባንኩ የመረጃ ደህንነት መዋቅር አሁንም ድረስ እጅግ አስተማማኝ፣ ወቅታዊ እና አዳዲስ የዓለም አቀፍ መስፈርቶችን በሚገባ የሚያሟላ መሆኑን ዳግም ያረጋገጠበት ሆኗል። በአሁኑ ወቅት በመላው ዓለም የሳይበር ጥቃቶች ስልታቸውን እየቀያየሩና ይበልጥ እየረቀቁ በመምጣታቸው፣ ቡና ባንክ ለዚህ ጉዳይ የሰጠው ትኩረት ተራ የቁጥጥር ስራን ማለፍ ብቻ ሳይሆን ደንበኞቹን ካልተጠበቀ አደጋ ለመታደግ ያለውን ዝግጁነት የሚያንፀባርቅ ነው። ባንኩ ይህንን የላቀ ደረጃ ማሟላቱ የደንበኞቹን የግልና የፋይናንስ መረጃዎች በከፍተኛ ጥንቃቄና በሚስጥር ለመጠበቅ ያለውን ጽኑ አቋም የሚያሳይ ሲሆን፣ ከዚህም በተጨማሪ ማንኛውንም አይነት የደህንነት ስጋቶች አስቀድሞ የመለየት፣ የመከላከል እና ድንገተኛ አደጋዎች ቢከሰቱም እንኳ የባንኩን መደበኛ ስራ ሳይስተጓጎል በፍጥነት የማስቀጠል አቅሙን (Operational Resilience) በሚገባ አሳድጓል። ይህ ስኬት ባንኩ በአገር ውስጥና በዓለም አቀፍ ደረጃ በፋይናንስ ተቋማት ላይ የሚጣሉ ጥብቅ የደህንነት መመሪያዎችንና የሕግ ማዕቀፎችን በሚገባ ማክበሩን ለባለድርሻ አካላት ማረጋገጫ የሰጠበት አጋጣሚ ሆኖ አልፏል። ለዚህ አመርቂ ውጤት መገኘት የባንኩ አመራሮችና መላው ሰራተኞች ላሳዩት ከፍተኛ ትጋትና ቅንጅት የባንኩ ከፍተኛ አመራር ምስጋናቸውን አቅርበዋል። ይህ ስኬት የጋራ ጥረት ውጤት መሆኑን በመጥቀስ፣ የተገኘው የብቃት ማረጋገጫ ከደንበኞች፣ ከአጋር ድርጅቶችና ከመንግስት ተቆጣጣሪ አካላት ጋር ያለውን የቆየ እምነትና ታማኝነት ይበልጥ እንደሚያጠናክረው ገልጸዋል። በመሆኑም ቡና ባንክ የISO/IEC 27001:2022 ዓለም አቀፍ ማዕቀፍን እንደ መርህ በመጠቀም፣ የመረጃ ደህንነትን ከባንኩ የዕለት ተዕለት ተግባራትና ከእያንዳንዱ ዲጂታል ግብይት ጋር በማስተሳሰር፣ በቀጣይም በቴክኖሎጂ የታገዘና አስተማማኝነቱ የተረጋገጠ የባንክ አገልግሎት ለህዝቡ ለማቅረብ ቁርጠኝነቱን በድጋሚ አረጋግጧል። Bunna Bank Reaffirms Security Excellence with Successful ISO/IEC 27001:2022 Audit Bunna Bank is proud to announce that it has successfully passed the ISO/IEC 27001:2022 Surveillance Audit, marking a significant milestone in its journey toward digital excellence and data integrity. Coming just one year after the bank’s initial certification, this successful audit confirms that Bunna Bank’s Information Security Management System (ISMS) remains robust, up-to-date, and fully compliant with the latest international standards. Strengthening the Trust Foundation In an era where cyber threats are increasingly sophisticated, this achievement underscores Bunna Bank’s proactive approach to safeguarding its information assets. The successful surveillance audit is not just a regulatory checkmark; it is a testament to the bank’s commitment to: • Protecting Customer Data: Ensuring the highest levels of confidentiality and integrity for client information. • Operational Resilience: Strengthening the bank’s ability to detect, respond to, and recover from security incidents. • Regulatory Compliance: Meeting and exceeding both local and international benchmarks for financial data security. A Collaborative Success The bank’s leadership extended its gratitude to the entire staff for their role in this achievement. “This milestone reflects our continued commitment to maintaining a world-class ISMS and strengthening the trust we share with our customers, partners, and regulators. A sincere thank you to our management and teams for their dedication, collaboration, and ongoing efforts to sustain these international standards.” By adhering to the ISO/IEC 27001:2022 framework, Bunna Bank ensures a culture of continual improvement, ensuring that security is woven into the fabric of every digital transaction and internal process.

ቡና ባንክ የISO/IEC 27001:2022 ዓለም አቀፍ የመረጃ ደህንነት ኦዲትን በስኬት ማጠናቀቁን አስታወቀ Read More »

የቡና ባንክ ባለአክሲዮኖች 16ኛ መደበኛ እና 7ኛ አስቸኳይ ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ

ቡና ባንክ ዓመታዊ የባለአክሲዮኖች ጠቅላላ ጉባዔውን አካሄደ በታሪኩ ከፍተኛ የሆነውን ከ2.6 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ አስመዝግቧል፤ የአንድ አክሲዮን ትርፍ 146.7 በመቶ አድጓል ። የ5 ቢሊዮን ብር ዝቅተኛ የተከፈለ ካፒታል መጠንን ከአንድ ዓመት ቀድሞ አሳክቷል፡፡ ቡና ባንክ አ.ማ ዓመታዊውን የባለአክሲዮኖች 16ኛ መደበኛ ጠቅላላና 7ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔውን ቅዳሜ ህዳር 13ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ ኢንተርናሽናል ኮንቬንሽን ሴንተር አካሂዷል።  በርካታ ቁጥር ያላቸው ባለአክሲዮኖች በታደሙበት በዚሁ ጉባዔ ላይ የቡና ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር አቶ ሙሉጌታ አስማረ የባንኩን እኤአ የ2024/25 የሂሳብ ዓመት ሪፖርት ለባለአክሲዮኖች አቅርበዋል። በሪፖርቱ እንደተገለጸው፣ እኤአ በ2024/25 የሥራ ዘመን ባንኩን ወደ አዲስ የላቀ የአፈጻጸም ምዕራፍ ያሸጋገረ የፋይናንስ ውጤት መመዝገቡ ይፋ ተደርጓል። በዚህም ባንኩ በሂሳብ ዓመቱ ያጋጠሙ የኢኮኖሚ ውጥረቶችንና ተግዳሮቶችን በብቃት ተቋቁሞ፣ ከታክስ በፊት 2.627 ቢሊዮን ብር ትርፍ አስመዝግቧል፤ ይህም ከባለፈው ዓመት 930 ሚሊዮን ብር የትርፍ አፈጻጸም ጋር ሲነፃፀር የ182.5 በመቶ ዕድገትን የሚያንጸባርቅ ታሪካዊ ስኬታማ ውጤት ነው ተብሏል። በተጨማሪም፣ ባንኩ በሂሳብ ዓመቱ በአንድ ሺህ ብር አክሲዮን ላይ ያስመዘገበውን ትርፍ (Earnings Per Share) ባለፈው ዓመት ከነበረው 161.57 ብር የ146.7 በመቶ ዕድገት በማስመዝገብ ወደ 398.65 ብር ከፍ ማድረግ ችሏል። ከዚህ ታሪካዊ የትርፍ ብልጫ ባሻገር፣ ባንኩ የረጅም ጊዜ የፋይናንስ መዋቅራዊ ጥንካሬውን የበለጠ በማጎልበት፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ያስቀመጠውን የ5 ቢሊዮን ብር ዝቅተኛ የተከፈለ ካፒታል መጠን አንድ ዓመት ቀድሞ በማሳካት፣ የተከፈለ ካፒታሉን ወደ 5.054 ቢሊዮን ብር በማድረስ የባንኩን የዕድገት መሠረት አጠናክሯል። ይህንን የላቀ ውጤት ለባለአክሲዮኖች ይፋ ያደረጉት የባንኩ የዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር አቶ ሙሉጌታ አስማረ፣ ባቀረቡት ሪፖርት እንደገለጹት፣ “ይህ ስኬት የቡና ባንክ ጠንካራ የሥራ ባህልና የረጅም ጊዜ ስትራቴጂያዊ ራዕይ ፍሬ ነው። የትርፍ መጠኑን ወደ ላቀ ደረጃ ከፍ ከማድረግ በተጨማሪ፣ ካፒታላችንን በማጎልበት ለባንካችን ቀጣይ አዳዲስ ፈጠራና መስፋፋት የሚሆን የማይናወጥ መሠረት መጣል ተችሏል” በማለት የሂሳብ ዓመቱን ስኬት ገልጸዋል። በሪፖርቱ እንደተመለከተው፣ የባንኩ አጠቃላይ ሀብት ይህንኑ ጥንካሬ በሚያንጸባርቅ መልኩ በ20.3 በመቶ አድጎ 65.58 ቢሊዮን ብር ላይ ደርሷል። ከዚህ በተጓዳኝ ባንኩ ጠንካራ የሀብት ማሰባሰብ ሥራ በመሥራት ጠቅላላ የተቀማጭ ገንዘቡን በ16.7 በመቶ በማሳደግ 51.2 ቢሊዮን ብር ላይ አድርሷል። በተለይም 65.0 በመቶ የሚሆነው የተቀማጭ ገንዘብ የቁጠባ ሂሳብ መሆኑ፣ የባንኩን የገንዘብ ምንጭ መረጋጋትና ዘላቂነት በግልጽ ያሳያል ሲል ባንኩ አስታውቋል። ሪፖርቱ እንደሚያሳየው ባንኩ የገቢ ምንጮቹን በብቃት በማቀናጀት የባንኩ ጠቅላላ ገቢ በ46.2 በመቶ አሳድጎ 11.739 ቢሊዮን ብር የደረሰ ሲሆን፣ ከዚህ ጎን ለጎን የውጭ ምንዛሪ ግኝትንም በ16.5 በመቶ በመጨመር 195.2 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር መሰብሰብ መቻሉም በዳይሬክተሮች ቦርድ ሪፖርት ተጠቅሷል። በተጨማሪም ባንኩ የብድር አቅርቦቱን በ9.8 በመቶ አሳድጎ 42.69 ቢሊዮን ብር ያደረሰ ሲሆን፣ ከዚህ ጋር ተያይዞ የመክፈያ ጊዜ ያለፈባቸው ብድሮች ምጣኔ (NPL) ከብሔራዊ ባንክ የ5 በመቶ ገደብ በታች 4.09 በመቶ ሆኖ እንዲመዘገብ በማድረግ፣ የብድር አስተዳደር ጥራቱን አረጋግጧል ብለዋል የዳይሬክተሮች ቦርድ ሰብሳቢ አቶ ሙሉጌታ አስማረ በንግግራቸው ። ሰብሳቢው አክለው እንደተናገሩት በዘመናዊ የባንክ አገልግሎት መስክ ቡና ባንክ የዲጂታል ሽግግሩን በማጠናከር፣ የሞባይል ባንኪንግ ግብይት መጠኑን ወደ 40.4 ቢሊዮን ብር ከፍ ያደረገ ሲሆን በተለይም በቅርቡ በጀመረው የዲጂታል ብድር አገልግሎት እስከ ጁን 30 ድረስ ብቻ 2.64 ቢሊዮን ብር ብድር በማቅረብ በገበያ ትስስሩ ያለውን የጎለበተ አቅም በተግባር አሳይቷል ብለዋል። ከዚህም ባሻገር ቡና ባንክ ማህበራዊ ኃላፊነትን እንደ ወሳኝ ጉዳይ በመያዝ ለተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች በድምሩ 20.3 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማበርከቱ ተጠቅሷል። ቡና ባንክ በ2030 ከሃገሪቱ ግንባር ቀደም ሦስት የፋይናንስ ተቋማት አንዱ የመሆን ራዕዩን ለማሳካት ስትራቴጂያዊ እቅዱን በቁርጠኝነት መፈጸም መቀጠሉን አስታውቋል። በቀጣይ ዓመት የአደረጃጀት መዋቅር ለውጥን ማጠናቀቅ፣ የዲጂታል ባንክ አገልግሎቶችን እና የብድር ተደራሽነትን ማስፋፋት፣ እንዲሁም የዋና መ/ቤት ሕንፃ ግንባታን በታቀደለት የጊዜ ሰሌዳ ማጠናቀቅ ዋና የትኩረት አቅጣጫዎች እንደሚሆኑ ሪፖርቱ ያሳያል። አቶ ሙሉጌታ አስማረ የባንኩን ዓመታዊ አፈጻጸም አስመልክቶ በንግግራቸው እንደጠቀሱት፣ “በሂሳብ ዓመቱ የተመዘገበው ድል በሁሉም ባለድርሻ አካላት መካከል ያለውን ጠንካራ ትብብር ማሳያ ነው ያሉ ሲሆን አክለውም ለጋራ ዕድገትና ብልጽግና በትጋት መስራታችንን ከምንጊዜውም በላይ አጠናክረን እንቀጥላለን” በማለት አጽንኦት ሰጥተው ተናግረዋል። በመጨረሻም የቦርድ ሊቀመንበሩ ባስተላለፉት መልዕክት ሁሉም የቡና ማህበረሰብ አባላት እጅ ለእጅ ተያይዘው ባንኩን ወደተሻለ ደረጃ ለማሻገር እንዲሰሩ የጠየቁ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እንደሁልጊዜው ሁሉ ለባንኩ ጥያቄዎች ተገቢውን ምላሽ በመስጠት በዘርፉ ጤናማ ውድድር እንዲኖር ስላደረገው ከፍተኛ አስተዋፅኦም አመስግነዋል፡፡ የባለራዕዮች ባንክ የሆነው እና ከተመሰረተ 16 ዓመታትን ያስቆጠረው ቡና ባንክ ከ14 ሺህ በላይ ባለአክሲዮኖችና ቁጥራቸው ወደ 4000 የሚጠጋ ቋሚ ሰራተኞች ያሉት በመላው የአገሪቱ ክፍሎች በሚገኙ 454 ቅርንጫፎቹ የባንክ አገልግሎቶችን በመስጠት ላይ የሚገኝ ባንክ ነው።                                                                         ሕዳር 13፣ 2018 ዓ.ም.                                                                       ኮርፖሬት ኮሚዩኒኬሽንስ ዳይሬክቶሬት                                                                                           ቡና ባንክ ለበጠ መረጃ ኢሜይል: communications@bunnabanksc.com ድረ-ገጽ: https://www.bunnabanksc.com ስልክ፡ +251911403884፣ +251945598585

የቡና ባንክ ባለአክሲዮኖች 16ኛ መደበኛ እና 7ኛ አስቸኳይ ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ Read More »

የጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ

የቡና ባንክ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 16ኛ መደበኛ እና 7ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ህዳር 13 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ ዓለም አቀፍ የስብሰባ ማዕከል ስለሚካሄድ፤ ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ተወካዮች በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ቦታ በጉባዔው ላይ እንድትገኙ የማህበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ የአክብሮት ጥሪውን ያቀርባል፡፡ቡና ባንክየባለራዕዮች ባንክ! AGM #16th #BunnaBank #ShareHolders #Visionaries #Ethiopia

የጠቅላላ ጉባዔ ጥሪ Read More »

የቡና ባንክ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 16ኛ መደበኛ እና 7ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔዎች ጥሪ

በኢትዮጵያ ንግድ ሕግ አንቀፅ 366/1/፣ 367/1/፣ 370፣ እና በባንኩ መመስረቻ ፅሑፍ አንቀፅ 21 እና 22 መሰረት የቡና ባንክ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 16ኛ መደበኛ እና 7ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔ ህዳር 13 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት ጀምሮ በአዲስ ዓለም አቀፍ የስብሰባ ማዕከል ስለሚያካሂድ፤ ባለአክሲዮኖች ወይም ሕጋዊ ተወካዮች በተጠቀሰው ቀን፣ ሰዓትና ቦታ በጉባዔው ላይ እንድትገኙ የማህበሩ የዳይሬክተሮች ቦርድ የአክብሮት ጥሪውን ያቀርባል፡፡                                                       ድረ ገጽ፡ http://www.bunnabanksc.com/ ማሳሰቢያ የቡና ባንክ አ.ማ የዳይሬክተሮች ቦርድ

የቡና ባንክ አ.ማ የባለአክሲዮኖች 16ኛ መደበኛ እና 7ኛ አስቸኳይ ጠቅላላ ጉባዔዎች ጥሪ Read More »

This will close in 0 seconds

Open Your Bank Account Today!

አካውንት ይክፈቱ የክፍያ ካርድዎን ያዝዙ ፣ ፈጣን አገልግሎት ማግኘት ይጀምሩ! ዛሬውኑ ይቀላቀሉን!

Open Bunna Account

You cannot copy content of this page